የደባርቅ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች/Debark woreda pp supportres

  • Home
  • Ethiopia
  • Debark'
  • የደባርቅ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች/Debark woreda pp supportres

የደባርቅ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች/Debark woreda pp supportres Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የደባርቅ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች/Debark woreda pp supportres, ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ, Debark'.

08/10/2025
22/09/2025

የትምህርት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነዉ !!
ህጻናት ይማሩ!

የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት እና ብልጽግና ማምጣት የሕዝቦቿን ኑሮ ማሳደግ የሚቻለው በሚኖራት የተማረ የሰው ኃይል እምቅ አቅም ነዉ።

እንደሀገር ለመጽናት እንደ ህዝብ ለመኖርም ትምህርት ላይ መስራት ብቸኛዉ መዉጫ መንገድ መሆኑ ሀቅ ነዉ።

ትምህርት ዘላቂ የአስተሳሰብ ለውጥን በማምጣት ፣ የአንድን ሀገር ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና በማረጋገጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ከቤተሰብ ጀምሮ ማህበረሰቡ በጋራ መስራት ይኖርበታል።

በክልላችን ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና ወጣቶች ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲገቡና ያለአንዳች የጊዜ ብክነት ማግኘት ያለባቸውን የትምህርት ፍሬ እንዲያገኙ ማስቻል ይጠበቅብናል።

በዚህ ረገድ በትምህርት ዘመኑ ያለው አጀማመር ካለፉት ጊዜያት ለውጦች ቢኖሩትም አሁንም ፈጣን ጥረትና እገዛ ከሁላችንም ይጠበቃል።

!
!
!
!

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

21/09/2025

"ትምህርት አገር ይገነባል ፤ ትውልድን ያስቀጥላል"

በእርግጥም በዘመነ ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ትምህርት የህልውና መሰረት ነው፡፡ ይህ እውነታ በዋነኝነት ዘመናችን ከተመሰረተበት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ሥርዓት ባህሪ የሚመነጭ ነው፡፡ የአለም የኃይል አሰላለፍ የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎት፣ አስተሳሰብና ባህል በመፍጠር፤ ትምህርት መንግሥታት ለሚመኙት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና ዐብይ ሚና ይጫወታል:: በዚህ መነሻ የክልላችን መንግሥት ለትምህርት ጥራት ከፍ ያለ ትኩረት ይሰጣል። የነገ ሀገር ተረካቢዎች በትምህርት ዙሪያ ሊገነዘቧቸው ከሚገባቸው ወሳኝ እውነታዎች ውስጥ ቀዳሚው ትምህርት የዓለም ሥርዓት መቆጣጠሪያ ትልቁ መሳሪያ መሆኑን ነው።

በዚህ መነሻ የትምህርትን አስፈላጊነት እንዲህ እንቃኘዋለን:-

1. የኅብረተሰብ ዕድገት እና መሻሻል

ትምህርት የኅብረተሰብ ዕድገት እና መሻሻል ቁልፍ አካል ነው። ሰዎች ሲማሩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለህብረተሰቡ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስለሚያደርጉ የተረጋጋ እና አነቃቂ ማኅበረሰብ መፍጠር ይችላሉ።

በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የትምህርት አስፈላጊነት የሀገር ዕጣ ፈንታን ለመወሰን ትልቁ አቅም ሆኖ ያገለግላል። የአንዲት ሀገር ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በተማሩ ዜጎቿ ጥረት ነውና፡፡

2. ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት

ትምህርት በአገራት ልማት ውስጥ የጋራ ድጋፍ እና መረጋጋት ምንጭ ነው። የአንድ ሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ ከትምህርት ጋር በቅርበት የተያያዘ ነው። በትምህርት ሥርዓቱና ዝማኔው ወደኋላ የቀረ አገር የዳበረ ኢኮኖሚ ሊገነባ አይችልም። ከተፈጥሮ ሀብት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ አቅም ቢኖረው እንኳ በተማረ የሰው ኃይል (በትምህርት በታነፀ ትውልድ) ካልተደገፈ ኢኮኖሚው ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው ሊሆን አይችልም።

3. ጥሩ ዜጎችን መፍጠር

ትምህርት በኅብረተሰቡ ውስጥ የሰለጠነ እና ትክክለኛ ስነ ምግባር ያላቸውን ሰዎች ብቁ አድርጎ ያፈራል። እነዚህ እውቀት ያላቸው ሰዎች ትክክለኛ ሀሳቦችን ይፀንሳሉ፣ መጨረሻም ለታላቅ ሕልውና ይጓዛሉ። የህግ ጥሰት ወይም የሥርዓት አልበኝነት ችግር በምንም መልኩ እውቀት ባላቸው ዜጎች ማኅበረሰብ ውስጥ አይገጥምም። በአንድ አገር ውስጥ ጤናማ የትውልድ ቅብብል ሊኖር የሚችለው ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ሥርዓት ሲፈጠር ነው።

4. የተሻሻለ ማኅበረሰብ

አሁን ባለንበት ዓለም፣ እንደ ኢትዮጵያም ሆነ እንደ አማራ ክልል በሕዝባችን ውስጥ ትምህርት ማግኘት በዙሪያችን ባሉ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ ሰፊያ የገበያ አቅም ባለው ቀጠና ውስጥ የበቃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ወሳኙ መንገድ በትምህርት ተሽሎ መገኘት ነው።

5. የበለፀገ ሕይወት መስጠት

ትምህርት ሁል ጊዜ በኅብረተሰብ ውስጥ ከፍ ያለ ነው። ምቹ የአኗኗር ዘይቤን ለማረጋገጥ ሰዎች ራሳቸውን ማስተማር እና ስኬታማ እና እርካታ ለማግኘት ጥሩ ገቢ ያለው ሥራ ለማግኘት በትምህርት የበቁ መሆን አለባቸው።

ትምህርት የተሻለ ዝና ለማግኘት፣ በጎ ተፅዕኖ ለማምጣት አቅምና ጉልበት ይሆናል፤ በፍጥነት የስኬት መሰላልን የመውጣት ዕድልን ይጨምራል። ትምህርት የበለፀገ ሕይወት ለመምራት ተመራጭ መንገድ ነው።

6. ወደ ማህበረሰቡ መመለስ
የተማሩ ሰዎች በተረጋጋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ማኅበረሰብ ውስጥ መኖር ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ይገነዘባሉ። አካባቢያቸውን ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡንም ለማሻሻል በሚረዱ ፕሮጀክቶች ላይ የመሳተፍ ዕድላቸው ሰፊ ነው። በአካባቢያቸው ያሉ አካባቢያዊ ችግሮችን በመፍታት የመሳተፍ ዕድላቸው ሰፊ ነው። ለአንድ ግለሰብ ጥሩ ትምህርት፣ ግለሰቡን በግል፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርገዋል። ትምህርት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንን በተሻለ መንገድ እንድንሰራ ይረዳናል።

በተለይም፦
ሀ. የሞራል እና የሥነ-ምግባር እሴቶች

አንድን ግለሰብ እንዲያስብ እና እንዲያሰላስል የሚያደርግ በመሆኑ፣ ማንኛውም ነገር አንድ እርምጃ ወደ ተሻለ ውሳኔ እንዲመራ ያደርጋል (አቅም ይፈጥራል)

ለ. የመፍጠር እና የማሰብ ችሎታዎች

ትምህርት የአንድን ሰው የፈጠራ ክህሎት ያሻሽላል። አንድ ሰው ችሎታውን በፈጠራ አቀራረቦች እንዲጠቀም እና የበለጠ ከፍ እንዲል ዕድሉን ያቀርባል፡፡ ትምህርት ያላቸው ሰዎች በደንብ ማሰብ እና ማሰብ ይችላሉ፡፡ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲያንጸባርቁ እና እንዲተነትኑ አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡

ሐ. ምቹ ኑሮ መኖር
ሁሉም ሰው ምቹ ኑሮ መኖር ይመኛል ነገር ግን ይህ እንዲሆን ሰውየው የተማረ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ዘላቂ ሀብት ምንጩ ትምህርት ነውና። አንድ ሰው የተሻለ ኑሮን ለማግኘት እና የተደላደለ ኑሮ ለመኖር የትምህርትን ጥቅም ተረድቶ መማር አለበት።

መ. በሀገራት ዜጎች መካከል እኩልነት

የየትኛውም ሀገር ዜጋ እኩል እስከተማረ ድረስ በትምህርት ዓለም እኩል ዕድል ይኖረዋል፡፡ የዓለምን ሥርዓት የመቅረፅና የመምራት አቅም የገነቡ አገራት ትልቁ መሳሪያቸው ትምህርት ነው። በየትኛውም ዓለም የተሻለ የትምህርት አቅም ያላቸው ዜጎች በየትኛውም አገር ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ ነው።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

20/09/2025

ሀገር የገጠማትን ስብራት በዘላቂነት ለመጠገን ትምህርት ላይ መሥራት ግድ ይላል።

የነገዋ ሀገር የምትገነባው በዛሬዎቹ ተማሪዎች ትከሻ ላይ ነው ። በተማሪዎች እና ትምህርት ላይ አልሞ መሥራት ትውልድ ላይ መሥራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ። አማራ ክልል ባለፉት ዓመታት በገጠሙት የሰላም እጦት ምክንያት ከተጎዱ ተቋማት መካከል የትምህርት ዘርፉ አንዱ ነው።

ያለፈው ዓመት ደግሞ በውስጥ በገጠመን የፀጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ ተነጥለው የከረሙ ልጆች ቁጥር ከፍተኛ ነዉ፡፡ ምናልባትም ዛሬ እንደሀገርም ሆነ እንደ ክልል የገጠመን ችግር የትምህርት ሥርዓቱ ስብራት ውጤት ሊሆን ይችላል ፤ ሀገር የገጠማትን ስብራት በዘላቂነት ለመጠገን ትምህርት ላይ መሥራት ግድ ይላል፡፡

የትምህርት ዘርፉ መሪዎች፣ የወላጅ መምህራን ኅብረት፣ ምሁራን እና ሌሎች የሚመለከታቸው ዜጎች ሁሉ የትምህርት ሥርዓታችን የገጠመውን ስብራት ለመጠገን ተቀራርበው መምከር አለባቸው፡፡ ትላንት የገጠመን ችግር ነገም የሚፈትነን ከኾነ መሠረታዊ ክፍተት አለና በሚገባ መመርመር ይገባል ፡፡

•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

ልግመኛ ሰው ራዕይ የለዉም!ልግመኝነት በመደመር ፍልስፍና ሊወገድ የሚገባ እና እንደቀይ መስመር የሚታይ ጉዳይ ነው። ልግመኝነት ያቀድነውን ሁሉ የሚያመክን፣ የወጠንነውን፣ የወጥነውን የሚያጨናግ...
15/08/2025

ልግመኛ ሰው ራዕይ የለዉም!

ልግመኝነት በመደመር ፍልስፍና ሊወገድ የሚገባ እና እንደቀይ መስመር የሚታይ ጉዳይ ነው።
ልግመኝነት ያቀድነውን ሁሉ የሚያመክን፣ የወጠንነውን፣ የወጥነውን የሚያጨናግፍ፣ የተለምነውን የሚያፈርስ፣ ወደፊት ያሰብነውን ወደኋላ የሚጎትት ክፉ ልማድ ነው።
#መደመር

29/07/2025
"ብልጽግና ፓርቲ የጠራና ተሻጋሪ ሃሳብ ባለቤት በመሆኑ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው"አቶ ፍስሃ ደሳለኝየአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘ...
10/07/2025

"ብልጽግና ፓርቲ የጠራና ተሻጋሪ ሃሳብ ባለቤት በመሆኑ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው"
አቶ ፍስሃ ደሳለኝ
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን፤ ካልሆነ ግን ራሳችን እንከላከላለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጎረቤት ሀገራት ጋር...
03/07/2025

ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን፤ ካልሆነ ግን ራሳችን እንከላከላለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን፤ ካልሆነ ግን ራሳችን እንከላከላለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ውጊያ አንፈልግም፣ ውጊያን አንመርጥም፣ ትብብርና በጋራ ማደግን ነው የምንፈልገው ብለዋል፡፡

ከሁሉም ወንድሞቻችን ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በሰላም የማያኖር ጉዳይ ካለም ራሳችን እንከላከላለን ብለዋል፡፡

ለዚህም በኢትዮጵያ ወገን የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ ነው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ውጭ ህልውና የላትም፤ ከኢትዮጵያ ውጭ ጎረቤቶቻችንም ህልውና የላቸውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ያልተፈቱ ችግሮች ስለነበሩ በዚያ ምክንያት ወጣ ገባ የሚሉ ጉዳዮች እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚ፣ የሕዝብ ቁጥር፣ የዘመነ ሰራዊት ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው÷ ከኤርትራ ጋር የጦርነት ስጋት ለሚያነሱ አካላት በእኛ በኩል ምንም ዓይነት ውጊያ እንደማንፈልግ ማወቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ ኢትዮጵያ ትጸናለች፤ ለማጽናት የሚያበቃ በቂ አቅም አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ በታሪክ ጠላቶች ነበሯት፤ አሏት፤ አይናቸው እያየ ግን እናንሰራራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

Address

ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ
Debark'
0581170450

Telephone

0581170450

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደባርቅ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች/Debark woreda pp supportres posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share