03/06/2026
በየጣቢያው ድምጽ የተሰጠበት መረጃ በምርጫ ክልሎች ላይ እየተደመረ ነው - ቦርዱ
ግንቦት 26፣ 2018 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየጣቢያው ድምጽ የተሰጠበት መረጃ ወደ ምርጫ ክልሎች ሄዶ የማዳመር ስራ እየተሰራ ይገኛል አለ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት፤ በትናንትናው ዕለት የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ አጠናቅቀው በምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ለጥፈዋል።
በየጣቢያው ድምጽ የተሰጠበት መረጃ ወደ ምርጫ ክልሎች ሄዶ የማዳመር ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ቀደም ብለው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት የጨረሱና የድምጽ ቆጠራ አጠናቀው ውጤት የለጠፉ ጣቢያዎች ሰነዶችን ወደ ምርጫ ክልል የላኩት ሰነድ ወደ ማዕከል ጉዞ መጀመሩን ጠቅሰዋል።
ውጤቱን የማዳመር ስራ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፤ በቦርዱ በተዘጋጁ ቅጾች በአግባቡ ተሞልተውና ተዘጋጅተው መምጣት አለባቸው ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ድምጽ ከተሰጠ በኋላ በውጤት ማመሳከሪያና ማሳወቂያ ቅጽ ውጤቱ ይሞላል፤ እያንዳንዱ ዕጩ ያገኘው ውጤት በቁጥር ይገለጻል ሲሉ አብራርተዋል።