12/11/2025
አስደንጋጭ የሕግ ጥሰት በሻሸመኔ ! 🥹😢
: ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሻሸመኔ ከተማ በቅንጦት ሰርግ ደምቃ ነበር ። በዚህ ሰርግ የቅንጦት መኪናዎች ፣ ታላላቅ ፌስቲቫሎች ታይተውበታል ። ነገር ግን አንድ የሰርጉ ተሳታፊ የሻሼን ድባብ ረብሾታል ።
የከተማዋ መሀል አደባባይ (Town Square) ላይ በአደባባይ ሽጉጥ መዝዞ በርካታ ጥይቶችን አርከፍክፏል ። በአካባቢው የነበሩ ሰላማዊ ነዋሪዎችን ክፉኛ አስደንግጧል።ይህ አስደንጋጭ እና ትዕቢት የተሞላበት የሕግ ጥሰት ብዙዎችን አስደንግጧል ፣ አስቆጥቷል ።
በጠራራ ፀሐይ እንዲህ አይነቱ የሕግ ጥሰት እና ስርአት አልበኝነት እንዴት ሊፈፀም ቻለ? በማለት ጥያቄ ያነሱም አሉ። የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር እንዲህ ዓይነቱ ልቅ የሕግ ጥሰት ተደጋግሞ እንዳይከሰት ምን ዓይነት አስቸኳይ እርምጃ ይወስዳል?
* ይህ ድርጊት ለሕዝብ ደኅንነት እና ለሕግ የበላይነት ስላለው ክብር ምን ዓይነት መልእክት ያስተላልፋል?
ሕግን ማክበር የሁላችንም ግዴታ ነው! ከሕግ በላይ ማንም የለም! ግንዛቤን እናሳድግ!
ይህ ነገር በእውነቱ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ ?ሀሳባችሁን አካፍሉን ?