በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት, Government Organization, ምስራቅ ጉራጌ ዞን/መስቃን ወረዳ/ቡታጅራ, Butajira.

This is our official real Meskan District page, follow and like it to get updated information.
ይህ ትክክለኛ የመስቃን ወረዳ የፌስ ቡክ ፔጃችን ነው ፎሎና ላይክ በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲደርሶ ያድርጉ።

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! #ግንቦት 25 2018 ዓ.ምየመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

#ግንቦት 25 2018 ዓ.ም

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

FDREGovermentCommunication

7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና የህዝብ ድምፅ የተከበረበት ነው - ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችበተካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ የምርጫ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ፣ ተአማኒና የህዝብን ድምፅ ያከበ...
02/06/2026

7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና የህዝብ ድምፅ የተከበረበት ነው - ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

በተካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ የምርጫ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ፣ ተአማኒና የህዝብን ድምፅ ያከበረ ሂደትን የተከተለ መሆኑን መታዘባቸውን የተለያዩ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ገለፁ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች ምርጫው ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን ከዚህ ቀደም ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች ወደ ውጤት እየተቀየሩ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)የመስቃን ማረቆ ምርጫ ቁጥር 1 የፓርቲው የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ እሸቱ ዘለቀ፤ ምርጫው እስካሁን ባለው ሂደት ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት አሁን እስካለበት የምርጫ ሂደት ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት የታየበት መሆኑን አንስተው፤በድህረ ምርጫ ወቅትም ቀድመው የታዩ ሰላማዊ ሂደቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በጋራ ምክር ቤት በምርጫው ሂደት ዙሪያ የተደረጉ ውይይቶች ዛሬ ላይ ለተመዘገቡ ውጤቶች የጎላ አበርክቶ እንደነበራቸው አመላክተዋል።

የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ኸይሩ ሀምዛ በበኩላቸው፤ ምርጫው የህዝብ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ የተረጋገጠበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በምርጫ ሂደቱም ምንም አይነት እክል እንዳላጋጠመ ጠቅሰው፤ ህዝቡ እርስ በእርስ የመከባበር ኢትዮጵያዊ ባህሉን ያሳየበት ታሪካዊ እለት ነው ብለዋል።

በመስቃን እና ማረቆ ምርጫ ቁጥር 1 የክልል ምክር ቤት እጩ ተዋዳዳሪ የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፤7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ካለፉት የምርጫ ሂደቶች ልምድ በመውሰድ ብዙ የተሻሻሉ ስርዓቶች የተከወኑበት እንዲሁም በምርጫ ሂደቱ የህዝብ ሚና ጎልቶ የተንፀባረቀበት መሆኑን ገልፀዋል።

የምርጫ ሂደቱ ግልፅ በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ የገለፁት ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ውጤቱንም በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

(ደሬቴድ)

ኢትዮጵያ መርጣለች፣ ጸንታለች፣ አሸንፋለች
02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች፣ ጸንታለች፣ አሸንፋለች

ኢትዮጵያ መርጣለች!  voted!
02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!
voted!

02/06/2026
ዋጋ የከፈለውና የመረጠው ታላቁ ሕዝባችን፦• ሁኔታዎች ያልገደቡት፦ የአካል ጉዳት ድምፅ ከመስጠት ያላገደው።• ተስፋ የሰነቀው፦ ሕመም እና እርጅና የሀገርን ብሩህ ተስፋ ከማየት ያልከለከለው።•...
01/06/2026

ዋጋ የከፈለውና የመረጠው ታላቁ ሕዝባችን፦
• ሁኔታዎች ያልገደቡት፦ የአካል ጉዳት ድምፅ ከመስጠት ያላገደው።
• ተስፋ የሰነቀው፦ ሕመም እና እርጅና የሀገርን ብሩህ ተስፋ ከማየት ያልከለከለው።
• ቁርጠኛው፦ የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጁን አዝሎ በጽናት የተሰለፈው።
• የማይበገረው፦ ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆመው።

ይህን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነው! ያከበራችሁን ይህንን ታላቅ ሕዝብ አክብራችሁ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

የሕዝባችን አስደናቂ ጽናት በምርጫው ዕለት፦✅ የተፈጥሮ ፈተናዎችን ያሸነፈ✅ ማኅበራዊ ሁነቶችን የተሻገረ✅ ታጋሽና ቁርጠኛ✅ ሁሉንም ያካተተይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነው! ያከበራችሁን ሕ...
01/06/2026

የሕዝባችን አስደናቂ ጽናት በምርጫው ዕለት፦
✅ የተፈጥሮ ፈተናዎችን ያሸነፈ
✅ ማኅበራዊ ሁነቶችን የተሻገረ
✅ ታጋሽና ቁርጠኛ
✅ ሁሉንም ያካተተ

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነው! ያከበራችሁን ሕዝብ አክብራችሁ፣ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ማኅበረሰብ በንጽሕና አገልግሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ውጣ ውረዶችን አሸንፎ ታሪክ ለሠራው የኢትዮጵያ ሕዝብ" ልባዊ ክብርና ምስጋና አቀረቡ****************...
01/06/2026

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
"ውጣ ውረዶችን አሸንፎ ታሪክ ለሠራው የኢትዮጵያ ሕዝብ" ልባዊ ክብርና ምስጋና አቀረቡ
*************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ታሪካዊ የምርጫ ዕለት ጽናቱን ላሳየውና ተአምር ለሠራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ "የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው፤ ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው?" ካሉ በኋላ፣ ሕዝቡ የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም ማሳየቱን ገልጸዋል።

በዛሬው ታሪካዊ ዕለት የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣ የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው፣ እንዲሁም ሠርግ፣ ኀዘንና ወሊድን የመሰሉ ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው ዜጎች በነቂስ ወጥተው መምረጣቸውን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣ የአካል ጉዳት፣ ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከመመልከት ያላገዳቸው፣ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸውና ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳዩት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ በመሆኑ ከልብ የመነጨ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል ትልቅ መታደል መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተመራጮች ያከበራቸውን ሕዝብ መልሰው እንዲያከብሩና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል እንዲበቁ ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)**************ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**************

ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል።

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የድምፅ መስጫ ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ተራዘመ ***************************የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12:00 ሰ...
01/06/2026

የድምፅ መስጫ ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ተራዘመ
***************************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) በተደነገገው መሠረት፤ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ተብሎ በመታመኑ የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተመዘገቡ መራጮች መርጠው በተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

#የኢትዮጵያምርጫ #ምርጫ2018 #የምርጫቦርድ #ኢትዮጵያ

Address

ምስራቅ ጉራጌ ዞን/መስቃን ወረዳ/ቡታጅራ
Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት:

Share