የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication This is The official Butajira City Gov't COMM.fb page-ይህ ትክክለኛው የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን (fb)ፔጅ ነው፦
(1)

የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ወደ ምርጫ ጣቢያ ይዞ መግባት እንደማይቻል ያውቃሉ? ******************7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ታዲያ በምርጫ ወቅት ...
23/05/2026

የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ወደ ምርጫ ጣቢያ ይዞ መግባት እንደማይቻል ያውቃሉ?
******************

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ታዲያ በምርጫ ወቅት ወደ ምርጫ ጣቢያ ምን ነገሮችን ይዞ መግባት እንደሚቻል ያውቃሉ?

1. ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሑፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም።

2. ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤና ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም።

3. የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት ይኖርበታል።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ግንቦት24

23/05/2026

የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች የምርጫ ዝግጅት

ድምፅ ለመስጠት ….1. ድምፅ ለመስጠት ወደተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ ፡- ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድዎን ይያዙ ፣ ለ) የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም በመራጮች ምዝገባ ወ...
23/05/2026

ድምፅ ለመስጠት ….

1. ድምፅ ለመስጠት ወደተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ ፡-

ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድዎን ይያዙ ፣

ለ) የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተረጋገጠ ሌላ ሰነድ ፣ ወይም ማንነትዎ በምርጫ ምዝገባ ወቅት በምስክሮች ስለመረጋገጡ በመራጮች መዝገብ ላይ የሰፈረ መሆኑ፣

ሐ) የመራጮች መዝገብ ላይ ስምዎ መስፈሩ ይረጋገጣል፤

መ) ድምፅ ያልሰጡ መሆንዎ ሲረጋገጥ ድምጽዎን የመስጠት መብት አለዎት።

2. የመራጮች የምዝገባ መታወቂያ የጠፋብዎ ከሆነ ለምርጫ ጣቢያው በማስረዳት በመዝገቡ ላይ ስምዎ የሰፈረና ያልመረጡ መሆኑ ተረጋግጦ ጉዳዩ በቃለ ጉባኤ ተይዞ እንዲመርጡ ይደረጋል።

በቡታጅራ ከተማ የትምህርት ብርሃን በተሰኘው የፈተና ስርዓት መሠረት 1031 ጎልማሶች ተመዘኑ(ግንቦት 15/2018) በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር  የትምህርት ብርሃን በተሰኘ...
23/05/2026

በቡታጅራ ከተማ የትምህርት ብርሃን በተሰኘው የፈተና ስርዓት መሠረት 1031 ጎልማሶች ተመዘኑ

(ግንቦት 15/2018) በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ብርሃን በተሰኘው የፈተና ስርዓት ሲከታተሉ የቆዩ 1031 ጎልማሶችና ወጣቶች ምዘናቸውን ወስደዋል።

ትምህርት ሚኒስትር በሃገሪቱ የማይምነት ቁጥርን ለመቀነስ በማለም ትምህርት የመማሪያ እድሜያቸው በተለያየ ሁኔታ የገፋ ሰዎች “ሀገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን” በተሰኘ የፈተና ስርዓት የሚያልፉበት ሁኔታ ማመቻቸቱ የሚታወስ ነው።

ስርዓቱ ከ3ኛ ክፍል ማጠናቀቅ ጋር አቻ እንደሆነ እና ፈተናውን ያለፉ በተግባር ተኮር ትምህርት እንዲቀጥሉ የሚያስችል ነው።

በዛሬው ዕለትም የቡታጅራ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በትምህርት ቤቶችና ማዕከላት (17 በሚሆኑ) ለጎልማሶች የሰጠው ፈተና የትምህርት ብርሃን” በተሰኘው የፈተና ስርአት መሠረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ ስርአቱ ከ3ኛ ክፍል ማጠናቀቅ ጋር አቻ እንደሆነ እና ፈተናውን ያለፉ በተግባር ተኮር ትምህርት እንዲቀጥሉ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል።

የተግባር ተኮር ትምህርቱ ግብርና፣ ጤና እና ቴክኖሎጂን እንደሚያካትት ጠቁመዋል።

በጤና፣ የንፅህና አጠባበቅ፣ የምግብ ዝግጅት፣ የህፃናት አያያዝ እና ሌሎች ጉዳዮችንም በሚዘጋጅ መመሪያ ከሳይንስ አኳያ ትምህርት እንዲወስዱ መደረጉንም አቶ አብዶ ገልፀዋል።

ወጣቶችና ጎልማሶች በሁሉም ሂደት በንቃት በመከታተል ከማንበብና መፃፍ በተጨማሪ የሙያ የእውቀትና ክህሎታቸው እንዲጎለብት የተዘረጋው እድል ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

ምርጫና የዜጎች መብቶች…..ይህ መብት የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 38(1)(ሀ) ስር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ልዩነት በቀጥታና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በህዝብ ጉ...
23/05/2026

ምርጫና የዜጎች መብቶች…..

ይህ መብት የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 38(1)(ሀ) ስር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ልዩነት በቀጥታና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በህዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ› መብት አለው በማለት በደገገው መብት ውስጥ የሚታቀፍ ነው፡፡

በሌላ አነጋገር ህዝቡ በመረጣቸው እንደራሴዎች አማካኝነት እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት መብት ነው ይህ መብት፡፡

ስለዚህ ዜጎች ምርጫ በአንድ ወይ በሌላ መልኩ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በነቂስ ወጥተው ድምጽ መስጠት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛና ተዓማኒ ምርጫ እንዲካሄድ ኃላፊነታቸውንም መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የሀገሪቱ ዜጎች በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሂደት ያሏቸውን ተጨማሪ መብቶች በአንቀጽ 38 በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በዚሁ መሠረት የመጀመርያውና ዋነኛው መብት የመምረጥና የመመረጥ መብትን አፈጻጸም በተመለከተ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጾታ፣በቋንቋ፣ በኃይማኖት፣በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት አይደረግበትም የሚለው ነው፡፡

ይህ መብት አንድ ኢትዮጵያዊ በማናቸውም የሀገሪቱ ክፍሎች ልዩነት ሳይደረግበት የመምረጥና የመመረጥ መብት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የተረጋገጠው የምመረጥና የመመረጥ መብት አንድ መራጭ የሚመርጠውን ፓርቲ ወይም እጩ በምስጢር የመምረጥ መብት ያለው መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ይህ መብት በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ (እና በመንግሥት) ላይ በተጓዳኝነት መራጩ ድምጽ በሚስጥር ለመስጠት የሚያስችለውን አካባቢያዊና ቴክኒካዊ ሁኔታ የማሟላት ግዴታ ይጥላል፡፡

እርስዎ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተዘጋጅተዋል! በመምረጥ ሀገርዎን ያሻግሩ!

ሴት ልጅን የደፈረ ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣተከሳሽ መቻል ምስጋናው በቀን 18/05/2018 ከቀኑ በግምት 3:30 በማሆንበት ጊዜ በቡታጅራ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማረሚያ ጀርባ ተብሎ በ...
22/05/2026

ሴት ልጅን የደፈረ ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ መቻል ምስጋናው በቀን 18/05/2018 ከቀኑ በግምት 3:30 በማሆንበት ጊዜ በቡታጅራ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ማረሚያ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባትን ዕድሜዋ 17 ዓመት የሆናትን የግል ተበዳይ ወደ ቤት እየሄደች እያለ እኔ እወስድሻለው በማለት አታሎ ወደ ጫካ ውስጥ በመውሰድ እጇን ጎትቶ እራሷን እንዳትከላከል በማድረግ አስገድዶ የደፈራት መሆኑን ተከሳሽ አስቦ በፈፀመው ወንጀል ተከሷል።

የቡታጅራ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዐ/ህግ የወ/ሕ አንቀጽ 620(2(ሐ) ጠቅሶ ባቀረበው ክስ በሚሰማበት ቀንም ተከሳሽ ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ዐ/ህግ ምስክሮችን አሰምቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ዐ/ህግ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዳ በመሆኑ ይከላከላል ሲል ብይን ሰጥቷል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በቀን 14/09/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በተከሰሰበት በወ/ህ/አ 620(2(ሐ) ስር ጥፋተኛ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከግምት በማስገባት ተከሳሽ 10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እንዳቀጣ ወስኗል።

ሕብረተሰቡ ከዚህ ቅጣት መማር ያለበት በተከሳሽ በተጣለው ቅጣት እንዲማር እና በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ያለውን የሴት ልጅ ጥቃት እንዲከላከል ፣ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉን ሴቶች እርዳታን ማድረግ፣የልጅቱን አዋዋል እንዲቆጣጠር ፣ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ችግርም ሲገጥም ለሚመለከተው የህግ አካል በማሳወቅ ወንጀለኞችን እንዲያጋልጥና አሳልፎ በመስጠት ለፍትህ እንዲተባበር እየጠየቅን ወንጀልን በጋራ እንከላከል እያልን እናሳስባለን።

የበዓል ገበያ ድባብ በቡታጅራ ከተማበምስራቅ ጉራጌ ዞን መዲና በቡታጅራ ከተማ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የበዓል ገበያ ድባብየ1447ኛው ዓ.ሒ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-...
22/05/2026

የበዓል ገበያ ድባብ በቡታጅራ ከተማ

በምስራቅ ጉራጌ ዞን መዲና በቡታጅራ ከተማ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የበዓል ገበያ ድባብ

የ1447ኛው ዓ.ሒ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል ለዚህም በቡታጅራ ከተማ አርብ ገበያ የበዓል ገበያ በደማቅ ሁኔታ እየተከናወነ ነው።

በትልቅነቱና በበቂ የግብአት አቅርቦቱ የሚታወቀው አርብ ገበያ ለበዓሉ የእርድ እንስሳት እና ሌሎች ምርቶች በተለየ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ሽያጭና ግብይት አእያስተናገደ ይገኛል።

ዒድ -ሙባረክ !!
መልካም በዓል!!

በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ በጸረ ሰላም ኃይሎች ሊደናቀፍ አይችልም :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) (ግንቦት 14/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ...
22/05/2026

በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ በጸረ ሰላም ኃይሎች ሊደናቀፍ አይችልም :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

(ግንቦት 14/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በኢንሴኖ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ በጸረ ሰላም ኃይሎች ሊደናቀፍ አይችልም ብለዋል።

የኢንሴኖ ከተማና አካባቢው የተፈጥሮ ጸጋ የተቸረው የታታሪ እና የእንግዳ ተቀባይ ህዝብ ባለቤት ነው ብለዋል።

ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በአካባቢው ባጋጠመ የጸጥታ ችግር ምክንያት ህዝቡን ከልማት ስራው ለመነጠል ጥረት ያደረጉ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እንዲፈታ መንግስት፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች እና መላው ህዝብ የላቀ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

በአካባቢው አሁንም ድረስ አልፎ አልፎ የጸጥታ ችግር እየተስተዋለ ስለመሆኑ በንግግራቸው አስታውቀዋል።

የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

በሰው ደም የሚነግዱ አካላት ለዘመናት አብረው በኖሩ ህዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ሊሳካ እንደማይችል ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የመስቃን ሱሙት ሰንጋ ሊቃ የበላይ ጠባቂ ሼህ ሰይድ ሰልማን ፋሪስ መላውን ህዝብ በማስተባበር በአካባቢው ዘላቂ ሰላም በማስፈን ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል የተጀመረው የልማት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው መላው ህዝብ ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጥ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው በምርታማነት የሚታወቅ የተፈጥሮ ጸጋ ባለቤት ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩ ምርታማ እንዳይሆን ነጋዴው ሰርቶ እንዳያተርፍ እንዲሁም ተማሪው በእውቀት እራሱን እንዳያሻሽል በአካባቢው ጽንፈኛ ኃይል የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት የአካባቢው ሰላም እንዲረጋገጥ የላቀ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

የተጀመረው ልማት እና ሰላም እንዲረጋገጥ በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጥ አቶ ሙስጠፋ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢንሴኖ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሐመድ ኑር ስርሞሎ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ቃሉን የሚኖር ፣ታማኝ እና ብቁ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ተግዳሮቶችን ሁሉ ወደ ድል በመቀየር በሀገሪቱ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆን እየተጋ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተካሔደ መሆኑን ከንቲባው አስረድተዋል።

ለከተማዋ እድገት የክልሉ መንግስት የላቀ ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት አቶ መሐመድ ኑር አብራርተዋል። (የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

የወራቤ  የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ በ132/33 ኪሎ ቮልት አቅም የተገነባው የወራቤ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በተ...
22/05/2026

የወራቤ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

በ132/33 ኪሎ ቮልት አቅም የተገነባው የወራቤ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በተገኙበት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የዚህ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ መገንባት በስልጤ ዞንና በአጎራባች አካባቢዎች ለዓመታት የነበረውን የሃይል እጥረትና የመቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።

የማከፋፈያ ጣቢያውወደ ሥራ መግባቱ በአካባቢው አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር ከማድረጉም በላይ፣ የተቀላጠፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር እና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍ ያለ እገዛ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

በተለይም አነስተኛና ከፍተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ምሰሶ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በሀይል መካፋፈያ ምረቃ ሥነ-ሥርዓትላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።(EBC)

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በኢንሴኖ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው (ግንቦት 14/20...
22/05/2026

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በኢንሴኖ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

(ግንቦት 14/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በኢንሴኖ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ፣የክልል፣የዞን የስራ ኃላፊዎች እና የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ አባላት ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ በሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣የምግብ ሉአላዊነት ተምሳሌት፣በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣ጸጋን ወደ ሀብት፣ብልጽግናን እመርጣለሁ አሻራዬን አኖራለሁ፣ትላንትን ማከም ነገን መተለም እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
(የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

50 ሚሊዮን ድምፆች - በአንድ ጀምበር ታላቁ ሁነት በኢትዮጵያ *****************ኢትዮጵያ በድጋሚ ታሪክ ልትጽፍ ተዘጋጅታለች፤ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በአንድ ጀምበር ወደ ምርጫ...
21/05/2026

50 ሚሊዮን ድምፆች - በአንድ ጀምበር ታላቁ ሁነት በኢትዮጵያ
*****************

ኢትዮጵያ በድጋሚ ታሪክ ልትጽፍ ተዘጋጅታለች፤ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በአንድ ጀምበር ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የሚያመሩበት ታላቅ ሀገራዊ ሁነት እየተቃረበ ነው።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ሂደት ብቻ አይደለም፤ የሕዝብ ተሳትፎ፣ የመንግሥት አቅም፣ የተቋማት ዝግጁነት እና የሀገር አንድነት የሚታይበት የታሪክ አጋጣሚ ነው።

በአፍሪካ ከሚካሄዱ ትልልቅ ምርጫዎች አንዱ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ሁነት፣ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞዋን ወደ አዲስ ደረጃ ለማሸጋገር የምታደርገውን ጉዞ በይበልጥ የሚያፋጥን እደሚሆን እሙን ነው።

50 ሚሊዮን መራጮች ማለት ቁጥር ብቻ አይደለም። ይህ የብዙ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ እምነቶች እና ትውልዶች ድምፅ ሲሆን የዴሞክራሲ እውነተኛ ኃይል በዜጎች ተሳትፎ የሚወሰንበት ይህ ታሪካዊ ቀን ደርሷል።

ምርጫ በተለያዩ ሀገራት ከፖለቲካ ልዩነት በላይ ሀገራዊ መግባባትን የፈጠረ፣ የሲቪክ ተሳትፎን በማዳበር የዴሞክራሲ ባህሎችን ያዳበረ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቁንጮ እሴት ነው። ይህ ልምምድ በኢትዮጵያም የዴሞክራሲያዊነት ዋንኛ መመዘኛ ሆኖ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት እየታየ ነው።

አሁን ላይ አፍሪካ በፍጥነት እየተቀየረች ነው፤ ወጣት ኃይል፣ የከተማ ዕድገት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስፋት እና የፖለቲካ ንቃተ ኅሊና አህጉሪቱን ወደ አዲስ ዘመን እየወሰዷት ነው።

በዚህ ለውጥ ውስጥ ኢትዮጵያ ያላት ቦታ ትልቅ ነው፤ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ጥንታዊ ታሪክ፣ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከልነት እና እያደገ ያለ የኢኮኖሚ አቅም ያላት ሀገር እንደመሆኗ፣ የምርጫ ሂደቷ በመላው አህጉር በትኩረት ይታያል።

50 ሚሊዮን መራጮች፣ አንድ ሀገር፣ አንድ ታሪካዊ አጋጣሚ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ። የታላላቅ ሀገራት ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ዴሞክራሲ በአንድ ቀን አይገነባም፤ በተሳትፎ፣ በመማር እና በቀጣይነት እንጂ።

ምናልባትም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የዴሞክራሲ ታሪክ የሚያበራ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችል መሆኑ በብዙዎች ታምኖበታል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication:

Share