SWER Prosperity party women Wing የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bonga
  • SWER Prosperity party women Wing የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ

SWER Prosperity party women Wing  የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ This page reflects the activities and views promoted by women members of the Prosperity Party.

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በህዝቦች መካከል የነበረውን አብሮነት ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ...
24/10/2025

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በህዝቦች መካከል የነበረውን አብሮነት ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ሀሳብ ወሰን ተሻጋር በጎ ፍቃድ አገልግሎት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተገኝተው አከናወኑ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ በሁለቱ ክልሎች መካከል የሚደረገው የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ስራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክር ታላቅ የበጎነት ስራ መሆኑን ተገልጿል።

ኃላፊዋ አክለው እንደገለጹት ለተቸገሩ ወገኖቻችን የምንረዳበትና የምናግዝበት ተገባር ከመሆኑ ባሻገር ህብረ ብሄራዊነታችንን የሚያጎለብት፣ የህዝባችንን የስነልቦና አንድነት የሚያጠናክርና የሁለቱን ክልል እህትማማችነት የሚያጠናክር ተግባር ነው ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ በ14 መስኮች በሚከናወነው የክረምት ወራት በጎ ተግባር ላይ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ በማድረግ በቅንጅት ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር የሚያግዝ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከብልጽግና ፓርቲ እሴቶች አንዱ የሆነውን በህዝቦች መካከል መቀራረብን እና መተጋገዝን የማጠናከር መልካም ተግባርን በማስቀጠል እሴቶችና ብዝሃ ሃብቶች አልምተን በመጠቀም ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።

በሴቶች ክንፍ መሪነት በክረምት ወራት የተለያዩ በጎ ተግባራት ለማከናወን ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ ይታወቃል በዚህም በርካታ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ዲሞክራሲና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስዩም ደጉ እንኳን ወደ ኢትዮጵያዊቷ የሰፊ የስንዴ ምርት ባለቤት ወደሆነች የማዕከላዊ ክልል ሀዲያ ዞን በሠላም መጣችሁ በማለት ይህ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ጉዞ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት በማጠናከር አብሮነት እንዲፀና የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የከንባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፀጋነሽ ደመቀ ይህ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሁለቱም ክልሎች መካከል ያለውን አብሮነት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ አቅመ ደካሞችን ስንደግፍ ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን የሚያሳይ ነው በማለት ገልጸዋል።

በጉዟቸው መረሐ ግብር በክልሉ ከከተማው ለተወጣጡ አቅመ ደካማ ወገኖች የተለያዩ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎንም የሀዲያ ዞን በሴቶች የተከናዘነ የሌማት ትሩፋት ስራ ጉብኝት አድርገዋል።

የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክልላችን ላሉ 100 የመንግስት ሰራተኛ ሴቶች ነጻ የት/ት እድል ተሠጥቷል ❤
23/10/2025

የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክልላችን ላሉ 100 የመንግስት ሰራተኛ ሴቶች ነጻ የት/ት እድል ተሠጥቷል ❤

አንድ መቶ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነጻ የሀገር ዉስጥ የትምህርት ዕድል ለሴቶች መመቻቸቱን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል ።

የክልሉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢ.ፈ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ6ቱም ዞኖች የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሀገር ዉስጥ ነፃ የትምህርት ዕድል ለሴቶች አመቻችቷል።

በክልሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራሄል ሌዊ የክልሉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢ.ፈ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የትምህርት ዕድሉ ለክልሉ በሁለተኛ ዲግሪ 75 በሶስተኛ ዲግሪ 25 በድምሩ 100 ሴቶችን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል ።

አመልካቾች ለ6ቱም ዞኖች በተሰጠዉ ኮታ መሠረት መረጃቸውን በየዞናቸው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በኩል በማቅረብ ማመልከት እንደሚችሉም ወ/ሮ ራሄል ገልጸዋል ።

የኢ.ፈ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ጥረት እያደረገ መሆኑንም ወ/ሮ ራሄል ተናግረዋል ።

በተመቻቸው የትምህርት ዕድል በሁለተኛ ዲግሪ ካፋ 27፣ዳውሮ 15፣ቤንች ሸኮ 14፣ሸካ 6፣ምዕራብ ኦሞ 5 እና ኮንታ 3 የተፈቀደ ሲሆን በሶስተኛ ድግሪ መርሃ ግብር ካፋ 7፣ዳውሮ 5፣ቤንች ሸኮ 4፣ሸካ 2፣ምዕራብ ኦሞ 2 ኮንታ 1 ኮታ መሰጠቱን ወ/ሮ ራሄል ለቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በአቅም ግንባታ ስራዎችን በእውቀትና በትጋት  የሚመሩ ሴት መሪዎችን በማብቃት ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ።በደቡብ ምእራብ ኢ/ያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ሴቶች ክንፍ...
21/10/2025

በአቅም ግንባታ ስራዎችን በእውቀትና በትጋት የሚመሩ ሴት መሪዎችን በማብቃት ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ።

በደቡብ ምእራብ ኢ/ያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት በሚዛን ክላስተር የህብረትና የቤተሰብ አመራሮችን በማሰልጠን አቅማቸውን የመገንባት ስራ ተሠርቷል።
በክንፉ አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉ ሦስት የአሰራር መመሪያዎች በስልጠናው የቀረቡ ሲሆን ሰልጣኞችም አደረጃጀቶችን ለመምራት የሚጠቅም እውቀት እንዳገኙ በአስተያየታቸው አስቀምጠዋል።
ሰብለፀጋ አየለ

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አደረጃጀት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለመጨመርና በብልጽግ እና ፓርቲው ያስቀመጠዉን ግብ ለማስፈፀም የአቅም ግንባ...
16/10/2025

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አደረጃጀት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለመጨመርና በብልጽግ እና ፓርቲው ያስቀመጠዉን ግብ ለማስፈፀም የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ ነዉ።
በዛሬዉ ዕለትም በደ/ም/ ኢ/ህ/ክ/ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ለቦንጋ ማዕከል ሴት መንግስት ሰራተኞ ህብረትና ቤተሰብ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ''የሴቶች ክንፍ አደረጃጃትና አሰራር መመሪያ ግንባር ቀደም አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ወሳኝ ነው'' የሚል አላማ ይዞ በወ/ሮ ውባለም በዛብህ የክልሉ ብ/ፓ/ ሴ/ክ/ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ተሰጥቷል።
https://www.facebook.com/profile.php?id=61574976748042&mibextid=ZbWKwL

የሴቶች ክንፍ የአደረጃጀት ተልዕኮና አሰራር መመሪያ ላይ ለክንፍ አመራሮች ሰልጠና ተሰጠ። ጊምቦ፣ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም (ዑፋ)የጊምቦ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ...
11/10/2025

የሴቶች ክንፍ የአደረጃጀት ተልዕኮና አሰራር መመሪያ ላይ ለክንፍ አመራሮች ሰልጠና ተሰጠ።

ጊምቦ፣ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም (ዑፋ)
የጊምቦ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም ተግባር አፈጻጸምና የ2018 ዓ.ም ጠቋሚ እቅድ ላይ ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ነው የሴቶች ክንፍ የአደረጃጀት ተልዕኮና አሰራር መመሪያ ላይ ለክንፍ አመራሮች ሰልጠና የተሰጠው።

በአደረጃጀት ስራዎች ግንባር ቀደምና ተተኪ ሴቶቶችን መመልመልና ማደራጀት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ አባይነሽ አምበሰ ሁሉም ሴቶች ሀገራዊ ሁኔታን የተረዱ እና ለሀገራቸው ከፊት የሚቆሙ እንዲሁም የብልፅግና ጉዞን ማረጋገጥ የሚችል አባል መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ አብራርተዋል።

በተጨማሪ የጊምቦ ወረዳ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አባይነሽ አምበሰ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም የሴቶች ክንፍ አደረጃጀት ማጠናከር ዙሪያ ለክንፍ አመራርና አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች የሴቶችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በየቀበሌው ያሉ የሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶች የራሳቸውን ሚና መወጣት ይኖርባቸዋልም ብለዋል።

በየሩብ አመቱ ኮንፈረንስ እንደሚኖር የጠቆሙት ወ/ሮ አባይነሽ የብልጽግና ህብረትና ቤተሰብ በጊዜ ሰሌዳ ውይይት በማድረግ አደረጃጀቱን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

በብርሃነ አባተ

ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
የጊምቦ ወረዳ መን/ኮሚ/ጉዳ/ጽ/ቤት

‎የበጎነት እሴት ከቁስ ተሻጋሪ ባሻገር የህዝብ ለህዝብና የአብሮነትን ትስስር የሚያጠናክር ነው፦  ፍሬው ሞገስ (ዶ/ር) ‎‎የበጎነት እሴት ቁስ ተሻጋሪ ባሻገር የህዝብ ለህዝብና የአብሮነት ት...
05/10/2025

‎የበጎነት እሴት ከቁስ ተሻጋሪ ባሻገር የህዝብ ለህዝብና የአብሮነትን ትስስር የሚያጠናክር ነው፦ ፍሬው ሞገስ (ዶ/ር)

‎የበጎነት እሴት ቁስ ተሻጋሪ ባሻገር የህዝብ ለህዝብና የአብሮነት ትስስር የሚያጠናክር ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ፍሬው ሞገስ ዶ/ር) ገለጹ።

‎በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል መሪ ሀሳብ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ልዑካን በወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ተግባር ለማካሄድ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።

‎በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ፍሬው ሞገስ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያን አንድ ስንሆን ፣ስንተባበርና ስንተጋገዝ ታላቅ ታሪካዊ ገድል የፈጸምንበት የህዳሴ ግድብ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎በመረዳዳት ፣በመተጋገዝ እርስ በርስ በመተሳሰብ ያሉትን ችግሮችን በጋራ በመቅረፍ የበጎነት እሴቶችን አጠናኮሮ ማስቀጠል የዘውትር ተግባር ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ የወስን ተሻጋሪ የደቡብ ኢትዮጵያ ሴቶች ክንፍ ላደረገው የበጎ ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

‎በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ማከናወን መቻሉን የገለጹት ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ በዚህም የአረጋዊያንና አቅመደካሞችን ቤት በመገንባት፣ በማደስ ፣የተቸገሩ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

‎የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንድነትን የሚያጠናክርና የእርስ በርስ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጎለብት ፣የወንድማማችነትና አህትማማችን አብሮነት እሴቶችን በማጠናከር ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ማህበራዊ ፍትህ ለማረጋገጥና በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን በመከወን የበርካታ የአቅመ ደካማ፣ የአረጋዊያንን እና የተቸገሩ ወገኖችን እምባ በማበስ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

‎በጎ ፍቃድ አገልግሎት ድንበር የለውም ያሉት ኃላፊዋ የአብሮነት ትስስርን በማጠናከር የእርስ በርስ ማህበራዊ መስተጋብር ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዎጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

‎የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያብ ቶማስ
‎የፓርቲያችን ኢኒሼቲብ የሆነው የበጎነት እሴት ወንድማማችነት /እህትማማችነት እሴቶችን ከማጠናከር ባሻገር በተጨማሪ የዜጎች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ኑሮን ለማቅለል ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክልል
የብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያ

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ
02/10/2025

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ

02/10/2025

የሸከቾ ህዝብ ዘመን መለወጫ በአል በሸካ ዞን ጌጫ ከተማ በድምቀት ተከበረ

እንኳን ለሸካቾ ህዝብ የዘመን መሀወጫ መሽቀሮ በአል በሰላም አደረሳችሁ!
30/09/2025

እንኳን ለሸካቾ ህዝብ የዘመን መሀወጫ መሽቀሮ በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ሴቶችን ለማሳተፍና ለማብቃት የሚደረግ ድጋፍ ቤተሰብን ብሎም ማህበረሰብን ማብቃት ነውና በቦንጋ ከተማ አስተዳደር የተደረገው ድጋፍ በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣ ነው! በርቱ...
30/09/2025

ሴቶችን ለማሳተፍና ለማብቃት የሚደረግ ድጋፍ ቤተሰብን ብሎም ማህበረሰብን ማብቃት ነውና በቦንጋ ከተማ አስተዳደር የተደረገው ድጋፍ በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣ ነው! በርቱልን ቦንጋዎች

27/09/2025

የመስቀል በዓሉን ስናከብር የተደመረ አቅማችንን በመጠቀም ተጋግዘንና ተባብረን በፍቅር የመኖር ባህላችንን ለማጽናት ከምን ጊዜውም በላይ የበረታን ሆነን መገኘት አለብን ፦ አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለደመራ እና ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ።

በመልዕክታቸው፣ “መስቀል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆችን ሁሉ ያለምንም ልዩነት በመሰቀል እስከ መሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ የሰጠበት የፍቅር መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል።

የመስቀሉ ፍቅር የሰዉ ልጅና አምላኩን ያራራቀ ግንብ አፍርሶ አንድ ያደረገ የሰላምና የፍቅር ምልክት በመሆኑ ብርሃነ መስቀሉን በምናከብርበት ወቅት በመስቀሉ የተገለጸውን የሰው ልጅ የማዳን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና የተከፈለውን ዋጋ በማሰብ አንዳችን ከአንዳችን ጋር በመተሳሰብና በፍቅር ልናከብር እና ልንኖር ይገባል ብለዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የማስታረቅን ሂደት በመስቀል ላይ ሆኖ ሲያከናውን ለበደሉት ይቅርታን በማድረግ ይቅርባይ እንድንሆን ማስተማሩን የገለጹት አቶ ፍቅሬ "ዛሬም ብረሃነ መስቀሉን ስናከብር በዉስጣችን አንዳች ቂምና በቀል ይዘን ሳይሆን በይቅርታ ልብ ሆነን ልናከብር ይገባል ብለዋል።

የመሰቀል ደመራ በዓል ከኃይማኖታዊ ትውፊት ባሻገር ህብረብሔራዊ አንድነትን በማነፅ አይተኬ ሚና መኖሩን የገለጹት ኃላፊው ኢትዮጵያውያን ያላቸዉን የእርስ-በርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩበት፣ የተራራቁ ቤተሰቦችን፣ ወዳጅ ዘመዶችን የሚያቀራርብ ፣ የይቅርታንና የመተባበር መንፈስን የሚያጎለብት ታላቅ ኃይማኖታዊ እሴት መሆኑን አንስተዋል።

በዩኒስኮ በቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በህብረብሔራዊነት ደምቀን በፍቅር ከመሰባሰባችን ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስርን በመፍጠር የብልጽግና ተምሳሌታዊ ጉዞን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በህብረት ስንቆም ፣ ስንተባበርና ስንተጋገዝ መስራትና ማሸነፍ እንደሚቻል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፣የአረንጓዴ አሻራና ሌሎች ሀገራዊ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ማሳያዎች ናቸው ያሉት አቶ ፍቅሬ የሰላም ዕሴትን በማስረጽ የተደመረ ዓቅማችንን ተጠቅመን የሀገራዊ ልዕልና ግንባታን በማሳለጥ ሁለንተናዊ የብልጽግና ከፍታችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችንና የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅ ፣በመርዳት፣በመንከባከብ ሊሆን ይገባል በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ!🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
26/09/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ!🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Address

Ethiopia South West Ethiopia Region Bonga City
Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SWER Prosperity party women Wing የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share