Southwest Communications

Call Contact the organization
ሀገር የህዝቦቿ የተዳመረ የጋራ ውቅር ቤታቸው ናት! በዘመናት መንገድ በትውልድ ቅብብሎሽ እየተገነባች እያደገች እና እየበለጸገች የምትጓዘው በተገነባ የጋራ ዕራይ እና በተጋመደ የአስተሳሰብ አ...
07/10/2026

ሀገር የህዝቦቿ የተዳመረ የጋራ ውቅር ቤታቸው ናት! በዘመናት መንገድ በትውልድ ቅብብሎሽ እየተገነባች እያደገች እና እየበለጸገች የምትጓዘው በተገነባ የጋራ ዕራይ እና በተጋመደ የአስተሳሰብ አንድነት ነው። አቶ ፍቅሬ አማን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰመስተዳድር

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው7ው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል ...
07/10/2026

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው

7ው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የምክር ቤት አባልና የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ከተማ በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ አጭር ማብራሪያ አቅርበዋል።

በቀረበው ማብራሪያም ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።

እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ቀድሞ "የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቀድሞ "የፕላንና ልማት ሚኒስቴር" የነበረው "የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" የነበረው "የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" በሚል ስያሜያቸው መቀየሩ ተገልጿል።

በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም መሆኑም ተብራርቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እያቀረቡ እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደ አዲስ በተቋቋሙት ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶችም ሆነ የስያሜ ለውጥ በተደረገባቸው ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ዙሪያ በቀጣይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

#የመደመርመንግሥት

07/10/2026

ኢትዮጵያን አልቻሏትም አይችሏትም

ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር፦ የካይሮ የማግለያ ሴራ እና የኢትዮጵያ ቁርጠኝነት በዓባይ ወንዝ ላይ ፍጹማዊ የብቸኝነት መብት ይገባኛል የምትለው ግብፅ በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ተቸንክራ፣  ለዓባይ ...
06/10/2026

ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር፦ የካይሮ የማግለያ ሴራ እና የኢትዮጵያ ቁርጠኝነት

በዓባይ ወንዝ ላይ ፍጹማዊ የብቸኝነት መብት ይገባኛል የምትለው ግብፅ በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ተቸንክራ፣ ለዓባይ ውኃ ስትል ኢትዮጵያን ማዳከም የሚለውን ግቧን ከቀጥታ ጦርነት እስከ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አማፅያንን ማደራጀት እና መደገፍ ቀጥላለች።

በእነዚህ ሁሉ የዓመታት የሴራ እና የማዳከም እንቅስቃሴዋ ኢትዮጵያን ከልማት እና ዕድገቷ መግታት ያልቻለችው ግብፅ፣ ዛሬም አማራጭ ያለችውን ሁሉ ከመጠቀም ግን አልቦዘነችም።

ሲደላት እና ጉዳይ ሲኖራት አፍሪካዊት፣ ሲከፋት እና ሴራ ስትሻ ዓረባዊት መሆንን የተካነችበት ግብፅ፣ በዓባይ ወንዝ ላይ የበቀለው ሕዳሴ ግድብ ተመርቆ እስኪረታት ድረስም ሆነ ዛሬ የዓባይ ወንዝን የዓረብ ብቸኛ ጉዳይ እያደረገችው ስትከስ ኖራለች። ዳሩ ግን ኢትዮጵያውያን በተፈጥሮ ሀብታቸው ለመልማት የማንንም ፈቃድ አይሹምና ሲጫኗቸው የበለጠ እንደሚስማር እየጠበቁ ሕዳሴን ዕውን አደረጉት።

ይሁንና ግብፅ ዛሬም እውነቱን መቀበል አትሻምና በዓባይ ላይ የተሸነፈችበትን እውነት ተቀብሎ ለቀጣናዊ ትብብር ከመሥራት ይልቅ፣ ቀጣናዊ ትብብር በሚል የዳቦ ስም ኢትዮጵያን ወደ ቀይ ባሕር እንዳትወጣ ያግዘኛል ያለችውን ሁሉ እያደረገች ነው። ከሰሞኑ ያደረገችውም የዚሁ ቅጥያ ነው።

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ በግብፅ ኒው ኤል-ዓላሜይን ከተማ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት መካከል የሱዳን፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎችን ሰብስባ በቀጣናዊ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ መከርን፣ የጋራ መግባባት ላይ ደረስን ብላ ያስወጣችው መግለጫ የካይሮን ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል።

በቅድሚያ ነገር በቀጣናው ሰላም እና ትብብር አዋኪ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን የምታራምደው ግብፅ፣ ቀጣናዊ ትብብር እና በጋራ ማደግን እንዲሁም ለመልካም ጉርብትና ቅድሚያ የሚሰጠውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አሸንፋለሁ በሚል ከንቱ ቅዠት ስለምትደክም እንጂ፣ ቀጣናዊ ትብብር የሚለው የካይሮ ስልት ከአንገት በላይ ባይሆን ኖሮ ትክክለኛ አጋሯ ኢትዮጵያ በሆነች ነበር።

ዳሩ ግን ሻዕቢያን በፍላጎቷ መልክ ቀርፃ እና የገንጣይነት ተልዕኮ ሰጥታ ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር በጊዜያዊነት የነጠለችው ግብፅ፣ ከሦስቱ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት መሪዎች ጋር ተሰበሰብኩ፣ የጋራ አቋማችንም ይኸው ነው ብላ የቀይ ባሕር ጉዳይ የቀይ ባሕር ተዋናዮች ብቸኛ መብት ነው የሚል መግለጫ ስታወጣ ስትታይ፣ የስብሰባውም ሆነ አጠቃላይ የካይሮ ዓላማ ምን እንደሆነ የሚናገረው ብዙ ነው።

ቀይ ባሕር ላይ ብሔራዊ ጥቅም እና ጉዳይ አለን ብለው ያመኑ በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ከድንበራቸው ከ10 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀትን አቋርጠው ቀይ ባሕር ላይ የጦር መንደር ሲገነቡ እና ጦር ሲያሰፍሩ ተንፍሳ የማታውቀው፣ ደግሞም ዓባይ ላይ እውነትን እና የፍትሐዊነት መርሕን በያዘችው ኢትዮጵያ የተሸነፈችው ግብፅ፣ የኢትዮጵያ ቀጣይ መዳረሻ ቀይ ባሕር ነው ብላ ስላመነች ብቻ በሁለትዮሽ፣ በሦስትዮሽ እና በአራትዮሽ በሚሉ ስያሜዎች ከኢትዮጵያ በተቃራኒ መቆሜን ይደግፉልኛል ያለቻቸውን መንግሥታት ነጋ ጠባ እየጠራች በቀጣናው ደኅንነት ላይ መክረን አቋም ያዝን ስትል ራሷን እየሸወደች ትገኛለች። አዎ! የኢትዮጵያ ቀጣዩ መንገድ ግብፅ እንዳለችውም ወደ ቀይ ባሕር ነውና ይህን በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረግ ጉዞ የሚያስቆም ኃይል የለም።

መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በተመሠረተው የመደመር መንግሥት መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ይህንኑ ሐሳብ አፅንኦት በመስጠት፣ ኢትዮጵያ የጠላትን ሴራ በጣጥሳ መሻቷን በተግባር እንደምትከውን አስምረውበታል። በመሆኑም አስተማማኝ የባሕር መግቢያ እና መውጫ እንዲኖራት መንግሥታቸው በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አብስረዋል።

ለሁለቱ የኢፌዴሪ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ንግግር ያደረጉት እና የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ ያብራሩት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሐሳብ በማጠናከር፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉዳይ ማድረግ የቻለችውን የባሕር በር ጥያቄ በጋራ ጥቅም፣ በሰጥቶ በመቀበል እና በሰላማዊ መንገድ ዕውን እንዲሆን ጥረት ይደረጋል ሲሉ ወደ ኋላ ላይመለስ የተነሣ ጥያቄ መሆኑን ለወዳጅ እና ጠላት ቁርጡን አሳውቀዋል።

በመሆኑም በግብፅም ይመራ በሌላ አካል፣ የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄን የሚያደናቅፍ አካል እየተሸነፈ እንደሚሄድ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ እንደልማዷ እያሸነፈች የቀጣናው መሪ ሀገር የመሆን ጉዞዋን ከማሳካት የሚያግዳት ኃይል እንደማይኖር እርግጥ ሆኗል።

#የመደመርመንግሥት

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሰራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ መከሩየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሰራተኞች አዲስ ከተሾሙት የ...
06/10/2026

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሰራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ መከሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሰራተኞች አዲስ ከተሾሙት የቢሮ ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ወ/ሚካኤል ጋር በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የመከሩበት የትውውቅ መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱ ወቅት ሀላፊው እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባትና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በታችኛው መዋቅር የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በቁርጠኝነት፣ ታማኝነትና በተጠያቂነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተጨማሪም ፍትሐዊና ጥራት ያለው አገልግሎት ለማረጋገጥ የበላይ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በመድረኩ የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና አሰራርን ለማዘመን የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸውን ሀላፊው ጠቁመዋል። በዚህም መሰረት የ2018 እና የ2019 አንደኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ተገምግሞ ጠንካራና ደካማ ጎኖች የሚለዩ ሲሆን፤ የጤና ግንባታ ፕሮጀክቶችም ከጊዜ፣ ከጥራትና ከሀብት ቆጣቢነት አኳያ ተገምግመው ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ይደረጋል። ብልሹ አሰራሮችን በመታገል ግልጽነትና ፍትሐዊነትን ለማስፈን፣ ከታችኛው መዋቅር ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የዲጂታል የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን በስፋት ለመተግበር በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የጤናና ጤና ነክ ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ መልካም ስራዎችን ለማስቀጠልና ደካማ ጎኖችን ለማረም ሰራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወሰን ጨመሳ ባለፉት ዓመታት ከአጋሮች ጋር በመሆን ህብረተሰቡን ከወባ ወረርሽኝ መታደግ መቻሉን አውስተው፣ በቀጣይም ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ከቢሮው ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/
📌በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
📌በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
📌በትሬድስ
https://www.threads.com/
📌በብሉ ስካይ
https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social
በደብልው ኤን ሶሻል
https://wnsocial.com/page/16775

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን  ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን  ለጠቅላይ ሚኒስትር ...
06/10/2026

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሀገራቸው መንግስት እና ህዝብ ስም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎች ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

ይህ አዲስ የሥራ ዘመን ኃላፊነት ሕዝቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር እና ለኢትዮጵያ ዕድገት ባላቸው ራዕይ ላይ ያለውን ትልቅ እምነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ እና ጥልቅ የወንድማማችነት ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ገልጸው፤ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች፣ የአገራቱ ብልጽግና እና የአፍሪካን አጠቃላይ እድገት መሰረት ባደረገ መልኩ ይህን ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/
📌በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
📌በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
📌በትሬድስ
https://www.threads.com/
📌በብሉ ስካይ
https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social
በደብልው ኤን ሶሻል
https://wnsocial.com/page/16775

ቀይ ባሕር የጋራ ካልሆነ ዓባይ እንዴት የጋራ ሊሆን ይችላል?ኢትዮጵያ ዝም ማለትን ከድክመት ጋር አላምታታችም። ብሔራዊ ጥቅሟ ሲፈተን፣ በግልጽና በፍጥነት ትመልሳለች።በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥ...
06/10/2026

ቀይ ባሕር የጋራ ካልሆነ ዓባይ እንዴት የጋራ ሊሆን ይችላል?

ኢትዮጵያ ዝም ማለትን ከድክመት ጋር አላምታታችም። ብሔራዊ ጥቅሟ ሲፈተን፣ በግልጽና በፍጥነት ትመልሳለች።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪካዊ ጠላቶቿን ተልዕኮ በተሸከሙ ዲፕሎማቶች ላይ ቆራጥ ርምጃ ወስዷል። ይህ ርምጃ፣ ድንገተኛ ውሳኔ አልነበረም። ለዘመናት የተከማቸ ትዕግስት ካለቀ በኋላ፣ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የተወሰደ አስፈላጊ ርምጃ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን ግልጽ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነትን፣ የጋራ መከባበርንና ቀጣናዊ ትብብርን ታከብራለች ነገር ግን በሉዓላዊነቷ፣ በግዛት አንድነቷና በመሰረታዊ ብሔራዊ ጥቅሞቿ ፈጽሞ አትደራደርም።

የባሕር በርን የማግኛ መንገድ በሰጥቶ መቀበል መርሕ መሆኑን ደጋግማ ገልጻለች።ይህ መርሕ በቀይ ባሕር ጉዳይ ላይም በግልጽ ታይቷል።

በሌላ መልኩ ግን የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች፣ "ጠረፍ የማይጋሩ ሀገራት የቀይ ባሕር አካል አይደሉም" የሚል አግላይ መግለጫ አወጡ። የአል-አላሚን መግለጫ ተብሎ የተሰየመው ይህ ሰነድ፣ የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ የሚመለከታቸው የባሕር ጠረፍ ያላቸው ሀገራት ብቻ ናቸው ሲል ደመደመ።

እውነታው ግን ፍጹም የተለየ ነው።

ከቀይ ባሕር 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለምትገኘው ኢትዮጵያ፣ በባሕሩ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም የጸጥታ ስጋት፣ በኢኮኖሚዋ፣ በሎጂስቲክስ እንዲሁም በብሔራዊ ደህንነቷ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።

የታጣቂዎች እንቅስቃሴ፣ የባሕር ላይ ውንብድና፣ የሀያላን ስትራቴጂያዊ ፉክክር ሁሉም ኢትዮጵያን ይነካሉ፣ ድንበር ብቻ ሳይሆን እጣ ፈንታ ይጋራሉና። ከዚህም የሚያስገርመው፣ የመሪዎቹ ራሱን የሚቃረን አቋም ነው።

ቀይ ባሕር የጠረፍ ተጋሪዎቹ ብቻ ነው ካሉ በኋላ፣ ተመሳሳዩ መሪዎች፣ የዓባይ ወንዝ ግን "የጋራ ሀብታችን ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።
ጥያቄው ቀላል ነው፦ ቀይ ባሕር የጋራ ካልሆነ፣ ዓባይ እንዴት የጋራ ሊሆን ይችላል?

ቀይ ባሕርን በጂኦግራፊ የሚጋሩ ሀገራት የባሕሩ ባለቤት ከሆኑ፣ የዓባይ ወንዝ 85 በመቶ ባለቤት ለሆነችው ኢትዮጵያም ተመሳሳይ መብት ሊሰጣት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ፣ አንድ ሚሊ ሊትር ውሃ እንኳ ከግዛቷ የማይፈልቀው ካይሮ፣ ለዘመናት የዓባይን ወንዝ በበላይነት ስትጠቀም ኖራለች።

ኢትዮጵያ ግን "ዓባይ የእኔ ብቻ ነው" ብላ አታውቅም። በጋራ ተጠቃሚነት መርህ፣ የተፋሰሱን ሀገራት በማይጎዳ መልኩ፣ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ስታስተዳድር ቆይታለች።

"የኔ ባሕር የኔ ነው፣ የናንተ ወንዝ ግን የጋራችን ነው" የሚል ድርብ አስተሳሰብ የያዙ ሀገራት ጋር መግባባት ከባድ ነው። የአል-አላሚን መግለጫ፣ የቀጣናውን ሀገራት የሚያገልል፣ ስግብግብነትን የሚያሳይ ሰነድ ነው።

በቅርቡ የታዩ ተናጠላዊ ውሳኔዎች ለ21ኛ ክፍለ ዘመን የማይመጥን በጋራ መልማት እና የማደግ መርህን የሚጻረር ሆኖ ይነሳል።
ኢትዮጵያ ለሰላም ትቆማለች፣ ለትብብር እጇን ትዘረጋለች። ብሔራዊ ጥቅሟ ሲፈተን ግን፣ ወደኋላ አትልም።



በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/
📌በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
📌በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
📌በትሬድስ
https://www.threads.com/
📌በብሉ ስካይ
https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social
በደብልው ኤን ሶሻል
https://wnsocial.com/page/16775

06/10/2026

አዲስ ከተመሰረተው መንግስት ጋር ተባብረን የሀገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን :- የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች

የመደመር መንግስት በመመስረቱ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ እንደ ዜጋ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የቀጣይነት ጉዞ እና የሀገራዊ አንድነት ማብሰሪያኢትዮጵያ በሕዝብ ነፃ ፍላጎት እና በዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በይፋ ጀምራለች። ቀ...
06/10/2026

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የቀጣይነት ጉዞ እና የሀገራዊ አንድነት ማብሰሪያ

ኢትዮጵያ በሕዝብ ነፃ ፍላጎት እና በዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በይፋ ጀምራለች።

ቀደምት የሥልጣን ሽግግሮች በግጭትና በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራዊ ኪሳራን አድርሰዋል። ዛሬ ግን ሀገራችን ከእነዚያ የታሪክ ስህተቶች በመማር፣ የሕዝብን ድምፅ እና የሐሳብ አሸናፊነትን ያስቀደመ አዲስ የመንግሥት ምሥረታ እውን አድርጋለች።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በነፃነት እና በነቂስ ወጥተው በሰጡት ድምፅ በትናንትናው ዕለት 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምሥረታ ጉባኤ አዲሱን የመደመር መንግሥት በይፋ መሥርቷል።

በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ያሳለፍነው የምርጫ ሂደት ውዥንብሮችን እና ፈተናዎችን አልፎ የሕዝብን ሕልውና ያፀና እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህል መሠረቱን ያጠነከረ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

አዲሱ የመደመር መንግሥት የሕዝብን አደራና እምነት ሙሉ በሙሉ ተረክቦ የተነሳ በመሆኑ፣ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል የሚያስችል ጠንካራ አቅም አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው “በዚች ሀገር አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ አይኖርም” ሲሉ እያንዳንዱን ዜጋ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥታቸው በትጋት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

ይህ የሕዝብ ውሳኔ ሰጪነት እና የሀገር ሉዓላዊነት ማረጋገጫ የሆነው መንግሥት፣ ባለፉት ዓመታት የዜጎችን የዘመናት ጥያቄዎች የመለሱ በርካታ ታላላቅ የልማት ስኬቶችን አበስሯል።

የሀገራችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለዜጎች ምቹ የኑሮ ሁኔታን እና የሥራ ዕድል የፈጠሩት የገበታ ለሀገር፣ የገበታ ለትውልድ እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ትልቅ አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል።

የሌማት ትሩፋት እና በበጋ መስኖ ስንዴ ምርት የተመዘገበው ታሪካዊ ስኬት ሀገራዊ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል።

የኢትዮጵያውያን የጋራ አቅምና የፅናት ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሀገራችንን በቀጣናው የኃይል ምንጭ በማድረግ ለኢኮኖሚው ትልቅ ማነቃቂያ እየሆነ ይገኛል።

የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ በባሕር በርና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያላትን ፍትሐዊና ተፈጥሯዊ ፍላጎት በግልጽ ብሔራዊ ጥቅም አድርጎ በማስቀመጥ፣ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ውይይት በማድረግ ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን አከናውኗል።

አዲሱ የመደመር መንግሥት በሕዝብ ሙሉ ድጋፍ እና በተመዘገቡት ታላላቅ የልማት ስኬቶች ታግዞ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ የታላቋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋና ከፍታ የመገንባት ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

#የመደመርመንግሥት

! ! ! ‎

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሀሳብ ልዕልና እንዲመራና ለሕዝብ የተገዛ እንዲሆን መስራት ይገባል- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴየኢትዮጵያ ፖለቲካ በሀሳብ ልዕልና እንዲመራ ፣ ለሕዝብ የተገዛ እና ስክነት...
06/10/2026

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሀሳብ ልዕልና እንዲመራና ለሕዝብ የተገዛ እንዲሆን መስራት ይገባል- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሀሳብ ልዕልና እንዲመራ ፣ ለሕዝብ የተገዛ እና ስክነትን የጋራ ሀብት ያደረገ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፤ ሀገራዊ ሰላም፣ የዲፕሎማሲ ጥረቶች እና የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡

በቅርቡ የተካሄደው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ፣ ህብረ-ብሔራዊቷን ኢትዮጵያ በጽኑ የሀሳብ ምዕራፍ ላይ በማነጽ ፖለቲካው በሀሳብ ልዕልና እንዲያምን ሰፊ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ዋና ትኩረት ሰላም እና ብልጽግና በመሆኑ ፤ ከዚህ አላማ ውጪ ከቆሙ አካላት ጋርም ቢሆን በሰላም ለመነጋገርና ለመወያየት ፈቃደኛ መኮኑንና ወጤት መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

በጋራ ተጠቃሚነት እና በዲፕሎማሲያዊ የሰጥቶ መቀበል ላይ ተመስርቶ አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት ጥረት አህጉራዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ መሠረታዊ መብት መሆኑን ነው አጽንኦት የሰጡት።

በኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ ላይ በግልጽም ሆነ በስውር አዎንታዊ ሃሳቦች መታየታቸው እና ውይይቶች መደረጋቸው ገልጸዋል።

አዳዲስ ልማቶች እና ሐሳቦች ሲመጡ ተያይዘው የሚመጡ ፈተናዎችን በጤናማ እና በመልካም ሐሳቦች ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎችን በመስጠት ማለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን ታሪክ እና ጠንካራ ተሞክሮዎች በመጠቀም ለሀገር ዕድገት፣ ለፖለቲካ መሠረቶች ማጠናከሪያ እንዲሁም የሰንደቅ ዓላማን ክብር ከፍ ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/
📌በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
📌በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/
📌በትሬድስ
https://www.threads.com/
📌በብሉ ስካይ
https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social
በደብልው ኤን ሶሻል
https://wnsocial.com/page/16775

Address

Bonga

Telephone

+251913241234

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Southwest Communications:

Shortcuts

Share