SWEPRS Bureau of Agriculture, Livestock & fishery department

SWEPRS Bureau of Agriculture, Livestock & fishery department ደቡብ ምዕራብ እንስሳትና ዓሣ ልማት ዘርፍ የክህሎትና ዕውቀት ሽግግር በማምጣት አርሶ አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሠራ ዘርፍ

04/02/2025
10/01/2025

የቅድመ ወላጅ ዶሮ ማዕከል የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያ አቅርቦትና ስርጭት ችግርን በዘላቂነት የሚፈታ ነው፡፡
*************************

በእንስሳት ዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ምርታማነት ለመቀየር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ አሰራርን ማዘመንና ልዩ ትኩረት መስጠት ላይ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ ለዚህም የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ትልቅ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

በሌማት ትሩፋት በልዩ ትኩረት ከሚሰሩ ስራዎች መካከል አንዱ የዶሮ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለዶሮ እርባታ ምቹ የሆኑ ሥነ-ምህዳሮች ያሏት ሀገር ብትሆንም የዶሮ እርባታ ዘርፉ ለምግብ ስርዓቱ እና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሲያበረክት የነበረው አስተዋፅዖ ከተለያዩ መለኪያዎች አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ሆኖ ቆይቷል።

ለዚህ በምክንያትነት ከሚጠቀሱት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሀገር ውስጥ የዶሮ ዝርያዎች ምርታማነት አነስተኛ መሆን እና ዝርያቸው የተሻሻሉ ዶሮዎች ከውጪ ለማስገባት የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት መኖር እንዲሁም የዶሮ መኖ ዋጋ ውድ መሆን ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያ አቅርቦትና ስርጭትን በመፍታት ምርታማነትን እያሳደገ ይገኛል፡፡

የተሻሻለ የዶሮ ዝርያ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ኩባንያ ጋር በመተባበር የቅድመ ወላጅ ዶሮ ማዕከል (Grandparent stock farm) ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ማዕከሉ በሌማት ትሩፋት የተያዙ ግቦችንና አጠቃላይ አገራዊ የዶሮ ልማትን ለማሳደግ ትልቁን ድርሻ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡

በዚህ መነሻነት ማዕከሉ በሚቀጥሉት ወራቶች (ከሚያዝያ ወር ጀምሮ) በአጠቃላይ 550,000 የሚደርሱ ቴትራ ኤች የተባሉ የዶሮ ዝርያ ወላጅ ዶሮዎችን በማምረት ለማስፈልፈያ ተቋማት ያሰራጫል፡፡ የቴትራ ኤች የዶሮ ዝርያ ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው (ለስጋና ለእንቁላል የሚሆኑ) ዶሮዎች ሲሆኑ ይህ ዝርያ በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ውጪ በአፍሪካ አህጉር በጋና፣ ሴኔጋል እና ቡርኪናፋሶ ይገኛል፡፡

እነዚህ ዶሮዎች በምርታማነታቸው የተመረጡ ሲሆን በአጭር ጊዜ እንቁላል የሚጥሉ፣ በሞት መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ፣ የእንቁላል ምርታቸው በቤት ውስጥ እርባታ በአመት ከ230-250 የሚደርስ እና የእንቁላሉ ክብደትም የተሻለ ሲሆን ከ60-62 ግራም መጠን ያለው ነው፡፡

በመሆኑም ይህንን ማዕከል ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን በሀገር ውስጥ ያሉ የግልና የመንግስት ማስፈልፈያ ማዕከላትን ለማጠናከር፣ ጥራት ያለው የመኖ አቅርቦትና ተደራሽነትን ለማስፋፋት እንዲሁም የዶሮ ስነ ህይወት ደህንነት ጥበቃ ስርዓትን ለመተግበር እና የጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

#ከማምረትበላይ

----------------
ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia

እንስሳት ዝርያን ማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው።በኮንታ ዞን በማዳቀል መንታ ጥጃ ተገኘ።ዝርያ የተሻሻለች አንዲቲ ላም 42 ሊትር ስትታለብ 27 የአካባቢ ላሞች ጋር እኩል ነው።
10/12/2024

እንስሳት ዝርያን ማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው።

በኮንታ ዞን በማዳቀል መንታ ጥጃ ተገኘ።

ዝርያ የተሻሻለች አንዲቲ ላም 42 ሊትር ስትታለብ 27 የአካባቢ ላሞች ጋር እኩል ነው።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!!!ሚያዝያ 25/2016 ቦንጋ የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ህዝበ ክርስቲያኑ በዓልን ስያከ...
03/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!!!ሚያዝያ 25/2016 ቦንጋ የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ
ህዝበ ክርስቲያኑ በዓልን ስያከብር በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ እንድሆን እየተመኘ ማንኛውም እርድ የእንስሳት ጤና ፕሮቶኮልን የጠበቀና በባለሙያ ምርመራ የታገዘ እንድሆን እያሳሰብን በእርድ ወቅት የሚገኙ ቆዳና ሌጦ በየቦታ እንዳይወድቅ በጥንቃቄና በጥራት እንድሰበሰብ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

ዓሣን እንደ ጎመን ከጓሮ
01/02/2024

ዓሣን እንደ ጎመን ከጓሮ

Address

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
Bonga

Telephone

+251917310909

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SWEPRS Bureau of Agriculture, Livestock & fishery department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share