ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office

  • Home
  • Ethiopia
  • Boditi
  • ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office

ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office ትጋት ለላቀ ስኬት ! https://t.me/Boditiprosperity

18/09/2026
18/09/2026
‎የጊፋታ በዓል ዋዜማ የሴቶች አደረጃጀቶች በተለያዩ ዝግጅት አከበሩ‎‎ቦዲቲ ፤መስከረም 8/2019 የወላይታ ዞን ሴቶች አደረጃጀቶች የታላቁ ጊፋታ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በልዩ ድምቀ...
18/09/2026

‎የጊፋታ በዓል ዋዜማ የሴቶች አደረጃጀቶች በተለያዩ ዝግጅት አከበሩ

‎ቦዲቲ ፤መስከረም 8/2019 የወላይታ ዞን ሴቶች አደረጃጀቶች የታላቁ ጊፋታ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በልዩ ድምቀት ዋዜማውን አክብረዋል።

‎የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ጊፋታ በውስጡ በርካታ እሴቶችን የያዘ በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

‎ከዚህም አንድነትን፣ ይቅርታን፣ ፍቅርን፣ አብሮነትንና እህተማማችነት በዋናነት ይጠቅሳሉ ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት፥ በዓሉ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ እርስበርስ ፍቅርንና እህተማማችነትን የምንገልጽበት ነው ብለዋል።

‎ጊፋታ በዓሉን ለማድመቅ ሴቶች ገና ወራቶች ሲቀሩ የተለያዩ ኩኔቶችን በመሰራት በዓሉን በፍቅር እንደሚጠባበቁም ተናግረዋል።

‎ሴቶች የቅቤ ዕቁብ በመጣል፣ የገንዘብ ቁጠባ በማድረግና እንሴት መፋቅ ለበዓሉ ወራቶች ሲቀሩ የሚሰሩ ተግባራት መሆናቸውንም ገልፀዋል።

‎በዓሉን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፥ ለዚህም ሴቶች የሚጠብቅባቸውን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም አሳስበዋል።

‎ሴቶች ለጊፋታ ከሚያዘጋጁት ምግብ እና መጠጥ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በተጨማሪ የቁጠባ ባህላቸውን የሚያሳድጉበት ነው ያሉት።

‎በጊፋታ በዓል የሴቶች ሚና አንጻር ከአዲሱ ዓመት ከአምስተኛው ወር ጀምሮ ለተለያዩ ባህላዊ ምግቦች ማለትም ለቆጮ፣ ለሙቹዋ፣ ለባጪራ የሚሆኑ የደረሱ እንሰቶችን በመፋቅ ዝግጅት እንደሚያደርጉም አስታውሰዋል።

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ላምበቦ ጊፋታ በዓል በወላይታ ህዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅና የማንነት መገለጫ ነው ብለዋል።

18/09/2026

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጊፋታ በዓል ኩነት ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅመ ለመሸፈን በማሰብ ሁሉም ቀበሌያት አንዳንድ ሰንጋ በሬ ድጋፍ ለከተማ ማዕከል ሰጡ

ቦዲቲ ፤ መስከረም ፤ 8/2019 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጊፋታ በዓል ኩነት ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅመ ለመሸፈን ሁሉም ቀበሌያት አንዳንድ ሰንጋ በሬ ድጋፍ ለከተማ ማዕከል ሰጠጥተዋል።

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጊፋታ በዓል ኩነት ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅመ ለመሸፈን በማሰብ ሁሉም ቀበሌያት አንዳንድ ሰንጋ በሬ ድጋፍ ለከተማ ማዕከል ሰጡቦዲቲ ፤ መስከረም ፤...
18/09/2026

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጊፋታ በዓል ኩነት ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅመ ለመሸፈን በማሰብ ሁሉም ቀበሌያት አንዳንድ ሰንጋ በሬ ድጋፍ ለከተማ ማዕከል ሰጡ

ቦዲቲ ፤ መስከረም ፤ 8/2019 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጊፋታ በዓል ኩነት ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅመ ለመሸፈን ሁሉም ቀበሌያት አንዳንድ ሰንጋ በሬ ድጋፍ ለከተማ ማዕከል ሰጠጥተዋል።

በቦዲቲ ከተማ የሚገኙ አስሩም ቀበሌ አስተዳደሮች ለሰብዓዊ ድጋፍ አላማ ያዘጋጁትን ሰንጋ በሬ የወላይታ ዞን ምክትል አፈጉባኤ አቶ ጻዲቁ ፈለቀ እና የከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት በተገኙበት አስረክበዋል።

የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ዘካሪያስ ጃታ ሁሉም ቀበሌያት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው በመፈጸም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ስለተወጡ አመስግነዋል።

የወላይታ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አመራሮችና ሰራተኞች በመምሪያቸው የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብረዋል።
18/09/2026

የወላይታ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አመራሮችና ሰራተኞች በመምሪያቸው የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብረዋል።

18/09/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት በተካሄደው የጊፋታ ሩጫ የቦዲቲ ከተማ ተሳትፎ በምስል።

በታላቅ ድምቀት የተካሄደው የጊፋታ ሩጫ በምስል፤
18/09/2026

በታላቅ ድምቀት የተካሄደው የጊፋታ ሩጫ በምስል፤

18/09/2026

ተወዳጁ የወላይታ ህዝብ ሃያያ ሌኬ /Hayaya Leke/ጨዋታ



#ዮዮጊፋታ

Address

Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share