28/05/2026
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች ሆይ‼️
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
የተሻለ የፖሊሲ አማራጭ ያቀረበውን፣ በምርጫ ክርክሮቹ የላቀ ሀሳብ በማቅረብ ነጥሮ የወጣውን፣ ለቀጣይ አምስት አመት ሀገርን የመምራቱ እድል ቢሰጠው ለማስተዳደር በበቂ ቁመና ላይ የሚገኘውን፣ ተባብሮና ተቀናጅቶ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነውን፣ ሚዛናዊና ምክንያታዊ የትግል ስልትን የሚከተለውን፣ ከየትኛውም ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ የራቀውን፣ የአድሱ ትውልድ ፓርቲ 👇
"ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ምርጫችሁ ይሁን‼️
✍️ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ሚዛናዊነት፣ ምክንያታዊነት፣ አብሮ ማሸነፍ እና አካታችነት መርሆቻችን ናቸው‼️
✍️ ትምህርት መር ብሔራዊ የልማት ስትራቴጅን እንከተላለን‼️
(Education Driven National Development Strategy - ENDS)
ሀገራችንን ቀስፎ የያዛት ጥላቻ መፈናቀል ጦርነት ስዴትና ሞት ደጉን የሀገራችንን ህዝብ ወግና ባህል እንድሁም እምነት የማይወክልና የሚያራክስ በመሆኑ በሀገራዊ እርቅና ብሔራዊ መግባባት እንድፈታና ዜጎች በሀገራቸው ያለስጋት ሰርተው እንድኖሩ በሰላም ወጥተው እንድገቡ ፓርቲያችን ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) አበክሮ ይሰራል።
ሁሉንም የሀገራችንን ህዝቦች መፈናፈኛ ያሳጣው የኑሮ ውድነት የዋጋ ግሽበት ረሀብና ድህነት የመኖሪያ ቤት እጦትና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውስብስብ ችግሮችና ማነቆዎች በተፈጥሮ የተከሰቱ ሳይሆኑ ከብልሹ አሰራርና አስተዳደር ከሙሰኝነት ካለጠራና ካልተገራ ፓሊሲና ስትራቴጅ እና የትግበራ እንዝህላልነት የሚመነጩ ናቸው ብሎ ፓርቲያችን ነእፓ ያምናል።
በመሆኑም እጅግ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ከህዝባችን ጫንቃ ላይ ማራገፍ የሚያስችል ፓሊሲና አሰራር ይዘንላችሁ መጥተናል። የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ የሆነውን ብዕርን ይምረጡ‼️
የጥቂቶች ብልጽግና በብዙሀን ድህነትና ጉስቁልና ላይ መመስረት የለበትም። ፓርቲያችን ነእፓ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልና የጋራ ተጠቃሚነት በሀገራችን እንድሰፍን የሚያስችል ፕሮግራም አዘጋጅቷል።
የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት በተግባር የሚያረጋግ ፓሊሲና ስትራቴጅ አበጅተናል። ሴቶች እድሉ ከተመቻቸላቸው የሀገር ዋልታና ማገር ናቸው።
አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ የማህበራዋዊና ኢኮኖሚያዊ ፓሊሲዎችን ቀርጸናል።
የውጭ ድፕሎማሲን የሚያጎለብት ለሀገራችን አምስት የባህር በር የሚያስገኝ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያጎናጽፍ በአርቆ አሳቢነት የተነደፈ ድንቅ ፓሊሲ አዘጋጅተናል። እንድሁም በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ዜጎቻችን የጣምራ ዜግነትን የሚፈቅድ አሰራር ጀባ ብለናል።
ወጣቶች በሀገራቸው ንቁ ተሳታፊ ሆነው ሰርተው ራሳቸውን ማበልጸግ ቤተሰቦቻቸውንና ሀገራቸውን መርዳት የሚያስችል እምቅ ኃይልና እውቀት እንዳላቸው እየታወቀ ቆራጥ አመራርና አሳታፊ አደረጃጀት ባለመዘርጋቱ ብዙ ወጣቶች ስራ አጥ ጥገኛና ተመጽዋች መሆናቸው አልፎም በስደት በየበረሀውና በየባህሩ ወድቀው እንድቀሩ መደረጉ እንቅልፍ የሚነሳው ፓርቲያችን ነእፓ ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የሀገር ኢኮኖሚ ዝርጋታን ይከተላል።
ነጻነትና እኩልነት ስንል ምን ማለታችን ነው??
✍️ ነጻነት ስንል፦
➠ የመናገር ነጻነት
➠ የማሰብ ነጻነት
➠ የእምነት ነጻነት
➠ ከድህነትና ረሀብ ነጻነት
➠ መፈናፈኛ ካሳጣን የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ነጻነት
➠ ከመፈናቀል ከጦርነትና ከስደት ነጻነት
➠ የመደራጀት ነጻነት
➠ ከፍርሀት ነጻነት
➠ ከጭቆናና አፈና ተጻነት
✍️ እኩልነት ስንል፦
➠ በብሄሮች መካከል
➠ በሃይማኖቶች መካከል
➠ በጾታ መካከል
➠ በእድሜ መካከል
➠ በትውልድ መካከል
➠ በክልሎችና አካባቢዎች መካከል
➠ በስራ ቦታና የስራ እድል ከማግኘት አኳያ
➠ የፍትህ እኩልነት
➠ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች
እኩልነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብሎ ፓርቲያችን ነእፓ በጽኑ ያምናል። ለተግባራዊነታቸውም ዘመናዊ አሰራሮችን አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይከተላል።
የመሬት ፖሊሲያችን ከመንግስት ጭሰኝነት የሚያወጣ የገጠርም የከተማም የመሬት ባለይዞታዎች በመሬታቸው በነጻነት የመጠቀም መብታቸውን የሚያጎናጽፍ ነው። ሰፊ ጥናት ከተደረገ በኋላ በሂደት ወደ ግል ይዞታነት በማሸጋገር መሸጥ መለወጥ የሚያስችል ህግ በሀገራችን ይሰፍናል።
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
የፓርቲያችን የመወዳደሪያ የምርጫ ምልክት ብዕር ነው። ብዕር ደግሞ ረቂቅ ሀሳቦች የሚሰፍሩበት ጥልቅ ምርምሮች የሚወጠኑበት ታላቅ መሳሪያ ነው። ብዕር እውቀት መር ፓሊሲያችንን የገለጽንበት ድንቅ መሳሪያ ነው።
ብዕር የእውቀት፣ የጥበብ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጅ፣ የስልጣኔ መገለጫ እና የችግሮች ሁሉ መፍቻ ድንቅ መሳሪያ ነው‼️
የእውቀትና ልዕልና መገለጫ የፍትህና ስልጣኔ ማብሰሪያ የሆነውን ብዕርን ይምረጡ‼️
ነጻነትን እኩልነትን ፍትህን ይምረጡ‼️
ብዕርን ይምረጡ‼️