Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን

Worebabo  Communication   ወረባቦ  ኮሙኒኬሽን የወረባቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ለወረዳዉ ማህበረሰብ ፈጣንና ተአማኒ መረጃ ለመስጠት ይተጋል!!

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን 7ኛው ጠቅላለ ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ መሆኑን ገለጸ++++++++++++++++ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ...
03/06/2026

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን 7ኛው ጠቅላለ ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ መሆኑን ገለጸ
++++++++++++++++

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ መሆኑን ገለጸ።

የምርጫ ታዛበ ቡድን ምርጫውን አስመልክቶ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ምልከታ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል።

የኢጋድ ታዛቢ ቡድን ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ምርጫ በማዘጋጀትና በማስፈጸም ረገድ ያሳየውን ከፍተኛ አስተዳደራዊና ተግባራዊ አቅም አድንቋል።

የኢጋድ የታዛቢዎች ቡድን ሰብሳቢ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዙቤ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የታዘቡት ምርጫ ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ የታየበት ነው።

ሰብሳቢዋ ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደረሰው ጥሪ መሠረት 26 አጭር ጊዜ ታዛቢዎችን ያቀፈ ቡድን በማሰማራት ሂደቱን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ጠቅሰው፣ በምርጫው የታዩ አስተዳደራዊ ማሻሻያዎችን አድንቀዋል።

ቦርዱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን በ501ዱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ ወደ 52 ሺህ የሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎችን በተሳካ ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል መቻሉን ቡድኑ በሪፖርቱ አመልክቷል።
ኢፕድ

በወረባቦ ወረዳ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁንና የምርጫ ኮሮጆዎች ወደ ማእከል በሰላም እንዲገቡ መደረጉን  የወረባቦ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አሳወቀ ። ▽▽▽▽▽ቢስቲማ -ግንቦት 25/20...
02/06/2026

በወረባቦ ወረዳ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁንና የምርጫ ኮሮጆዎች ወደ ማእከል በሰላም እንዲገቡ መደረጉን የወረባቦ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አሳወቀ ።
▽▽▽▽▽
ቢስቲማ -ግንቦት 25/2018 (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን )

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት በወረዳው ባሉ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት መጠናቀቁን የወረባቦ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አስታወቀ።

የወረባቦ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ም/ኮማንደር ከፈለኝ አረጋ ምርጫ ህጋዊ ፣ ህዝባዊ መንግስትን የመመስረቻና ዲሞክራሲን የማረጋገጫ ሂደት በመሆኑ ህብረተሰቡ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በወረዳው ባሉ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር በትናንትናው እለት ድምፅ ሲሰጥ ቆይቶ የድምፅ መስጠት ሂደቱ በስኬት ተጠናቋል።

በዛሬው እለት የምርጫ ቁሳቁሶችን ከምርጫ ጣቢያዎች ያለ ምንም የፀጥታ ችግር ወደ ማእከል እንዲገቡ መደረጉን የገለፁት ም/ኮማንደር ከፈለኝ የወረዳው ማህበረሰብና የፀጥታ ሀይል ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅና ላበረከተው አስተዋፅኦ ልባዊ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።

በወረባቦ ምርጫ ክልል  በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው። በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ  የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤቶችን ይፋ እያደረጉ ...
02/06/2026

በወረባቦ ምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው።

በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤቶችን ይፋ እያደረጉ ነው።

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የምርጫዋን እለት ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ

01/06/2026

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር አብዱ ሁሴን በወረባቦ ምርጫ ክልል ቢስቲማ 01 ሀ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ በሰጡበት ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ከአሚኮ

ለሀገርም ለህዝብም ይጠቅማል ያሉትን ለመምረጥ በመሳተፋቸው  መደሰታቸውን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ ▽▽▽▽▽▽ቢስቲማ - ግምቦት 24/2018 (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን )በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ...
01/06/2026

ለሀገርም ለህዝብም ይጠቅማል ያሉትን ለመምረጥ በመሳተፋቸው መደሰታቸውን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ
▽▽▽▽▽▽

ቢስቲማ - ግምቦት 24/2018 (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን )

በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የወረባቦ ወረዳ ማህበረሰብ የምርጫ ካርድ ባወጡበት የምርጫ ጣቢያ ከጧቱ 12 ሰአት ጀምሮ ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛል ።

ድምፃቸውን ሰጥተው ሲወጡ ያገኘናቸው አቶ አሊ መሀመድ ምርጫ ስልጣን የህዝብ መሆኑን በተግባር የምናይበት በመሆኑ በፍትሃዊ መንገድ ከማንም አካል ነፃ ሁኜ ለኔም ለሀገሬም ይበጃል ያልኩትን ፓርቲ በመምረጤ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

ሌላዋ ወ/ሮ ሃዋ ሰይድ ምርጫን መምረጥ መብት ቢሆንም እኔም መብቴን በአግባቡ በመጠቀም ስመርጥ ደስተኛ ሁኜ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የወረባቦ ምርጫ ክልል በተለያዮ የምርጫ ጣቢያዎች  የመራጮች ድምፅ መስጠት ተጠናክሮ ቀጥሏል
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የወረባቦ ምርጫ ክልል በተለያዮ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምፅ መስጠት ተጠናክሮ ቀጥሏል

በወረባቦ ምርጫ ክልል የተለያዮ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው
01/06/2026

በወረባቦ ምርጫ ክልል የተለያዮ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር  ዶ/ር አብዱ ሁሴን በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ተገኝተው   ድምጻቸውን ሰጡ።▽▽▽▽▽ቢስቲማ -ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን ) በወረባ...
01/06/2026

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር አብዱ ሁሴን በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጡ።
▽▽▽▽▽
ቢስቲማ -ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን )
በወረባቦ ምርጫ ክልል ቢስቲማ 01 ሀ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የአማራ ክልል ም/ርእሰ መስተዳደር ዶ/ር አብዱ ሁሴን በቦታው ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው በወረባቦ ወረዳ  7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው

በወረባቦ ወረዳ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

Address

Bistima
Bistima

Telephone

+251332210032

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን:

Share