Bedessa Town Administration Health Unit

Bedessa Town Administration Health Unit Bedessa Town Admin Health unit
የበዴሳ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት

ጥራት ያለው የሕክምና እና ምርመራ አገልግሎት የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።በዴሳ መጋቢት 19፣ 2018 ዓ/ም  ጥራት ያለው የሕክምና እና ምርመራ አገልግሎት ...
28/03/2026

ጥራት ያለው የሕክምና እና ምርመራ አገልግሎት የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

በዴሳ መጋቢት 19፣ 2018 ዓ/ም ጥራት ያለው የሕክምና እና ምርመራ አገልግሎት የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

በዴሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በዛሬው ቀን የCBC ማሽን ምርመራ አገልግሎት በይፋ ጀምሯል።
CBC(complete blood count) ማሽን ጥቅሙ ሙሉ የደም ቆጠራ ማድረግ ስሆን ታካሚዎች ጥራት ያለውን የሕክምና እና ምርመራ አገልግሎት እንድያገኙ ከማድረግ ባሻገር ከዚህ በፊት ሌላ አከባቢ ለሕክምና ተብሎ የሚወጡ ወጪዎችንና እንግልቶችን በሙሉ ይቀንሳል።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት ስሰጥ የነበረውን የultrasound አገልግሎት በተሻለ ጥራትና መጠን መስጠት መጀመሩ መንግስት ከመቼውም ግዜ በተሻለ መልኩ ለማህበረሰቡ ጤና መጠበቅ እየሠራ መሆኑ ማሳያ ነው።

የማላሪያ ኮንሰሪትየም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በወላይታ ዞን በበዴሳ ከተማ አስተዳደር እና በሶዶ ከተማ አስተዳደር ሾላ ኮዶ ጤና ጣቢያ በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ያሉ የጤና ሥራዎች ምልከታ አደረ...
23/03/2026

የማላሪያ ኮንሰሪትየም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በወላይታ ዞን በበዴሳ ከተማ አስተዳደር እና በሶዶ ከተማ አስተዳደር ሾላ ኮዶ ጤና ጣቢያ በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ያሉ የጤና ሥራዎች ምልከታ አደረጉ

ወላይታ ሶዶ፤መጋቢት 14 2018 ዓ.ም፤የማላሪያ ኮንሰሪትየም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተመራው ሉካን ቡድን በወላይታ ዞን በበዴሳ ከተማ አስተዳደር እና በሶዶ ከተማ አስተዳደር ሾላ ኮዶ ጤና ጣቢያ በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ያሉ የጤና ሥራዎች ምልከታ አደረጉ።

በመስክ ምልከታ ላይ የማላሪያ ኮንሰሪትየም Country Director, የማላሪያ ኮንሰሪትየም ዓለም አቀፍ Chair Person እና ሌሎች የቡድኑ አባላት በወባ በሽታ መከላከልና ማጥፋት እና በተላላፊ ባልሆነ የዝሆነ በሽታ ህክምናና መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን በበዴሳ እና በሾላ ኮዶ ጤና ጣቢያ ምልከታ አድርገዋል።

ከመስክ ምልከታ በኋላ በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ለዚህም የዞን፣ የከተማ አስተዳደር፣ የወረዳና የጤና ተቋማት ድጋፍና ክትትል ከፍተኛ መሆኑን አመስግነዋል።

14/03/2026
ጤና ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ፣ውብ፣ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።በዴሳ፣ የካቲት 19 ፣2018 ዓ/ም ጤና ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ፣ውብ፣ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆ...
26/02/2026

ጤና ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ፣ውብ፣ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በዴሳ፣ የካቲት 19 ፣2018 ዓ/ም ጤና ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ፣ውብ፣ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
በበዴሳ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት የበዴሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ተቋሙን ለተገልጋዮች ምቹና ሳቢ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል። ጽዳት፣ውበት እና ደህንነቱ የተጠበቀ ጤና ተቋም ተገልጋይን አገልግሎት የማግኘት ፍላጎትን የሚጨምር መሆኑ በሳይንስ የተረጋገጠ ከመሆኑ በተጨማሩ የተገልጋይ እርካታ እንድጨምር ከማድረግ ባሻገር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት" በሚል መሪህ ቃል ዞናዊ የጤናማ እናትነትን ወር መርሀግብር አካሄደ ወላይታ ሶዶ፤የካቲት 13 2018 ዓ.ም፤የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀገርአቀፍ የጤ...
20/02/2026

ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት" በሚል መሪህ ቃል ዞናዊ የጤናማ እናትነትን ወር መርሀግብር አካሄደ

ወላይታ ሶዶ፤የካቲት 13 2018 ዓ.ም፤የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀገርአቀፍ የጤናማ እናትነት ወር በወላይታ ሶዶ ከተማ አከበረ ።

በፕሮግራሙ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ም/ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ የእናቶችንና ህፃናትን ጤንነትን መጠበቅና ሞታቸውን መቀነስ የሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት መገለጫ በመሆኑ ሴክተሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል አንደሚገባ አሳስበዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የእናቶችና ህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ጎጆለ ጎአ እንደተናገሩት ጤናማ የእርግዝና፣ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎቶችን ለሁሉም እናቶች ተደራሽ በማድረግ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት መቀነስ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የተለያዩ የጤናማ እናትነት ሰነዶች እና የ7 ወራት የእናቶችና ህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ቀረበው በሪፖርቱ መነሻ በቀጣይ መፍትሄ በሚያመጡ ጉዳዮች ዙሪያ ተሳታፊዎች በሰፊው ውይይት አድርጓል ስል የዘገበው የመምሪያው ሕዝብ ግንኙነት ነው።

ወቅቱን የጠበቀ  ድጋፍና ክትትል የተቋማት አገልግሎት አሠጣጥ እንድሻሻል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።በዴሳ የካቲት 10፣ 2018ዓ/ም ወቅቱን የጠበቀ  ድጋፍና ክትትል የተቋማት አገልግሎት አ...
17/02/2026

ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍና ክትትል የተቋማት አገልግሎት አሠጣጥ እንድሻሻል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

በዴሳ የካቲት 10፣ 2018ዓ/ም ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍና ክትትል የተቋማት አገልግሎት አሠጣጥ እንድሻሻል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

በበዴሳ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት ስር ባሉ ሁሉም ጤና ተቋማት የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በዛሬው ቀን በበዴሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በይፋ ተጀምሯል። በተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ጤና ተቋማት፣ ጤና ኬላዎች፣ እስከ ማህበረሰብ ድረስ ጠንካራ ድጋፍ ተደርጎ ባለድርሻ አካላት በተገኙቡት ግብረ-መልስ ይሰጣል።

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ችላለች። በጠንካራ የጤና ሥርዓት እና በብዙዎች ርብርብ ለሌሎች ተሞክሮ በሆነ መንገድ በሽታ...
26/01/2026

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!

ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ችላለች።

በጠንካራ የጤና ሥርዓት እና በብዙዎች ርብርብ ለሌሎች ተሞክሮ በሆነ መንገድ በሽታውን መቆጣጠር ችለናል።

ለዚህ ስኬት ከፍተኛ ርብርብ እና ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራችሁ የጤና ባለሙያዎች፣ አጋሮች እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ።

አቶ ዳዊት ደሳለኝ
የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ

በበዴሳ ከተማ አስተዳደር በበዴሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል  በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት መድረክ ተካሂዷል በዴሳ፤ጥር 14/2018ዓ.ምበበዴሳ ከተማ አስተዳደር በበዴሳ መጀመ...
22/01/2026

በበዴሳ ከተማ አስተዳደር በበዴሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት መድረክ ተካሂዷል

በዴሳ፤ጥር 14/2018ዓ.ምበበዴሳ ከተማ አስተዳደር በበዴሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የበዴሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ቢኒያም ብርሃኑ እንዳሉት ጤና ተቋማት ከሕብረተሰብ በሚሰጡ አስተያየቶችን መነሻ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጥን በሚፈለገው ልክ ማሻሻል እንዳለባቸው ጠቁሟል።

በመድረኩ የበዴሳ መ/ደ/ሆስፒታል የ5 ወር ተግባር አፈፃፀም የቀረበ ስሆን በቀረበው ሪፖርት መነሻ ከሕብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ አካላት ሰፊ ሃሳብና አስተያየት የሰጡ ስሆን ቀጣይ መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ተቋሙ፣ሕብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አብሮ በመቀናጀት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሠራ ተጠቁሟል።
በመድረኩ ላይ የበዴሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ቢኒያም ብርሃኑ፣የጤና ዩኒት አስተባባሪና ማናጅመንት፣ከየማሕበረሰብ ክፍል የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮችና አጠቃላይ የሆስፒታል አመራሮችና ሠራተኞች ተገኝቷል።

Address

Bedessa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bedessa Town Administration Health Unit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share