02/06/2026
በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የተካሄደው 7ኛው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ፣ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 1 የምርጫ ክልል እና 164 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሰላማዊ፣ ስልጡን እና ስኬታማ በሆነ መንገድ ተጠናቋል ብለዋል።
ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ የተካሄደው ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ እና ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
ለመላው ሰላም ወዳድ የከተማው ማህበረሰብ፣ከምርጫው መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ማጠቃለያው ድረስ ሕግን በማክበር፣ ሰላምን በማስቀደም እና ከፍተኛ የዜግነት ኃላፊነት ስሜትን በማሳየት ለቆማችሁ፤ የጸጥታ አካላት ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሌት ከቀን ያለመታከት በቁርጠኝነት ለወጣቹህ ለወረዳቹህ ለደከማችሁ፤ በሂደቱም ላይ ንቁ ተሳትፎ ላደረጋችሁ በሙሉ፤ በራሴ እና በፖሊስ መምሪያው ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን እና አክብሮቴን አቀርባለሁ ብለዋል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምሪያ
የሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://www.facebook.com/BahirDarCityAdministrationPoliceDepartment
🇪🇹" "በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል"🇪🇹