ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ, Government Organization, University Road, Bahir Dar.
(1)

This page is designed to promote and provide information on the comprehensive activities of the Mineral Resources Development Bureau.//ይህ ገፅ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ሁለተናዊ ተግባር ለማስተዋወቅና መረጃ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው።

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ካሳ ክፍያን ይፋ አደረገ።----------------------ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2018 ዓ.ም :- የባሕርዳር ከተማ አሥተዳድር ከ...
26/05/2026

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ካሳ ክፍያን ይፋ አደረገ።
----------------------
ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2018 ዓ.ም :- የባሕርዳር ከተማ አሥተዳድር ከንቲባ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን ከከተማ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

ከውሣኔዎች መካከልም የመንግሥትና የግል ተቋማት እና የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ካሳ ይገኝበታል።

ከተማ አሥተዳደሩ በቅርቡ ከ780 በላይ የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት እውቅና መስጠቱ ይታወቃል። ከንቲባ ኮሚቴው አንድ በቤት ማኅበር የተደራጀ አባል 2 መቶ 20ሺህ ብር ለካሣ ክፍያ መክፈል የሚጠበቅበት መሆኑን ነው ዛሬ የወሰነው።

ኾኖም ግን የከተማ አሥተዳደሩ ከንቲባ ኮሚቴ የዝቅተኛና የመካከለኛ ነዋሪዎችን የመቆጠብ አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት እና ዜጎችን የቤት ማኅበር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማሰብ ለቅድመ ቁጠባ አባላት የከፈሉትን 120ሺህ ብር የካሳ ክፍያው አካል እንዲሆን በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተገልጿል።

በዚህም 120ሺህ ብር የቆጠበ የማኅበር አባል ለካሣ ክፍያ የሚጠበቅበት ተጨማሪ 100 ሺህ ብር መኾኑ ነው የተጠቀሰው። ይህንም በባንክ እንዲከፍል ተደርጎ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ተገልጿል።

ከንቲባ ከሚቴው ይህ ውሣኔ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ የየማኅበሩ አባላት በተፈቀደው አጭር ቀናት ከላይ የተገለፀውን ክፍያ በባንክ ገቢ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።
@አሚኮ

🏔️ ከአባይ ወለል እስከ እራስ ደጀን ከፍታ፦ የአማራ ክልል ማዕድናት እና የአዲሱ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማብሰሪያ! ✨-------------------------ለዘመናት በምድራችን እምብርት ተሠውሮ ...
24/05/2026

🏔️ ከአባይ ወለል እስከ እራስ ደጀን ከፍታ፦ የአማራ ክልል ማዕድናት እና የአዲሱ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማብሰሪያ! ✨
-------------------------
ለዘመናት በምድራችን እምብርት ተሠውሮ የኖረው ተፈጥሯዊ ፀጋችን፣ አሁን የክልላችንን እና የሀገራችንን የኢኮኖሚ ትከሻ ሊያጠናክር "ከማዕድን ያባላል ወደ ማዕድን ያበላል" አድጎ ከቀኝ አዝማችነት ወደ መሪ ተዋናይነት ተሻግሯል! ከአማራ ክልል ተራሮች ስርና ከቀደሙት ወንዞች ተፋሰስ የተከማቸው እምቅ የማዕድን ሀብት የኢንዱስትሪ ትንሳኤያችን አዲሱ የምሥራች ሁኗል።

ከባህላዊና ከተገደበ የግብርና አጥር ወጥተን አገራችንን ወደ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት፣ አማራ ክልል ያሉትን የሀብት ክምችቶች በዕውቀትና በቴክኖሎጂ አቀነባብሮ መጠቀም ጀምሯል። በዚህም የከርሠ-ምድርና ገጸ_ምድር ሀብትን ወደ ብሔራዊ ምርታማነት የመቀየር አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ተከፍቷል።

የማምረቻው ዘርፍ እንደ ወንዝ ውሃ የኢኮኖሚውን አቅጣጫ የሚቀይር ሲሆነ፣ የአማራ ክልል ምድር ደግሞ የዚያ ወንዝ ታላቅና የማይነጥፍ ምንጭ ነው! 🌊

💎 የምድራችን በረከቶች፦ ከምድር ጥልቀት ወደ ፋብሪካዎች ግብዓት

አገራችንን የኢንዱስትሪ ፋና ለማድረግ በማዕድኑ ዘርፍ የጀመርነው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ(Mintex) እንዲሁም የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የማዕድን ዘርፉን ከምድር ውስጥ አውጥቶ ወደ ፋብሪካዎች ግብዓትነት የመቀየር ራእይን እያሳካ ይገኛል። በክልላችን የሚገኙ ማዕድናት ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑ እየተገለፀ በመሆኑ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል፦

✨ የከበሩ ማዕድናት (ወርቅ እና ውብ ኦፓል)፦ የውጭ ምንዛሪ ግኝታችንን ከማሳደግ ባለፈ፣ የጌጣጌጥ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪን በክልላችን በማጠናከር ለበርካታ ወጣቶች ክህሎትና የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ።

🏭 የከሰልና የኢነርጂ ማዕድናት፦ በክልላችን እየተስፋፉ ላሉት ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና የኃይል ማመንጫዎች ዋነኛ የኃይል ምንጭ በመሆን፣ ቀደም ሲል ለውጭ ከሰል ግዢ የሚወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በአገር ውስጥ ያስቀራሉ።

🧱 ቤንቶናይት፣ ሌዘር ክሌይ እና የኢንዱስትሪ ማዕድናት፦ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ለሴራሚክስ፣ ለግንባታ እና ለኬሚካል ፋብሪካዎች የማይተኩ የአገር ውስጥ ግብዓቶች ናቸው።

🏗️ የብረት ማዕድን ክምችቶች፦ የሀገራችንን የመሠረተ ልማት እና የከባድ ኢንዱስትሪ ሽግግር በራስ አቅም ለመደገፍ የጀርባ አጥንት ናቸው።

🏭 ከጥሬ ዕቃ ሽያጭ ወደ እሴት ጭማሪ (Value Addition)

የክልላችንን የብልጽግና ጉዞ የምናረጋግጠው ማዕድናትን በጥሬነታቸው በመሸጥ ሳይሆን፣ በቴክኖሎጂ አቅንተን እሴት ስንጨምርባቸው ብቻ ነው።

ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የማዕድናት ማቀነባበሪያ ማዕከላት ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ምርት አምራችነት ትሸጋገራለች።

በገዛ መሬታችን ያለውን ሀብት በጥራትና በክህሎት ተጠቅመን የውጭ ገበያን በዋጋና በጥራት መፎካከር የሚችል አቅም መገንባት አለብን።

ይህ ሽግግር በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የፀሐይ ኃይል (ሶላር) መሣሪያዎችን እና የሕክምና መሣሪያዎችን ለማምረት ወሳኝ የሆኑ ስልታዊ ማዕድናትን በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋልን ይጠይቃል።

የኢኮኖሚ ነፃነት ማለት በውጭ ምንዛሪ መግዛት ሳይሆን፣ በእጅ ያለን ሀብት በአገር አቅም አምርቶ ለዓለም ማቅረብ ነው!

💡"ወርቅ ሳይፈተን አያበራም፣ ሰው ሳይማር ወይም ሳይሠራ አይከብርም።"

የምንፈልገውን የኢንዱስትሪ ለውጥ የምናመጣው በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በዘርፉ በሰለጠነ የሰው ኃይል ብቻ ነው። የክልላችንን የተፈጥሮ ሀብት በዘመናዊና በዲጂታል አሠራር ፈትሸን፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲያንሰራራ ማድረጉ የጊዜው ትልቁ አገራዊና ክልላዊ ጥሪያችን ነው።

በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን እየሳቡት ያለው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት፣ የማዕድን ዘርፉን እንደ ታላቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ለመጠቀም ያለንን ዝግጁነት ያሳያል። አዲሱ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅም ለዚህ ዘርፍ የሚሰጠው የግብርና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች፣ ባለሀብቶች ወደ ማዕድን ልማትና ማቀነባበሪያ እንዲገቡ ታላቅ ማበረታቻ ሆኗል።

🎯 የኢትዮጵያ ትንሳኤ በወረቀት ላይ የተጻፈ ራዕይ ሳይሆን በየፋብሪካው መጋዘን የሚከማች ምርት፣ በየኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚሰማ የቴክኖሎጂ ምት እና በአማራ ክልል ምድር የተገኙ ማዕድናት በኢትዮጵያዊ ክህሎት ሲቀረጹ የሚታይ ሕያው እውነት ነው!

ኢትዮጵያ በምርቷ ትከበራለች፤ በአማራ ክልል ምድር የተከማቸው ሀብትም ለቀጣዩ ትውልድ የብልጽግና ፋና ሆኖ ይደምቃል። ይህ የኢንዱስትሪ አብዮት የሀገራችንን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራችንን ለዘመናት የሚያጸና የብሥራት ድምፅ ነው።

የክልላችን ማዕድን—ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ብልጽግና! 💪🇪🇹✨

የማዕድን ዘርፍ እና አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ******************(የዕለቱ መልዕክት)በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትንሳኤ ውስጥ ለዓመታት ተኝቶ የነበረው የማዕድን ሀብታችን አሁን ለሀገር ኢኮ...
24/05/2026

የማዕድን ዘርፍ እና አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ
******************

(የዕለቱ መልዕክት)

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትንሳኤ ውስጥ ለዓመታት ተኝቶ የነበረው የማዕድን ሀብታችን አሁን ለሀገር ኢኮኖሚ ትከሻውን እየሰጠ ይገኛል። ከባህላዊ የግብርና አጥር ወጥተን አገራችንን ወደ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ያሏትን የሀብት ክምችት በዕውቀትና በቴክኖሎጂ አቀነባብራ መጠቀም ጀምራለች። በዚህም የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ሀብቷን ወደ ብሔራዊ ምርታማነት የመቀየር አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች።

የማምረቻው ዘርፍ እንደ ወንዝ ውሃ የኢኮኖሚውን አቅጣጫ የሚቀይር ከሆነ ማዕድን ደግሞ የዚያ ወንዝ ምንጭ ነው። አገራችንን የኢንዱስትሪ ፋና ለማድረግ የጀመርነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ የማዕድን ዘርፉን ከምድር ውስጥ አውጥቶ ወደ ፋብሪካዎች ግብዓትነት የመቀየር ግዴታ አለበት።

የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን እያሳዩት ባለው አቅም የማዕድን ዘርፉን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነታችንን መቀነስ የምንችለው አሁን ነው። በገዛ መሬታችን ያለውን ሀብት በጥራትና በክህሎት ተጠቅመን የውጭ ገበያን በዋጋና በጥራት መፎካከር የሚችል አቅም መገንባትም አለብን።

ከውጥን ወደ እውነታ እየተሸጋገርን ባለበት በዚህ ወቅት የማዕድን ልማታችን ከጥሬ ዕቃ ሽያጭ አልፎ እሴት በተጨመረባቸው ምርቶች መደገፍ አለበት። የወርቅ፣ የኦፓል፣ የታንታለም እና የሌሎች ማዕድናት ፍሰት ለሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆን የሚችለው፣ የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በፓርኮቻችን ውስጥ ሲጠናከሩ ብቻ ነው።

የኢኮኖሚ ነፃነት ማለት በውጭ ምንዛሪ መግዛት ሳይሆን በእጅ ያለን ሀብት በአገር አቅም አምርቶ ለዓለም ማቅረብ ነው። ይህ ጉዞ በሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የሉዓላዊነትና የብልጽግና መለኪያ ነው።

የማዕድን ዘርፉን ወደ ኢንዱስትሪ ማቀናጀት ማለት የአገርን የቴክኖሎጂ አቅም መፈተን ማለት ነው። ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ማዕድናት ማቀነባበሪያ ማዕከላት ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ምርት አምራችነት ትሸጋገራለች።

ይህ ሽግግር በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የፀሐይ ኃይል መሣሪያዎችን እና የሕክምና መሣሪያዎችን ለማምረት ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን በአገር ውስጥ መጠቀምን ይጠይቃል።

"ውኃ ካልጠራ አይጠጣም፣ ሰው ካልተማረ አይጠቅም" እንደተባለው የምንፈልገውን የኢንዱስትሪ ለውጥ የምናመጣው በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በዘርፉ በሰለጠነ የሰው ኃይል ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ትንሳኤ በወረቀት ላይ የተጻፈ ራዕይ ሳይሆን በየፋብሪካው መጋዘን የሚከማች ምርት፣ በየኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚሰማ የቴክኖሎጂ ምት እና በምድር የተገኙ ማዕድናት በኢትዮጵያዊ ክህሎት ሲቀረጹ የሚታይ እውነት ነው።

በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን እየሳቡት ያለው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት፣ የማዕድን ዘርፉን እንደ ታላቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ለመጠቀም ያለንን አቅም ያሳያል። የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጁም ለዚህ ዘርፍ የሚሰጠው የግብርና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች፣ ባለሀብቶች ወደ ማዕድን ልማት እንዲገቡ ትልቅ ማበረታቻ ሆኗል።

የማዕድን ሀብታችንን በዘመናዊ አሠራር ፈትሸን፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲያንሰራራ ማድረጉ የጊዜው ትልቁ አገራዊ ጥሪ ነው።

ኢትዮጵያ በምርቷ ትከበራለች፤ በምድሯ የተከማቸው ሀብትም ለቀጣዩ ትውልድ የብልጽግና ፋና ሆኖ ይደምቃል። ይህ የኢንዱስትሪ አብዮት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራችንን ለዘመናት የሚያጸና የትንሳኤ ብሥራት ነው።

በየደረጃው ያለው የማዕድን ምርታችን ሲጎለብት ኢትዮጵያ የራሷን የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት ታውጃለች። ነገ የምናያት ኢትዮጵያ በምርቷ የምትኩራራ፣ በሀብቷ የምትበለጽግ እና ለአፍሪካ የብልጽግና ፋና የምትሆን አገር ናት።

የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

Ethiopian Broadcasting Corporation #ማዕድን #ኢኮኖሚ

መደመር አንቀጽ ኢትዮጵያ በብዙ ማዕድናት የታደለች ብትሆንም፤ አብዛኛው የማዕድን ሀብት ገና ወደ ልማት አልተሸጋገረም። እንደ ታንታለም ያሉ የከበሩ ማዕድናት የምርት ጅማሬዎች አሉ። እንደ ወር...
24/05/2026

መደመር አንቀጽ

ኢትዮጵያ በብዙ ማዕድናት የታደለች ብትሆንም፤ አብዛኛው የማዕድን ሀብት ገና ወደ ልማት አልተሸጋገረም። እንደ ታንታለም ያሉ የከበሩ ማዕድናት የምርት ጅማሬዎች አሉ። እንደ ወርቅ ባሉት ላይ ደግሞ በተወሰነ ደረጃ ጥሩ እንቅስቃሴ ጀምረናል። ሰፋፊ ሽፋን ያለባቸው እንደ ነዳጅና ፖታሽ ያሉ ሀብቶቻችን ገና ብዙ መሥራት የሚጠበቁብን ናቸው።

ሀገራችን ለነዳጅ ዘይት ግዢ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታወጣለች። ለማዳበሪያ ዋነኛው ግብአት የሆነውን ፖታሽን በከፍተኛ ደረጃ ታቅፋ፣ ለማዳበሪያ ቢልዮን ዶላሮች ትከሰክሳለች። የተፈጥሮ ሀብታም፣ የልማት ድኻ መሆናችን ያስቆጫል። ተገድደን ሳይሆን ወደን ፈቅደን ድኻ የሆንን ይመስላል።

ሌላው የሀገራችንን የመልማት ዕምቅ ዐቅም የሚወስነው የኃይል ሀብታችን ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ትልቅ ኃይል የማመንጨት ዕምቅ ዐቅም አላት። ከዚህ ዕምቅ ዐቅም ውስጥ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች ብቻ ከፍተኛ ኃይል ማመንጨት ትችላለች፤ ይህም ሀገራችንን በዚህ ረገድ ተመራጭ ያደርጋታል። ከዚህም ባለፈ ከነዳጅና ከጋዝ ተጨማሪ ኃይል የማመንጨት ዕድሎች አሏት።

የመደመር መንግሥት
ገጽ 51

Ethiopian Broadcasting Corporation #ማዕድን

ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም እየተቀየረ ነው።
24/05/2026

ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም እየተቀየረ ነው።

ለውብ የቤት ማስዋቢያዎች የምንጠቀመው ሴራሚክ ለብዙዎቻችን የቅንጦት እና በዶላር የሚገዛ የውጭ ምርት ነበር። ዛሬ ግን ይህ ታሪክ ተቀይሯል፤ ኢትዮጵያ የገዛ ምድሯን ማዕድን አቅልጣ ቤ....

23/05/2026
📌 አዲስ የምስራች ከደብረ ማርቆስ፦ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚያነቃቃው ግዙፉ "ዳት ግራናይት ፋብሪካ" የሙከራ ምርት ጀምሯል!-------------------------ግንቦት 1...
23/05/2026

📌 አዲስ የምስራች ከደብረ ማርቆስ፦ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚያነቃቃው ግዙፉ "ዳት ግራናይት ፋብሪካ" የሙከራ ምርት ጀምሯል!
-------------------------
ግንቦት 15/2018 ዓ.ም ፦ ለከተማዋም ሆነ ለሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ አዲስ ተስፋ የሰነቀው፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው ግዙፉ “ዳት ግራናይት ፋብሪካ” ግንባታውንና የቴክኖሎጂ ተከላውን አጠናቆ በይፋ ወደ ሙከራ ምርት ተሸጋግሯል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ለአካባቢው ኢኮኖሚ መነቃቃት ብቻ ሳይሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኮንስትራክሽን ግብዓት ራሳችንን ለመቻል ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

የፋብሪካው መከፈት ይዞአቸው የመጣቸው 4 ዋና ዋና ስልታዊ ጥቅሞች፦

1. የሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር 🛠️

ፋብሪካው ለደብረ ማርቆስ ከተማና ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊና ዘላቂ የሥራ ዕድል ይዞ መጥቷል። ከዚህም በላይ፣ የዘርፉን ዘመናዊ አሰራርና የቴክኖሎጂ እውቀት ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች በማስተላለፍ (Technology Transfer) ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

2. የውጭ ምንዛሬን ማዳንና የገቢ ምርትን መተካት (Import Substitution) 📉

ሀገራችን ለኮንስትራክሽን የሚሆኑ የዓለትና የግራናይት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት በየዓመቱ የምታወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል። የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የኢኮኖሚ ጫናውን በከፍተኛ ሁኔታ ያቃልላል።

3. የኮንስትራክሽን ዘርፉን የጥሬ ዕቃ እጥረት መቅረፍ 🏗️

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ላይ ትልቅ ማነቆ የሆነውን የጥሬ ዕቃ እጥረትና የዋጋ ንረት በመቅረፍ፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች በጥራትና በወቅቱ እንዲጠናቀቁ አስተማማኝ ግብዓት ያቀርባል።

4. የደብረ ማርቆስን የኢንዱስትሪ ማዕከልነት ማሳደግና የወጪ ንግድ (Export) 🌍
ፋብሪካው የሙከራ ምርቱን በስኬት አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት ሲሸጋገር፣ ምርቶቹን ለጎረቤት ሀገራትና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመላክ ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

💡 መልዕክታችን፦

እንዲህ ያሉ የሀገር በቀል ሀብትን የሚያለሙና የቴክኖሎጂ አቅምን የሚያሳድጉ ግዙፍ ማምረቻ ፋብሪካዎች መነሳታቸው፣ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ከማሳደጉም በላይ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ያጠናክራሉ። ለፕሮጀክቱ መሳካት አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

23/05/2026
ፋብሪካው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ነው። -----------------------ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም :- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕ...
23/05/2026

ፋብሪካው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ነው።
-----------------------
ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም :- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሞጆ ከተማ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካን መርቀዋል።

‎በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ መሰረት ልማቱ በ300ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክ እና የፖርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው ። ከዕቅድና መሬት ዝግጅት እስከ ሙሉ ሥራ ማስጀመር የወሰደው ጊዜ ዘጠኝ ወራት ብቻ ነው።

‎​በአሁኑ ወቅት 60x60 የሴራሚክ ንጣፎችን በስፋት ማምረት የጀመረው ይህ ፋብሪካ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የምርት ዓይነቶቹን በማስፋት የ80x80፣ 60x120፣ 70x140 እና 80x160 መጠን ያላቸውን የንጣፍ ዓይነቶችን፣ የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የፖርሲሌን ምርቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋዕለ ነዋይ የወጣበት ይህ ፋብሪካ፣ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ክንውን ነው።

‎ለ​ፋብሪካው ምርት የሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች 80 በመቶ የሚኾነው ከፋብሪካው በ100 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ይህም ሙሉ በሙሉ የተቀናጀ እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተሳሰረ የአቅርቦት ሰንሰለት ፈጥሯል።

ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ባላፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ከ4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን በቻለችበት በዚህ ወቅት የግራንዴር ሴራሚክ መከፈት የውጭ ምርት ጥገኝነትን የሚቀንስ ብቻ ሳይኾን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንድትኾን የሚያስችላት መኾኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
@አሚኮ

23/05/2026

Address

University Road
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ:

Share