Ethiopia Electric utility Bahir Dar Region

Ethiopia Electric utility Bahir Dar Region Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopia Electric utility Bahir Dar Region, Government Organization, Bahir Dar.

የኤሌክትሪክ ሃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን ስለማሳወቅ # # # # # በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚነሱ የኤሌክትሪክ መስመር ምሰሶ ማዘዋወሪያ ስራ ለመስራት መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ...
29/03/2026

የኤሌክትሪክ ሃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን ስለማሳወቅ
# # # # #
በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚነሱ የኤሌክትሪክ መስመር ምሰሶ ማዘዋወሪያ ስራ ለመስራት መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ ቀበሌ 13 ማለትም ካቶሊክ፤ ሳሚ ቁርጥ ቤት አካባቢ፤ባታ ፤ ሀይሌ ት/ቤት እና አምሳሉ ሜዳ አካባቢ፤ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ ኦክስጅን ማምረቻ፤ የፊስቱላ ታሚሚዎች ህክምና መስጫ እና በተጠቀሱት አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ የሚዉል መሆኑን በአክብሮት እያሳወቅን ክቡራን ደንበኞቻችን የታቀደው ስራ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እስከሚገናኝ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ እየጠየቅን በምርት እና በጥሬ እቃዎች ላይ ብክነት እንዳይከሰት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ወይም ሌላ የአማራጭ ሀይል እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናሳውቃለን።
የባህር ዳር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የአሜሪካ የንግድና ልማት ኤጀንሲ (USTDA) በኃይል ዘርፍ ዘመናዊነት ላይ ውይይት አካሄዱየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ...
27/03/2026

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የአሜሪካ የንግድና ልማት ኤጀንሲ (USTDA) በኃይል ዘርፍ ዘመናዊነት ላይ ውይይት አካሄዱ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመው ከአሜሪካ ንግድና ልማት ኤጀንሲ (USTDA) የልዑካን ቡድን ጋር በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ የኃይል ማከፋፈያ ስርዓቱን ለማጠናከርና የኤሌክትሪክ መረቡን (Grid) ዘመናዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ዕድሎች ላይ ከኤጀንሲው ጋር ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

በውይይቱም የኃይል ማከፋፈያ ስርዓታችንን ማጠናከር በሚቻልባቸው እድሎች፣ የኤሌክትሪክ መረብን (grid) ዘመናዊ ማድረግ፣ እንዲሁም እንደ ስማርት ሜትር (smart metering)፣ የኃይል ማከማቻ (energy storage) እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ባሉ የፈጠራ መፍትሄዎች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት መደረጉን ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል፡፡

ኢ/ር ጌቱ አክለውም፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና ለሀገሪቱ ዘላቂ የኃይል አቅርቦት ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ከኤጀንሲው ጋር የሚመሰረተው ጠንካራ አጋርነት በውይይቱ የተነሱትን ሃሳቦች ወደ ተጨባጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ ፕሮጀክቶች እንደሚቀይራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የትራንስፎርመር ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ላይ የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ተካሄደ$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎቱን ይበ...
05/03/2026

የትራንስፎርመር ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ላይ የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ተካሄደ
$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎቱን ይበልጥ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ከጀርመን ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የተፈረመው ከአለም አቀፍ የጀርመን ተራዶ ድርጅት Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit (GIZ) እና ካርልስሩሄ የቴክኖሎጂ ተቋም Karlsruhe Institute of Technology (KIT) ጋር ነው፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እየጨመረ የመጣውን የሃይል ፍላጎት መሸከም የሚችል የኤሌክትርክ መሰረተ ልማትን ለማዘመን አዳዲስ አሰራሮች በመተግበር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ከአጋር አካላት ጋር መሥራት የዲስትሪቡሽን ኔትዎርክን ለማጠናከር እንዲሁም ትራንስፎርመሮችን ጨምሮ ተቋሙ ያሉትን ንብረቶች ለመከታተል እና ለመቆጣጠር በተጨማሪም ኪሳራን ለመቀነስ እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡

አለም አቀፍ የጀርመን ተራዶ ድርጅት (GIZ) እና ካርልስሩሄ የቴክኖሎጂ ተቋም (KIT) ተወካይ በበኩላቸው ተቋሙ ጋር ለመስራት ዕድሉን በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ የኃይል ስርጭቱን ወደ ዘመናዊ የዲጂታል አስተዳደር ለማሻሻል የሚያስችል አስፈላጊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

ቴክኖሎጂው ወቅቱን የጠበቀ የዲስትርቡሽን ትራንስፎርመር ደህንነት መረጃ በርቀት በመሰብሰብ ችግር ከመከሰቱ በፊት ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡

በፕሮጀክት ሥራው በመጀመሪያ ደረጃ በአዲስ አበባ በሚገኙ ትራንስፎርመሮች ላይ በሙከራ ደረጃ የሚተገበር ሲሆን፣የቴክኖሎጂው አዋጭነት እና ውጤታማነት ከተረጋገጠ በኋላ በሌሎች ከተሞችና ክልሎች የሚተገበር ይሆናል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የኃይል አቅርቦትን አስተማማኝነት በማጠናከር የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ፣ የትራንስፎርመር ጉዳትን ለመቀነስ እና የሀገራችንን የኃይል ዘርፍ ወደ ዲጂታል ዘመን ለመውሰድ ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ይህንን   ሰምተዋል? ወርሃዊ ንባቤን አልተነበበልኝም፤ ቆጣሪ አንባቢ ቀረብኝ የሚል ቅሬታን የሚያስቀር ቴክኖሎጂ መተግበር ጀመረ👇   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ ደንበኞቹን...
21/02/2026

ይህንን ሰምተዋል? ወርሃዊ ንባቤን አልተነበበልኝም፤ ቆጣሪ አንባቢ ቀረብኝ የሚል ቅሬታን የሚያስቀር ቴክኖሎጂ መተግበር ጀመረ👇

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ ደንበኞቹን የእጅ ስልካቸውን ተጠቅመው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ንባባቸውን ከቤታቸው ሆነው የሚያስገቡበት የቴሌግራም ቻት ቦት () የመኩራ ትግበራ በተመረጠ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ይፋ አደረገ፡፡

የሙከራ ትግበራው (Pilot test) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን መተግበር ጀምሯል፡፡

ማዕከሉ ከ16 ሺህ በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ያሉት ሲሆን፤ እነዚህ ደንበኞች በያዝነው ወር ከየካቲት 13 እስከ 23 ድረስ የፍጆታ ንባብን በቀላሉ ቤታቸው ሆነው በeeuchatbot ቴሌግራም ተጠቅመው ለተቋማችን እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

👉 ቁጥር 4 አገልግሎት መስጫ ማዕከል የሚገኘው
➡️ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

👉 ማዕከሉ የሚያካልላቸው አካባቢዎች፡-

1️⃣ ከእንቁላል ፋብሪካ አደባባይ በሩፋኤል ቤተክርስቲያን አድርጎ፣ በጉለሌ ወረዳ 9፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በሚሊኒየም ሰፈር፣ በሸጎሌ አካባቢ፤

2️⃣ ከሚሊኒየም ሰፈር፣ በዊንጌት፣ በጴጥሮስ ቤተ-ክርስቲያን፣ በኮልፌ አጠና ተራ፣ በፓሪስ ካፌ፣ በ18 መብራት ኃይል ፊት ለፊት፣ በሻንቅላ ወንዝ በአማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን መሻገሪያ ድልድይ፣

3️⃣ በመሳለሚያ ወደ 18 አደባባይ፣ በደጉ ሆቴል ወደ ሰፈረ ሰላም ድልድይ፣ በታይዋን፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ በአበበ ቢቂላ፣ በአዲሱ ሚካኤል አካባቢ፣ በጨው በረንዳ፣ በእስላም መቃብር፣ በእንቁላል ፋብሪካ እና በጳውሎስ አካባቢ፣

👉 () ወርሃዊ የፍጆታ ንባብ በቀላሉ መላክ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

➡️ የፍጆታ ሂሳብን በወቅቱ ለመፈፀም
➡️ ወርሃዊ ንባቤን አልተነበበልኝም የሚልን ቅሬታ ለማስቀረት፤
➡️ ቆጣሪ አንባቢ ቀረብኝ የሚል ቅሬታን ለማስቀረት፣
➡️ ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ

👉 ቀጣይ ትግበራ

የሙከራ ትግበራው (Pilot test) የሚያመጣቸውን ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን በመለየት በቀጣይ በሌሎች ሪጅኖችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚተገበር ይሆናል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈጽም የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በነፋስ መወጫ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመር ተሸካሚ የብረት...
06/02/2026

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት ሲፈጽም የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በነፋስ መወጫ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ስርቆት ሲፈፅም የነበረ ግለሰብ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

መካከለኛ መስመሩ ለነፋስ መውጫ ከተማ ውሃ አገልግሎት፣ ለታች ጋይንት፣ ለክምር ድንጋይ እና አካባቢው አገልግሎት የሚሰጥ መጋቢ መስመር ነው፡፡

የባህርዳር ሪጅን ከአካባቢው መስተዳድር አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እና የአካባቢው የፀጥታ አካላቱም ባደረጉት ክትትል ከህገ ወጥ ግለሰቦች መካከል አንዱን ግለሰብ የነፋስ መውጫ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተቋማችንን ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችን በመቀላቀል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ወዲያውኑ ያግኙ!!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507

266 ሺህ 916 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏልበ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወር 266 ሺህ 916 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃ...
05/02/2026

266 ሺህ 916 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል

በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወር 266 ሺህ 916 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመው ዛሬ በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡

የአዲስ ኃይል ማገናኘት አፈፃፀሙም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ13.2 በመቶ ብልጫ መኖሩን በመግለጫቸው የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው አዲስ ኃይል ከተገናኘላቸው ደንበኞች መካከል 93.3 ከመቶ የድህረ ክፍያ እንዲሁም 6.7 ከመቶ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ተደረሽነትን እውን ለማድረግ ከዋናው ሃይል ቋት (ግሪድ) 47 የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉን በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ከዋናው ሃይል ቋት (ግሪድ) የራቁ ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራ ሥራ 16 ቀበሌዎችን በኦፍ ግሪድ ከፀሃይ ኃይል ማመንጫ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከዋናው ግሪድና በሚኒ ግሪድ ወይም ከፀሐይ ኃይል በአጠቃላይ 63 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወር ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ እንዲሁም የማያገለግሉ ንብረቶችን በማስወገድና ከልዩ ልዩ ገቢ በአጠቃላይ 52.26 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ 96 ከመቶ ማስመዝገብ መቻሉን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ባለፉት ወራት ከ52 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማሻሻያና መልሶ ግንባታ ስራዎች መከናወናቸውን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት ኤሌክትሪክ የተገናኘላቸው ደንበኞችን ጨምሮ የተቋማችን የደንበኞች ቁጥር 5.46 ሚሊዮን በላይ መሆኑንም ኢንጅነር ጌቱ ተናግረዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቹ በርካታ አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዋና ሥራ አስፈፃሚው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ከፍኖተ ሰላም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተላለፈ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት!ለፍኖተ ሰላም ከተማነዋሪዎችና ለክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ፤ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤታችን በከተማችን የሚገ...
02/02/2026

ከፍኖተ ሰላም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተላለፈ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት!

ለፍኖተ ሰላም ከተማነዋሪዎችና ለክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ፤

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤታችን በከተማችን የሚገኘውን የሰብስቴሽን አቅም ለማሳደግና ጥራት ያለው የኃይል አቅርቦት ለማቅረብ ሰፊ የሥራ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የግንባታ ሥራው በሚጀመርበት ወቅት በሳምንት አራት ቀናት (እሁድ፣ ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ) ከጠዋቱ 2:00 እስከ 10:00 ሰዓት በአለው ሙሉ በሙሉ የኃይል መቋረጥ እንደሚኖር እናሳውቃለን።

ስለሆነም ጀነሬተር ያላችሁ የግልና የመንጎስት ተቋማት እና ግለሰቦች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

የወፍጮ አገልግሎት ተጠቃሚዎችና ሌሎች አስቸኳይ ሥራ ያላቸው ደንበኞች ፕሮግራማችሁን ከወዲሁ እንድታስተካክሉ በጥብቅ እናሳስባለን።

#ማሳሰቢያ፦ ሥራው የሚጀምርበትን ትክክለኛ ቀን በቅርቡ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን፣ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ከወዲሁ ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ አቶ ተስፋዬ ቦጋለ የፍኖተ ሰላም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ መረጃውን ለፍኖተ ሰላም ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አድርሰዋል።

Finote Selam City Communications

29/12/2025

🇪🇹የኢነርጂ ፍጆታ ቢል እንዴት አንደሚያሰሉ ያውቃሉ? በምሳሌ እንመልከተው👇

💡አንድ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ደንበኛ በታህሳስ በወር 2018 ዓ.ም 450 ኪዋት ሰዓት የሚጠቀም ቢሆን፤ አዲሱ በተሻሻለው ታሪፍ 4ኛው ዙር (ከጥቅምት - ታህሳስ/2018 የተተገበረው) በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት ብር 5.0593 ላይ ያርፋል፡፡

🔌 የክፍያው ስሌት እንመልከት

➡️ የኢነርጂ ፍጆታ ሂሳብ = 450*5.0593= ብር 2,276.69

➡️ የአገልግሎት ሂሳብ፡-
ሀ) የድህረ ክፍያ ቆጣሪ = ብር 47.7
ለ) የቅድመ ክፍ ቆጣሪ = ብር 16.6

🔌 ድምር:

💡የድህረ ክፍያ ቆጣሪ = 2,276.69+47.7 = 2,324.39
💡የቅድመ ክፍ ቆጣሪ = 2,276.69+16.6 = 2,293.29

➡️ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%)
ሀ) የድህረ ክፍያ ቆጣሪ =2,324.39*0.15= ብር 348.6585
ለ) የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ =2,293.29*0.15= ብር 343.9935

➡️ የተቆጣጣሪ ባለሥልጣን (0.5%)
ሀ) የድህረ ክፍያ ቆጣሪ =2,324.39*0.005= ብር 11.62195
ለ) የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ= 2,293.29*0.005= ብር 11.46645

📺 የቴሌቪዥን ግብር =10.00

🔌 ጠቅላላ ድምር

💡የድህረ ክፍያ ቆጣሪ = ብር 2,694.51
💡የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ= ብር 2,658.75 ይሆናል ማለት ነው።

💵 በዚህ መልኩ ማንኛውን የመኖሪያ ቤት ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኛ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳቡ በቀላሉ በዚህ መልኩ አስልቶ ማወቅ ይችላል ማለት ነው፡፡

🪙 መረጃዎቻችን ይቀጥላሉ፡፡

#ይጠብቁን !

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

22/12/2025

በኃይልና በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት ሲመለከቱ በ908 የፅሁፍ መልዕክትያሳውቁን!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካትና የውስጥ አሠራሩን ለማዘመን በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል በኃይልና በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀል ጥቆማ ለመቀበል የሚያስችል የመልዕክት መቀበያ አጭር ቁጥር በሥራ ላይ አውሏል፡፡

በኃይልና በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት ወንጀል ደንበኞችን ለኃይል መቆራረጥ ተቋሙንም ለኪሳራ እየዳረገ ይገኛል፡፡ ወንጀሉን ለመከላከል ደግሞ ተቋሙ ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር የውድ ደንበኞቻችን ድጋፍ ወሳኝ ነው!

ውድ ደንበኞቻችን በየትኛውም ቦታ የኃይልና መሠረተ-ልማት ስርቆት ሲፈፀም ካስተዋሉ በ908 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ጥቆማዎን በመስጠት የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፤ የሁላችንም ሐብት የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይልና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ከስርቆት እንከላከል፡፡

የተቋማችንን ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችን በመቀላቀል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ወዲያውኑ ያግኙ!!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507

22/12/2025

💡ለመኖሪያ ቤት አዲስ ኃይል ለማግኘት የቤት ካርታ እንደማያስፈልግ ያውቁ ኖሯል?📍

✅ ለመኖሪያ ቤትዎ አዲስ ኃይል ለማግኘት ሲፈልጉ ምን ማሟላት ይጠበቅብዎታል?

👉 ማመልከቻ/ቅጽ መሙላት፣
👉 የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ ፓስፖርት/ብሄራዊ መታወቂያ፣
👉አንድ የወቅቱ ጉርድ 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ፣
👉የውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሥራው ደረጃውን ጠብቆ የተከናወነ መሆኑን እና ሀላፊነት የሚወስድ መሆኑን ድርጅቱ ባዘጋጀው ቅጽ ላይ የተፈረመ አባሪ ሰነድ፣
👉የኪራይ ቤት ከሆነ ቤቶቹን ለማስተዳደር ሥልጣን ከተሰጠው አካል ሃላፊነት መውሰድ የተጻፈ የውክልና ደብዳቤ፣
👉በአከራይ በኩል ተከራይ ቆጣሪ በስሙ አስገብቶ እንዲጠቀም የተሰጠ ህጋዊ ውክልና፣ ያልተከፈለ እዳ ቢኖር አከራይ ለመክፈል የተፈረመ የውል ግዴታ ሰነድ፣

የተቋማችንን ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችን በመቀላቀል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ወዲያውኑ ያግኙ!!

[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507

22/12/2025

💡ይህን ያውቁ ኖሯል? 💡

✅በተደጋጋሚ ዝቅተኛ የሆነ የፍጆታ ሂሳብ መክፈል ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ የሚዳርግ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ እንንገርዎ!!

👉ዝቅተኛ የሆነ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ መፈፀም ለተጠራቀመ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ይዳርጋል፡፡

👉ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች የቆጣሪ ንባብ ስህተት ሲያጋጥም ከተጠቀሙበት በታች ወይም በላይ ሊከፍሉ ይችላሉ፤ይህም ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ እንዲመጣ ምክንያት ይሆናል፡፡

👉ስለሆነም ውድ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ተደጋጋሚ ጊዜ ዝቅተኛ የሆነ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ከመጣባችሁ ለተጠራቀመ የፍጆታ ክፍያ ስለሚዳርግ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመሄድ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡

የተቋማችንን ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችን በመቀላቀል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ወዲያውኑ ያግኙ!!

[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507

25/10/2025

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Electric utility Bahir Dar Region posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share