Amhara Information Service

Amhara Information Service For whatever it's worth, never fall a victim of the struggle and when it so happens remain a soldier.

እውነተኛ መሪዎችን እንጂ ጉዳይ አስፈጻሚ ምስለኔዎችን የሚቀበል ሕዝብ የለም።ከሰሞኑ በሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የምክክር ሂደት ላይ እውነተኛ የሕዝብ ልጆች መሪዎቻችን ፥ የአክራሪ የፖለቲካ ቡ...
26/08/2026

እውነተኛ መሪዎችን እንጂ ጉዳይ አስፈጻሚ ምስለኔዎችን የሚቀበል ሕዝብ የለም።

ከሰሞኑ በሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የምክክር ሂደት ላይ እውነተኛ የሕዝብ ልጆች መሪዎቻችን ፥ የአክራሪ የፖለቲካ ቡድኖችን ፍላጎት ለመላው ኢትዮጵያዊ ስላጋለጡ ጥርስ እንደተነከሰባቸው የውስጥ መረጃ ደርሶናል።

በምክክር ሂደት የሃሳብ ልዩነት የሚጠበቅ ቢሆንም እኛ ያልነው ካልሆነ ሃገር የሚባል ወይም የጋራ ተጠቃሚነት የሚባል መርህ ገደል ይግባ የሚለው አክራሪ ብሔረተኛና ቆሞ ቀሩ የፖለቲካ ቡድን የዓላማየ እንቅፋት ናቸው ያላቸውን ጀግኖች መሪዎቻችንን ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲመደቡ በማድረግ አዳዲስ ምስለኔዎችን በቦታቸው ለመመደብ ግፊት እያደረገ ነው።

ይህ ቡድን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተደምሮ ሃገሩን የሚያሻግርበትን የሃገረ መንግሥት ግንባታ እውን በማድረግ ላይ ያለው ብልጽግና ፓርቲና የመንግሥት መዋቅርን እንደ ሽፋን በመጠቀም፤ ስሁት የሆነውን የቡድን ፍላጎቱን ለማሳካት የሚያስችል እድል ለመፍጠር በክልሉ መንግሥት አስተባባሪዎች ላይ ምስለኔዎችን ለመመደብ የሚያደርገው ጥረት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።

ክልላችን የአክራሪ ብሔረተኞችን ፍላጎት የሚያስፈጽሙ፥ ተለጣፊና አድርባይ ምስለኔዎችን የሚቀበሉበት ትከሻ የላቸውም።

እየተገነባ ያለውን ጠንካራ ሃገረ መንግሥት በጠንካራ ተቋማትና መሪዎች በማስቀጠል ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ለማውረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአማራ ክልል መሪዎች ታምነው የሚቀጥሉ እንጂ ለእኔ ብቻ የሚለውንና system sabotage ውስጥ እየዳከረ የሚገኘውን ንዑስ አንባገነን ቡድን ለማንገሥ የሚሠሩ አይደሉም። ሕዝባችንም ፈጽሞ አይቀበለውም።

18/08/2026

የአማራ ክልል አመራር አንድነት ከትናንት ስህተት የተማረና በሴራ የማይሸረሸር ጥንካራ ነው

​ታሪክ አላፊ ቢሆንም የእውነትና የፅናት አሻራ ግን ዘላቂ ነው። ቀደም ሲል በነበረው ስርዓት በእነ ዳንኤል ብርሃኔና በእነ ሰናይት መብራቱ አጥፊ ሚና አመራሩን እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ለማድረግ፣ ከህዝብ ለመነጠልና ያልተገቡ እኩይ ፍላጎቶችን ለማስረፅ የተሄደበት መንገድ በግልፅ ይታወሳል። የትናንቱ የከፋፋይነትና የሴራ ፖለቲካ ያሳየን ትልቅ ትምህርት ቢኖር ህዝብንና አመራርን የመነጣጠል እኩይ ተልዕኮ መጨረሻው ውድቀት ብቻ መሆኑን ነው።

​ዛሬ ደግሞ የትናንቱን የወያኔ የታሪክ ስህተት በመድገም፣ ፀረ-ብልፅግና የሆኑ አክቲቪስቶች ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የህዝባችንንና የእንቁ አመራሮቻችንን አንድነት ለመሸርሸር የሚደክሙት ድካም የህልም ሩጫ ከመሆን አይሻገርም። የወያኔን የቆየ ከፋፋይ ስልት መልሶ በመጠቀም የክልሉን አመራር ህብረት ማፍረስ ይቻላል ብሎ ማሰብ በፍጹም የማይሳካ የፖለቲካ ስሌት ነው።

​የአማራ ክልል አመራር ከትናንት ውደቀቶችና ስህተቶች የተማረ፣ የታሪክን ትምህርት በአግባቡ የተቀበለ እንጂ ዳግም ለሴራ የሚንበረከክ አይደለም። አመራራችን በእውነትና በህዝብ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አንድነት ያለው፣ ለህዝቡ ልማትና ሰላም ሌት ተቀን የሚተጋ እንጂ በውጭ አክቲቪስቶች ባዶ ጩኸትና የሀሰት ወሬ የሚናጋ ስላልሆነ፣ ከእውነት የራቀ ወሬ በመንዛት አመራሩን ከህዝብ እንዲሁም ከእርስ በእርሱ ለመነጠል የሚደረገው ሙከራ ሁሉ ከንቱ ድካም ሆኖ ይቀራል።

​በመሆኑም መላው ህዝባችን የአመራሮቻችን አንድነትና ውህደት ለክልላችን ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና መረጋገጥ ጠንካራ መሰረት መሆኑን ተረድቶ፣ ትናንት ያልሰራው የከፋፋይነት ስልት ዛሬም ቢሆን አይሰራም፤ የአማራ ክልል አመራርና ህዝብ አንድነት በሴራ አይሸረሸርም፣ በሀሰት ፕሮፖጋንዳም አይናጋም። አንድነታችን የጥንካሬያችን፣ ህብረታችን ደግሞ የድላችን ምስጢር ሆኖ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ባህር ዳርየ❤  Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
27/05/2026

ባህር ዳርየ❤

Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ

ብልጽግና በእነዚህ ጀግኖች ስለተወከለ ብቻ ሳይሆን ሕዝባችንም የልብ አውቃ የሆኑትን እነዚህን ልጆቹን ስላገኘ ኩራት ተሰምቶታል። ባህር ዳር ልጇቿን እንዲህ አክብራለች❤
26/05/2026

ብልጽግና በእነዚህ ጀግኖች ስለተወከለ ብቻ ሳይሆን ሕዝባችንም የልብ አውቃ የሆኑትን እነዚህን ልጆቹን ስላገኘ ኩራት ተሰምቶታል።
ባህር ዳር ልጇቿን እንዲህ አክብራለች❤

26/05/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር ❗️ማለት❓✅ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት ✅ የዜጎች ክብርና ተጠቃሚነትነት እውን የሆነባት ✅ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች የአፍሪካ ታላቅ ፤ የዓለምም ታላ...
26/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር ❗️ማለት❓

✅ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት
✅ የዜጎች ክብርና ተጠቃሚነትነት እውን የሆነባት
✅ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች

የአፍሪካ ታላቅ ፤ የዓለምም ታላቅ ሃገር ኢትዮጵያ በብልጽግና ፓርቲ እውን ትሆናለች።

ኢትዮጵያ ትሻገራለች- ወደ ተምሳሌት ሃገር የምታደርገው ግስጋሴም ይቀጥላል።

ብልፅግናን ይምረጡ! ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው።

ዛሬና ነገ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ የቅስቀሳ ቀናትን አስመልክቶ የክልላችን ሕዝብ ለፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያለውን ፍላጎትና ተነሳሽነት እያሳየ ይገኛል። ምርጫ የዜግነት ኀላፊነት ...
25/05/2026

ዛሬና ነገ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ የቅስቀሳ ቀናትን አስመልክቶ የክልላችን ሕዝብ ለፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያለውን ፍላጎትና ተነሳሽነት እያሳየ ይገኛል።

ምርጫ የዜግነት ኀላፊነት መሆኑን የተረዳው ሕዝባችን ፍላጎቱን በአደባባይ እየመሰከረ ይገኛል። ኢትዮጵያዊነት በምርጫው ቀንም በድምጽ ይረጋገጣል።

ብልፅግናን ይምረጡ! ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው።

ብልጽግናን መምረጥ ማለት ለእውነተኛ ልማት የሚሠራን መንግሥት መምረጥና ማቋቋም ማለት ነው። ብልጽግና የማይደፈሩ የልማት ህልሞችን ከህልምነት አውጥቶ እውን ያደረገ ፓርቲ ነው ስለሆነ።የሕዳሴው...
23/05/2026

ብልጽግናን መምረጥ ማለት ለእውነተኛ ልማት የሚሠራን መንግሥት መምረጥና ማቋቋም ማለት ነው። ብልጽግና የማይደፈሩ የልማት ህልሞችን ከህልምነት አውጥቶ እውን ያደረገ ፓርቲ ነው ስለሆነ።

የሕዳሴው ግድብ የጥቅመኞች መደበቂያ ዋሻ ሁኖ ነበር ፤ ብልጽግና ግን አጠናቆ በማስመረቅ ኢትዮጵያውያንን ከውርደት አድኗል። ሉዓላዊነታችንም ከፍ አድርጓል።

ለዘመናት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ የነበረው የነዳጅ ሀብታችንን የመጠቀም ጅማሮ እውን የሆነው በብልጽግና ነው። አሁንም በተሟላ አቅም ይቀጥላል።

በኢትዮጵያ አርሶ አደር ኃላቀር የአስተራረስ ዘዴ ላይ የተመሰረተ ኋላቀር ኢኮኖሚ ይዘን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ ብዙ አሰርት ዓመታት የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ የምናስገባ ምስኪኖች ነን። በየዓመቱ የምንደጉመው ገንዘብ ሳይቆጠር። ... ብልጽግና ይህንን አክሳሪ ታሪክ በመፋቅ ሃገራችን የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ባለቤት እንድትሆን እየሠራ ነው።

በታሪካዊ ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሃብቶቿ የቱሪዝም ሃብቷን ማስተዋወቅ የተሳናትና ከቱሪዝምና ከባህል ሃብታችን ልናገኝ የሚገባንን የምጣኔ ሃብታዊ ጥቅም ማግኘት የተሳናት ኢትዮጵያ በገበታ ለሃገር ፣ ገበታ ለሸገር ፣ ... እና ሌሎች የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ኢንሺየቲቮች የኢትዮጵያ ገነትነት በብልጽግና እየተገለጠ ነው።

ተቋማት አገልግሎታቸውን ቴክኖሎጂ መር እያደረጉ ነው። ተቋማት ከቆሻሻ ማከማቻነት ፤ ከተሞች ከተበከለ አየር መፈንጫነት የወጡት በብልጽግና ነው።

ሙሀመድ ጋዳፊ እና ተባባሪዎቹ የአዲስ አበባን የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነት የተጠየፉበትን ዘመን አሳልፈን ፥ በዚህ ትንሽ ዓመት እንዴትፐአፍርሰው ሠሯት ተብሏል። አዲስ አበባ እንደስሟ አዲስ አበባ የሆነችው በብልጽግና ነው።

ምኑ ተነክቶ ....
ብልጽግናን መምረጥ ማለት ለእውነተኛ ልማት የሚሠራን መንግሥት መምረጥና ማቋቋም ማለት ነው።

ብልፅግናን ይምረጡ! ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው።

Address

Giorgis Road
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Information Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Information Service:

Shortcuts

Share