የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት

  • Home
  • የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት

የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት, Government Organization, Gemjabet, .

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት  በቀን 27/02/2018 ዓ.ም በግዥ ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ  ስለ ዳኝነት አከፋፈል ትምህርት ተሰጠ።
06/11/2025

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በቀን 27/02/2018 ዓ.ም በግዥ ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለ ዳኝነት አከፋፈል ትምህርት ተሰጠ።

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት  በቀን 17/02/2018 ዓ.ም በህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለ ሰዓት አከባበር ትምህርት ተሰጠ።
06/11/2025

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በቀን 17/02/2018 ዓ.ም በህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለ ሰዓት አከባበር ትምህርት ተሰጠ።

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት  በቀን 14/02/2018 ዓ.ም በህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለአገልግሎት አሰጣት ትምርት ተሰጠ።
06/11/2025

በአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በቀን 14/02/2018 ዓ.ም በህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለአገልግሎት አሰጣት ትምርት ተሰጠ።

የአን/ጓ/ወረዳ ፋ/ቤት በቀን 25/02/2018አ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ  እንዲሁም የአብክመ የፋ/ቤቶች ማጠናከሪያ አዋጅ ቁጥር 297/2017 አንቀጽ 6/2/ መሠረ...
06/11/2025

የአን/ጓ/ወረዳ ፋ/ቤት በቀን 25/02/2018አ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የአብክመ የፋ/ቤቶች ማጠናከሪያ አዋጅ ቁጥር 297/2017 አንቀጽ 6/2/ መሠረት የአብክመ ጠ/ፋ/ቤት የዳኞች ከለላ በተመለከተ አሳትሞ የላከውን ለአን/ጓ/ወ/ፋ/ቤት ዳኞችና ጉባኤ ተሿሚ እርክክብ ተደረገ።

15/05/2025

የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች አስተዳደር አብይ ጉባኤ አዲስ የዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎችን የሥነ-ምግባር እና የዲሲፕሊን ደንብ አጸደቀ

ባህር ዳር፣ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም (አብክመ ጠ/ፍ/ቤት)

የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በላቀ የዳኝነት አገልግሎት በተምሳሌትነት የሚጠቀስ የዳኝነት ሥርዓት በክልሉ ውስጥ እውን ለማድረግ ሥር ነቀል የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም ገና ከጅምሩ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን ለመምራት የሚያስችሉ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው በክልሉ ምክር ቤት መጽደቃቸው ይታወሳል፡፡ ከእነዚህ ሕጎች መካከል የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ አዋጅ ቁጥር 297/2017 አንዱ ነው፡፡

የአዋጁ መግቢያ (Preamble) የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ዘላቂነት ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳል፡፡ ይህም በክልሉ ውስጥ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት እና ተገማችነት ያለው ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎትን በማስፈን የባለጉዳዮችን እርካታ ለማረጋገጥ እና በማኅበረሰቡ ዘንድ አመኔታ የተቸራቸው ፍርድ ቤቶችን ለመገንባት ያስችላል፡፡

የዳኞች ከለላ እና ጥበቃ በሕግ እውቅና ባለማግኘቱ ምክንያት ጥያቄው አንድ ጊዜ ሞቅ፣ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ የክልሉ ዳኞች የዘመናት አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አዲሱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራር ኃላፊነት ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ በተሰሩ በርካታ የምክክር እና የማሳመን ሥራዎች የዳኞች ከለላ እና ጥበቃ በክልሉ ምክር ቤት ተቀባይነት አግኝቶ በአዋጁ አንቀጽ 6 እና 7 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የዳኞች ከለላ እና ጥበቃ ዋነኛው ዓላማም ነጻ (Independent)፣ ገለልተኛ (Impartial) እና ብቃት ያለው (Competent) የዳኝነት አካልን ማረጋገጥ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡

ስለሆነም የዳኞች ከለላ እና ጥበቃ በሕግ እውቅና ማግኘቱ የዳኝነት ነጻነትን እና ገለልተኛነት በማረጋጥ የላቀ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት እና በአንድ በኩል የባለጉዳዮችን እርካታ ያረጋገጡ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በማኅበረሰቡ እምነት ያተረፉ ፍርድ ቤቶችን በክልሉ ውስጥ ለመገንባት ያስችላል፡፡

የዳኝነት ነጻነትን እና ገለልተኛነትን ለማረጋገጥ ከተወሰዱ መፍትሔዎች መካከል ቀደም ሲል በተለያዬ ስያሜ ይጠሩ የነበሩ እና በአስፈጻሚው አካል ሰብሳቢነት ይመሩ የነበሩ አደረጃጀቶች ቀሪ እንዲሆኑ እና በፍርድ ቤት ሰብሳቢነት የሚመራ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር መድረክን በበላይነት ማስተባበር እና መምራት አንዱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ስልጣንና ተግባር ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 5(7) ስር እንዲካተት ተደርጓል፡፡

የትብብር መድረኩን የሚመራ ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ እንዲቋቋምም ተደርጓል፡፡ ይህም ቀደም ሲል የተለያዩ ሰበቦችን በመፈለግ የተለያዬ ስያሜ ባላቸው አደረጃጀቶች አማካኝነት በክርክር በተያዙ መዝገቦች ላይ ሳይቀር ግምገማ በማድረግ በዳኞች እና በዳኝነት አካሉ ላይ ይደረጉ የነበሩ ጣልቃ ገብነቶች ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው፡፡

በተጨማሪም በክልል ደረጃ የዳኝነትና የፍትሕ አገልግሎትን በመሰረታዊነት ለመለወጥ የተጀመረዉን ሥራ የሚመራዉ የትራንስፎርሜሽን አብይ ኮሚቴ በየደረጃዉ ባሉ ምክር ቤቶች እንዲመራ መደረጉ በተመሳሳይ የዳኝነት ነጻነትና ገለልተኝነት ለማረጋገጥ ተብሎ የተወሰደ መልካም እርምጃ ነዉ፡፡

የዳኝነት ነጻነትን እና ገለልተኛነትን በማረጋገጥ ረገድ የውጭ ተፅዕኖና ጣልቃ ገብነትን መከላል ብቻዉን ግን በቂ አይሆንም ፡፡ ዳኞች ራሳቸዉ የዳኝነት ነጻነት እና ገለልተኝነትን ከሚጎዳ ተግባር መቆ

15/05/2025
ዜና         ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ  ይዞ የተገኘ ተከሳሽ ተፈረደበትጥላየ አድማስ  ቦጋለ የተባለ ተከሳሽ የኢ.ሬ.ዲ.ሪ የጦር መሳሪያ አስተዳደር  ቁጥጥር  ጥበቃ አዋጅ 1177/2012 ...
30/06/2023

ዜና
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ የተገኘ ተከሳሽ ተፈረደበት
ጥላየ አድማስ ቦጋለ የተባለ ተከሳሽ የኢ.ሬ.ዲ.ሪ የጦር መሳሪያ አስተዳደር ቁጥጥር ጥበቃ አዋጅ 1177/2012 አንቀፅ 22/2/ ስር የተደነገገውን በአዋጅ የተቀመጠውን ክልከላና ጥበቃ በመተላለፍ የፀና ፈቃድ ሳይኖረው ማያዚያ 2ቀን 2014ዓ.ም ከምሽቱ 2ሰዓት ላይ ግ/ቤት 01 ቀበሌ ጥርባ መውጫ ንብር ቁጥር ላይ 12010455 የሆነ ቱርክ ስሪት ሽኩጥ ይዞ የተገኘ መሆኑን ፖሊስ መርምረው አጣርቶ ዐ/ህግ የወረዳው ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ፍ/ቤትቱ ጉዳይ በማስረጃ አጣርቶ ጥፋተኛ በመሆን አረጋግጦ በቀን 19/10/2015ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ዓመት ከ2ወር እስራትና የብር 5000(አምስት ሽ)የገንዘብ መቆጮ እንዲቀጣ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጠ፡፡

የአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ለዋስትና ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ተግባራት እና ስለ ቅሬታ አቀራረብ በተመለከተ በቀን 21/7/2015 ዓ.ም የግ...
30/03/2023

የአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ለዋስትና ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ተግባራት እና ስለ ቅሬታ አቀራረብ በተመለከተ በቀን 21/7/2015 ዓ.ም የግንዛቤ ፈጠራ ትምህርት ተሰጠ፡፡

የአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለ ደሀ ደንብ እና ስለ ሀሰተኛ ምስክር በተመለከተ በቀን 7/7/2015 ዓ.ም የግንዛቤ ፈጠራ ትምህርት ተሰጠ፡፡
17/03/2023

የአን/ጓ/ወ/ፍ/ቤት በህዝብ ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት ለተገልጋይ ህብረተሰብ ስለ ደሀ ደንብ እና ስለ ሀሰተኛ ምስክር በተመለከተ በቀን 7/7/2015 ዓ.ም የግንዛቤ ፈጠራ ትምህርት ተሰጠ፡፡

Address

Gemjabet

26

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍርድ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share