Yibeltal Zewdu Erkyhun

Yibeltal Zewdu Erkyhun «ዝቅ ለጊዜው፣
ከፍ በጊዜ»
💚 💛 ❤ 🇪🇹 Author and Digital Creater
(2)

መንግስት ለነዳጅ በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)ባለፉት ወራት ያጋጠመውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር ለመፍታት መንግስት በወር 20 ቢሊየን ብር...
28/04/2026

መንግስት ለነዳጅ በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ባለፉት ወራት ያጋጠመውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር ለመፍታት መንግስት በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት አየር መንገዶች በረራዎቻቸውን እየቀነሱ ሲሆን፥ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ በረራ እንደሚያቆሙ እየገለጹ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ እንዳላቋረጠ እንዲሁም የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳልቆመ ገልጸው፥ ነገር ግን አንድም ኢትዮጵያዊ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ ሲጠይቅ አልተስተዋለም ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ገደማ ለነዳጅ ተጨማሪ ወጪ 100 ፐርሰንት ድጎማ መደረጉን ገልጸው፥ በዚህም በወር እስከ 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረግን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

 #ኢትዮጵያ|፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለከባድ ጭነት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገባች      ~~~~~~ኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፉን...
28/04/2026

#ኢትዮጵያ|፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለከባድ ጭነት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገባች
~~~~~~
ኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፉን ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ ለማሸጋገር በያዘችው ግብ መሠረት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ 92 ለከባድ ጭነት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገብታለች።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የተሽከርካሪዎቹን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ አረጋግጦ ወደ ሀገር እንዲገቡ ያደረገ ሲሆን፣ ይህም መንግሥት የግንባታና የንግድ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የጀመረው ስትራቴጂካዊ እርምጃ አካል መሆኑ ተገልጿል።

"እኔ እና ህወሓት ካልመራን ትግራይ ትውደም" ደብረጽዮን     ~~~~~~~የትህነግ ቅሬተ አካል ርዝሬዦች እነ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይን ወጣት ደግም መከራ ውስጥ ለመክተት አቋም ይ...
28/04/2026

"እኔ እና ህወሓት ካልመራን ትግራይ ትውደም" ደብረጽዮን
~~~~~~~
የትህነግ ቅሬተ አካል ርዝሬዦች እነ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይን ወጣት ደግም መከራ ውስጥ ለመክተት አቋም ይዣለሁ ብለዋል።

"የትግራይን ህዝብ እኔ ህወሓት ካልመራነው የትግራይ ወጣትም ሆነ ትግራዋይነት ገደል ይገባ፤ ኢትዮጵያዊነት ለኔ ተረት ነው" የሚለው የደብረጽዮን ንግግር በትግራይ ወጣት ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።

በዚህ ንግግራቸዎ የተቆጣው የትግራይ ወጣት የደበረጽዮንን አደረጃጀት ለመፋለም በመቀሌ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት እና ሌሎች ከተሞች በህቡዕ እየተደራጀ መሆኑም ተሰምቷል።

 #ባሕርዳር|፡ የባሕር ዳር ስታዲየም በቅርቡ ይጠናቀቃል‼      ~~~~~~የባህር ዳር ስታዲየምን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለሀገር እና ለአህጉር አቀፍ ውድድሮች ...
28/04/2026

#ባሕርዳር|፡ የባሕር ዳር ስታዲየም በቅርቡ ይጠናቀቃል‼
~~~~~~
የባህር ዳር ስታዲየምን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለሀገር እና ለአህጉር አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ሀገር እና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

Amhara Communications

 #ደሴ|፡ "ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው" - የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‼      ~~~~በደሴ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ አይጠየፍ ቀበሌ የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ...
28/04/2026

#ደሴ|፡ "ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው" - የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‼
~~~~
በደሴ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ አይጠየፍ ቀበሌ የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅና የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር ተከናውኗል።

📷
Dessie PP/ደሴ ብልፅግና ፓርቲ fans
Dessie City Administration Communication

➡️ ሰበር ዜና ‼ ኮለኔሉ ፋኖ ተማረከ           ~~~~~~~የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል እና አመራር የነበረ፣ አሁን ላይ የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር እና አዋጊ የሆነው ኮለኔል አ...
28/04/2026

➡️ ሰበር ዜና ‼ ኮለኔሉ ፋኖ ተማረከ
~~~~~~~
የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል እና አመራር የነበረ፣ አሁን ላይ የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር እና አዋጊ የሆነው ኮለኔል አለሙ ገብሩ በሀብሩ ወረዳ ጥምር ጦር በቁጥጥር ስር ውሏል።

እጅ አንሰጥም ያለው አብሮት የነበረው ሀይል የተደመሰሰ ሲሆን በሰላም እጅ የሰጠው ነፍሱን አድኗል።

ዝረረዝር መረጃውን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

27/04/2026

ገመና መገላለጡ እና የእርስ በርስ ትርምሱ ቀጥሏል‼
~~~~~~
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በፋኖ ደረጀ በላይ ላይ መግለጫ አአውጥቷል።

ራሱን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጣና ብርጌድ እያለ የሚጠራው ቡድን በፋኖ ደረጀ በላይ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ሲል በመግለጫ ጠየቀ።

በመግለጫው ፋኖ ደረጀ በላይ የጣና ብርጌድ አዛዥ የነበሩትን ሻለቃ ልባርጋቸው ሙጬን እና አጃቢያቸውን በደባ አስገ$ድሏል ሲል ክስ አቅርቧል።

ሻለቃ ልባርጋቸው ሙጬን እና አጃቢያቸውን በደባ የተገ$$ደሉት በአካባቢው የሚፈጸሙ የንጹሐን እገታዎችን፣ የገንዘብ ዝርፊያዎችን እና የአርሶ አደሮች መሣሪያ መነጠቅን በመቃወማቸውና ለትግሉ የተሰበሰበ 2.15 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅሙ አውሏል በማለታቸውና ከመንግሥት 12,000 ጥይቶችን በምስጢር ተቀብሏል ብለው በማጋለጣቸው እንደሆነ በመግለጫው ተገልጿል።

የጣና ብርጌድ አባላት ይህ ግድ$$ያ የልባርጋቸውን ተቃውሞ ለማጥፋት የታቀደ ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን የጽንፈኛው ፋኖ የላይኛው አመራር ጉዳዩን አይቶ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

ባለፈው ዓመት ሁለቱ ልጆቹ በራሳቸው በፋኖ አባላት ከተገ$$ደሉ በኋላ ደረጀ በላይ የፋኖ ታጋዮችን አንድ በአንድ በዘዴ የማስወገድ ሥራ እየሠራ እንደነበር የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ፋኖ ደረጄ በላይ የልጆቹን ሞት ለመበቀል ከመንግሥት ጋር በምስጢር ሲተባበር ቆይቷል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።

ከባህር ማዶ የሚታዘዝ የሞ$ት ድግስ‼ባህሩን አቋርጦ፣ ​ውቅያኖሶችን ተሻግሮ፣ በሻቢያና ግብፅ ታዝሎ የሚመጣው ድምፅ የሰላም አይደለም። ​የሞ$ት ድግስ ደጋሾች ባሉበት ሀገር ህግ ይከበራል፣ ህ...
27/04/2026

ከባህር ማዶ የሚታዘዝ የሞ$ት ድግስ‼

ባህሩን አቋርጦ፣ ​ውቅያኖሶችን ተሻግሮ፣ በሻቢያና ግብፅ ታዝሎ የሚመጣው ድምፅ የሰላም አይደለም።

​የሞ$ት ድግስ ደጋሾች ባሉበት ሀገር ህግ ይከበራል፣ ህጻናት በሰላም ይጫወታሉ፣ ወጣቶች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ። ድንበር አቋርጦ በዲጂታል መስኮት የሚመጣው ትዕዛዛቸው ግን እዚህ ያለውን ወጣት ወደ ጥፋት አዝቅት መግፋት ነዉ። 'ታጠቅ፣ ዝመት፣ ተዋጋ' የሚለው ትዕዛዝ የሚሰጠው፣ ጥይት በማይደርስበት፣ ቦምብ በማይፈነዳበት እና ሰላም በሰፈነበት የምቾት ቀጠና ውስጥ ሆኖ ነው።

​ምክንያቱም ጦርነት ስክሪን ላይ የሚታይ ፊልም ነው። የወጣቶች መስዋዕትነት ለእነሱ የፖለቲካ ጥገኝነት ማግኛ 'ማስረጃ' ነው።

ከባህር ማዶ የሚታዘዝ ሞ$ትን 'እምቢ' በል✊

27/04/2026

#ፍኖተሰላም|፡ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

በፍኖተ ሰላም ከተማ ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከአባላቱ፣ ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የምርጫ ምልክትና እጩ የማስተዋወቅና የጎዳና ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር!!





Finote Selam City Communications

27/04/2026

የትግሉ ዓላማ ➡️ አርሶ አደሩን አድማ! 🤔🤔🤔
~~~~~~~~~~
የትግሉ ዓላማ...

➡️ ህወሓት እንዳይከፋው አማራን አውድመው‼
➡️ አርሶ አደሩን ዝረፍ፣ ተቋማትን አውድም‼
➡️ ታሪካዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቱን አጥፋ ‼

27/04/2026

ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት
******
የሰው ልጆችን ሰብአዊ ልዕልና እና የሀገራትን ሉዓላዊነት የሚሸረሽረው ቁልፍ ችግር የኢኮኖሚ ጥገኝነት ነው። ሀገራችንም ብዙ ዘመኗን ኢኮኖሚዋ በፋይናንስ፣ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ በሌሎች ላይ ጥገኛ ሆኖ ኖሯለች። ሕዝብ በኢኮኖሚያዊ ችግሮችና ጉስቁልና ምክንያት ለእርዳታና ለድጋፍ ተጋልጧል።

በመሆኑም ለብሔራዊ ርዕያችን መሳካት በሀገር ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ነጻነትን፣ ተወዳዳሪነትን እና ልዕልናን ማረጋገጥ ይገባል የሚል ቁርጠኛ አቋምና እምነት አለን። ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ሲባል ከጥገኝነት የተላቀቀ፤ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን መፍጠር፣ መጠቀምና ማስፋት የሚችል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ፤ ኢኮኖሚን መፍጠር ማለት ነው።

ሀገራችንን የገዘፈ ኢኮኖሚ ባለቤት ማድረግ እና በሀገር እንዲሁም በዜጎች ደረጃ የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ለዜሮ የተጠጋ ማድረግ ነው።የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ርዕያችን ሀብት ማፍራት ብቻ አይደለም፡፡ የጋራ ዕሴት በመገንባት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሀገር ስኬት ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል ጭምር ነው፡፡

በዚህም አማካኝነት በኢኮኖሚ የበቃ ሀገርና ሕዝብ
በመፍጠር ለዓለም ሀገራት መትረፍን ያለመ ነው።

በዚህም፡-
• ከተረጂነት ወደ ረጂነት
• ከሸማችነት ወደ አምራችት
• ከንግድ ሚዛን ጉድለት ወደ ተመጣጣኝ ሚዛን
• የንግድና የገበያ ማዕከል
• የፈጠራና ኢንተርፕረነርሽፕ ማዕከል
• ለሰው ልጆች የተስማማ አረንጓዴ ሀገር ለመገንባት ያልማል።

ፓርቲያችን ብልፅግና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያልመውና እየተገበረ ያለው ዐቅም ያላትን ሀገርን ለመገንባት ነው፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን የሚሆነውም ከአንድ ዘርፍ ዕይታ ወጥቶ በብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ውጤታማ መሰናሰል እንደሆነ ይረዳል።

ብዝኃ ዘርፍ ተኮር ኢኮኖሚ ለተግዳሮቶች ምላሽ መስጠት የሚችል፣ የማይበገርና ጤናማ መዋቅር ላይ የሚመሠረት፣ ለሁለተናዊ ብልፅግና ዋስትና የሆነ ነው።

ለዘላቂ ዕድገት ያለን ቁርጠኝነት ኢኮኖሚያዊ ግሥጋሴያችን ከአረንጓዴ ዐሻራ ጋር የተሣሠረ መሆኑን በማረጋገጥ ነው። በዚህም የሚፈጠረው ብልፅግና፣ ሁሉም ዜጎቻችን የሚጋሩት ከመሆን ባለፈ፣ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ፍትሐዊ እና ርትዐዊ የሆነች ሀገርን ለመገንባት ያለመ ነው።ለዘመናት የቆየውን የውጭርዳታ ጥገኝነት መንሥኤዎችን በማረም ሀገራችንን በራሷ ዐቅም ላይ እንድትቆም እናደርጋለን።

በቀጣይ አምስት ዓመታት፡-

ሀገራችን በሁሉም መስኮች ከተረጂነት ወጥታ፣ ያላትን ዕምቅ የልማት ዐቅም ወደ ምንዳነት ቀይራ፣ የአህጉራችንንም ሆነ የቀጣናችንን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ወደ ምትፈታበት ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ጠንካራ ሥራዎችን እንሠራለን።

ይህንን የነጻነት ጎዳና በምንጀምርበት ወቅት፣ በሌሎች ሀገራት የሚከሠቱ ችግሮች፣ የተሣሠሩ ተግዳሮቶችን እና ቀውሶችን በውስጣችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ እንረዳለን፡፡

ነገር ግን ለእነዚህ ተግዳሮቶችና ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት የሚችል ዐቅም በመፍጠር፣ እየፈተኑን ያሉ ውጫዊ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም እንችላለን። አብዛኞቹ የውስጥ ችግሮቻችን ከውጭ ጥገኝነት ጋር የተያያዙ ናቸው። ይህንን ውስብስብ ትሥሥር በመገንዘብ ዘላቂ መፍትሔዎችን እንቀርፃለን።

በእርዳታ ላይ ያለንን ጥገኝነት እስከወዲያኛው እንዲያበቃ ለማድረግ እንሠራለን፡፡ የፖሊሲዎቻችንን አቅጣጫ በራሳችን ፍላጎት የመወሰን ሙሉ ነጻነታችን ይበልጥ በፅኑ መሠረት ላይ እንዲቆም እናደርጋለን።

በዓለም አቀፍ፣ በአህጉራዊና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም ድምፃችን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰማ የሚያስችለን ከተረጂነት ስንላቀቅ ነው። በመሆኑም ይሄንን የጥገኝነት ጉዞ እንቀይረዋለን ።ቀይረንም የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በአጎራባችም ሆነ በሌሎች ወሳኝ ሀገራት ዘንድ በማስከበር፣የራሳችንን አጀንዳ በነጻነት እናስፈፅማለን።

ይህ ለውጥ ለጠንካራውና ለሠራተኛው ሕዝባችን ትልቅ የሥነ ልቡና ስንቅ እንዲሆን በማድረግ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የጥገኝነት ስሜት እንሰብራለን፡፡ ሰብረንም የራሳችንን ዐቅም ማዕከል ያደረገ ሁሉን አቀፍና አካታች ልማት ለማከናወን ቆርጠን ተነሥተናል።
#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር
#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ

 #ቁጭ|፡ "ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው"     ~~~~~~በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎችን እና የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ...
27/04/2026

#ቁጭ|፡ "ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው"
~~~~~~
በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎችን እና የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ መረሀ ግብር ተከናውኗል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎችንና የምርጫ ምልክቱን ለህዝብ የማስተዋወቅ ስራ በቁጭ ከተማ በድምቀት ተከናውኗል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yibeltal Zewdu Erkyhun posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Yibeltal Zewdu Erkyhun:

Share