ANRS Bowcsa Ethics Officer Page

ANRS Bowcsa Ethics Officer Page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Bowcsa Ethics Officer Page, Public & Government Service, Bahir Dar.

07/06/2022
የተቋማትን ገጽታ ለመገንባት የኃላፊዎች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸየአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለሰራተኞች በስነ-ምግባር ዙሪያ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስ...
06/06/2022

የተቋማትን ገጽታ ለመገንባት የኃላፊዎች ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለሰራተኞች በስነ-ምግባር ዙሪያ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጠ
በዕለቱ መድረኩን በንግግር የከፈቱት ዶ/ር አበበ ባየ ሙስና በሃገራችን አደገኛ በሽታ ሆኗል፡፡ ድርጊቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፤ ለዚህ ደግሞ ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት የማህበረሰቡን አመለካከት ማስተካከል ተገቢ በመሆኑ ስልጠና መስጠት አስፈልጓል፤ ምንም እንኳን የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ ቢሆንም ጉዳዩ የህዝብ ጉዳይ ነው፤ የስነ ምግባር ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው፤ ለጥፋቱም ለልማቱም ተጠያቂዎች እኛው ነን፤ ያለውን የመጠበቅ የጠፋውን የመመለስም የኛው ስራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከክልሉ ስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የመጡትና የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ በስነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮሩ ረዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ዘረኝነት ከቤተሰብ ጀምሮ እሰከ ሃገር ሰፍኗል፤ ትውልዱ ከፈጣሪው ይልቅ ገንዘብን የማምለክ አዝማሚያዎች ይታያሉ፤ ለዚህ ደግሞ የስነ- ምግባር ትምህርት መሰጠቱ ቀና አስተሳሰብን፣ ምክንያታዊነትን.. በማዳበር እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና አለው፤ በተለይ ደግሞ ከቤተሰብ ጀምሮ ልጆች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል፤ ልጆች በባህሪያቸው ንግግራችን ሳይሆን ድርጊታችን ስለሚከተሉ ተግባር ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ በተቋማት ውስጥም ስነ-ምግባርን ለማስረጽና የተቋማትን ገጽታ ለመገንባት የኃላፊዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው፤ ያለዚያ በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ ነው፤ የሙስና ጉዳይ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ እንጅ በተወሰኑ አካላት ጥረት ብቻ የሚሳካ አይደለም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ተሳታፊዎችም የቀረበልን ስልጠና ሳቢና ማራኪ፣ ሳይንሳዊ፣ ትልቅ ጭብጥ እንድንይዝ ያደረገ፤ ወደራሳችን እንድንመለከትና እንድንተገብር፣ የአስተሳሰብ ለውጥ እንድናመጣና ወደፊት ከራስ አልፎ ለሃገር የሚጠቅም ተግባር ለመፈጸም እንድንዘጋጅ የሚያስችል ስልጠና አግኝተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ም/ቢሮ ኃላፊን በመወከል መድረኩን የመሩት አቶ መልካሙ አዳም ጉዳዩ የአመለካከት እንጅ የእውቀት ስላልሆነ ሁላችንም ወደሌላ ከመቀሰር ወጥተን አኩሪ ባህላችን በመጠበቅ ባህልና ስነ-ምግባር ሰፊ ቁርኝት ስላላቸው የአመለካከት ለውጥ ስናመጣ ሁሉም ስለሚስተካከል ሃገርን መውደድ ራስን ከመውደድ ይጀምራልና ሁላችንም ከቤተሰብ ጀምሮ የበኩላችን ለመወጣት ዝግጁ እንሁን ሲሉ መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የሴት ቀን!የእኩልነት ፍትሃዊነት ጥያቄሽዘመናትን ቆጥሮ ቢወጣ ፈንቅሎሽአሁንም አሉ ጥያቄሽን ሲሰሙዝቅ ሊያደርጉሽ አንገታቸውን ዝቅ የሚያደርጉጉዳይሽን ለዘመናት ያስዘገሙየእውነት ፍርድሽን የገመ...
31/03/2022

የሴት ቀን!
የእኩልነት ፍትሃዊነት ጥያቄሽ
ዘመናትን ቆጥሮ ቢወጣ ፈንቅሎሽ
አሁንም አሉ ጥያቄሽን ሲሰሙ
ዝቅ ሊያደርጉሽ አንገታቸውን ዝቅ የሚያደርጉ
ጉዳይሽን ለዘመናት ያስዘገሙ
የእውነት ፍርድሽን የገመደሉ
ሃብት ንበረትሽን በጠራራ የመዘበሩ
////........./////.............////.................

ቀን እኔ የእህቴ ጠባቂነኝ
ያለሴት በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነው ያሉ
ማታ አሲድ ሳኒታይዘር የሚቀቡ
በዱላ ሚነርቱ አንጀት ሚበጥሱ
በሴትነት ክብርሽ ሚቀልዱ
አሉ ቃል የእምነት ዕዳ መሆኑን ያልተረዱ
////............////////.............///////..................
አዎ መከበርማ አለበት
የአገር አስቀጣይ እንቁ ዘር እኮናት
ለእኔ ብቻ ያልፈጠረባት
ብዙዎች ወደ ኋላ የሚጎትቷት
ወደፊት ስትል እሾህ ሆነው የሚወጓት
ግን ችግር መከራው የማይበግራት
ያጎረሰችው የሚነክሳት
የእርሷ እሷ እንኳን የማትተኛላት
////////.............////////..........///////...............
አዎ መከበርማ አለበት
ከመከበር ባለፈ ሁነት………!
ሙስናን በጋራ ስንከላከል
የሴቶችን ጉዳይ እናሳካለን!

የሴቶችን ስር የሰደደና ዘመናትን ያስቆጠረ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስናነሳ ሴቶች የሚገባቸውን አላገኙም፣ አልሆኑም…....ወዘተ የሚሉ በረካታ ችግሮች ይጠቀሳሉ፤ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች ቀን በማ...
31/03/2022

የሴቶችን ስር የሰደደና ዘመናትን ያስቆጠረ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስናነሳ ሴቶች የሚገባቸውን አላገኙም፣ አልሆኑም…....ወዘተ የሚሉ በረካታ ችግሮች ይጠቀሳሉ፤ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች ቀን በማክበርና በመፈክር ብቻ ሊፈቱ እንደማይችሉ እሙን ነው፡፡
የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥቃቶችንም ለመቀነስ የሚቻለው ቀን ከማክበር በዘለለ ሴቶች ላይ ለሚፈጸሙ ግፎች ሁሉ ምንጭ ስለሆነው ሙስና ምን ያህል አውቀናል? ምን ያህል ታግለናል? ምን ያህልስ አስበንበትና ትኩረት ሰጥተነው እናውቃለን? ብሎ ማሰብ ሲቻል ነው፡፡
የስነ ምግባር ዝቅጠት የወለደው ሙስናና ብልሹ አሰራር በተለይ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለማስረዳት ምንም ማጣቀሻ ሳያስፈልግ ነባራዊውን የሃገራችን ሁኔታ ማየት እና በየፍትህ ተቋማቱ ያለሃጢያታቸው ፍትህን ፍለጋ የሚባዝኑትን ሴቶች መመልከት በቂ ነው፡፡ ስለዚህ የሴቶችን ጉዳዮች ስኬት ላይ ለማድረስ የምንችለው ሁላችንም ፍትሃዊ አሰራሮችን በመከተል ፍትሃዊ አገልግሎት ለመሰስጠትና ሙስናን ለመታገል ስንነሳ ነው፡፡
ሙስናን በጋራ ስንከላከል
የሴቶችን ጉዳይ እናሳካለን!

24/03/2022

ስነ ምግባራዊ (ethical)
የማይኮፈስ (ትሁት)፣
ለብዙሃኑ ደህንነትና ብልጽግና የቆመ፣
ሃቀኛና ቀጥተኛ፣
ቃል የገባዉን የሚፈጽም፣
ፍትሃዊና ሚዛናዊ፣
ሃላፊነትን የሚወስድ፣
ለሁሉም ሰዎች አክብሮት ያለዉ፣
ሌሎችን የሚረዳ፣ የሚደግፍ፣ የሚያበረታታና የሚያለማ፣
ሌሎችን የሚያገለግል፣
ለእዉነትና ለትክክለኛ ነገር ድፍረት ያለዉ፣................
//////////------------/////////////
ኢ-ስነ ምግባራዊ (unethical)
የሚኮፈስና ራሱን ብቻ ለመጥቀም የቆመ፣
ግለኝነቱ ከሚገባዉ በላይ የሰፋ፣ (egomania)
አጭበርባሪና አታላይ (Practice deception)
ቃልና ስምምነትን የሚያጥፍ፣
የሚያዳላና ፍትህ የሚያዛባ፣
ስህተትንና ወቀሳን በሌሎች ላይ የሚያላክክ፣
የሌሎችን ሰዎች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣
ለህዝብ ልማትና እድገት ደንታ ቢስ የሆነ፣
ለትክክለኛና እዉነተኛ ነገር ለመቆም ድፍረት የሌለዉ፣
ድጋፍና እርዳታ የማይሰጥ፣...........................///.........................................
ስነ ምግባራዊ አገልግሎት በመስጠት ስነ ምግባራዊነትን በተግባር እናረጋግጥ!
...........................//..................................................

ዳላ ኮስታ (1998) ለአመራሮች ሃቀኝነት ማለት የሚከተለዉን ነዉ ሲል ግልጿልልታቀርብ የማትችለዉን ነገር ቃል አትግባ፣ የዉሸት ማብራሪያ አትስጥ፣ አዋቂ ነኝ በሚል አትኩራራ፣ በግዴታ ላይ ጫ...
24/03/2022

ዳላ ኮስታ (1998) ለአመራሮች ሃቀኝነት ማለት የሚከተለዉን ነዉ ሲል ግልጿል

ልታቀርብ የማትችለዉን ነገር ቃል አትግባ፣ የዉሸት ማብራሪያ አትስጥ፣ አዋቂ ነኝ በሚል አትኩራራ፣ በግዴታ ላይ ጫና አትፍጠር፣ ተጠያቂነትን አትሽሽ፣ ራስህን ሌሎችን በአክብሮትና በክብር ከማስተናገድ ሃላፊነት ነጻ አታድርግ (ዳላስ ኮስታ,1998)፡፡

አመራሮች የሚያምኑት፣ የሚያስቡት፣ የሚናገሩትና የሚሰሩት ዉስጣዊ ወጥነት ሊኖረዉ ይገባል፡፡
ይህ ዉስጣዊ ወጥነት ከግልጽነት (openness) ጋር በመሆን ተከታዮች በአመራሮች ላይ ያላቸዉን መተማመን በዘላቂነት የሚገነባ ነዉ፡፡

ስነ ምግባራዊ ፈተናዎች (Ethical Challenges)የማጭበርበርና የማታለል ፈተና፣የሃላፊነት ፈተና፣የስልጣን ፈተና፣የልዩ ጥቅም ፈተና፣የታማኝነት ፈተና፣የወጥነት ፈተና፣
24/03/2022

ስነ ምግባራዊ ፈተናዎች (Ethical Challenges)
የማጭበርበርና የማታለል ፈተና፣
የሃላፊነት ፈተና፣
የስልጣን ፈተና፣
የልዩ ጥቅም ፈተና፣
የታማኝነት ፈተና፣
የወጥነት ፈተና፣

08/03/2022

Reasons to make anti-corruption projects women-specific /by 6 TI chapters in Africa/

Corruption affects everyone, but women are particularly affected by corruption in the public and basic services.
Women in positions of power are perceived as less corrupt and they need to be engaged as opinion makers, role models and champions.
Better educated and informed women are better empowered to fight corruption.
In families, integrity values are primarily passed to children through women.
Women are more affected by poverty than men – therefore, they are also more affected by the poverty-corruption cycle.

08/03/2022

The police and judiciary are perceived as the most corrupt institution in the 109 countries. When judiciaries are corrupt, justice can be bought at the highest price. As women often lack resources, fighting for one’s rights in a corrupt legal system is simply out of reach.


Global Corruption Barometer, 2013

03/03/2022

ጉቦ መቀበል (አንቀጽ 10)
ጉቦ መቀበል ማለት በሙስና ወንጀሎች አዋጅ 881/2007 መሰረት
ማንኛዉም የመንግስት (የህዝባዊ ድርጅት) ሰራተኛ በሃላፊነቱ ወይም በስራ ግዴታዉ
ማድረግ የማይገባዉን ለማድረግ ወይም ማድረግ የሚገባዉን ላለማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ጥቅም የጠየቀ፣ የተቀበለ፣ የተስፋ ቃል የተቀበለ እንደሆነ ነው፡፡
ጉቦ መቀበል የንጹሃንን ደም መጠጣት ነው!
ጉቦን በመጸየፍ
ለህሊናችን እንስራ!

የትውልድ ካንሰር የሆነው ሙስና በአገራት ላይ የሚያስከትላቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች በብዙ መልኩ የሚገለጹ ቢሆንም በዋነኛነት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስኮች ላይ የሚያስከትለው አደጋ ከ...
03/03/2022

የትውልድ ካንሰር የሆነው ሙስና በአገራት ላይ የሚያስከትላቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች በብዙ መልኩ የሚገለጹ ቢሆንም በዋነኛነት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስኮች ላይ የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነዉ፡፡ በዚህ ዘመን አገራችን ለገባችበት አሳዛኝ ክስተት ዋናው ምክንያት ሙስና መሆኑ ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው፡፡
በዚህ ዓመት ትራንስፓረንሲ ኢንተረናሽናል ሙስናን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ በደረጃ 87ኛ ነጥቧ ደግሞ 39 መሆኑን አመላክቷል፡፡ ምንም እንኳን አገራችን ያገኘችው ነጥብና ደረጃ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የተሸለ ቢመስልም የውጤቱ ዝቅተኛነት ከሚያሳየው ክፍተት በተጨማሪ ካለው አገራዊ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ገና መሰራት ያለባቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ ያመላክታል፡፡
በመሆኑም ሁላችንም በጋራ ሙስና ላይ በመዝመት ኢትዮጵያን ድህነት የተወገደላት፣ ፍቅርና ሰላም የሰፈነባት፣ እንደ ሲንጋፖር ሱቆች ሳይዘጉ ክፍት የሚያድሩባት አገር ለማድረግ የበኩላችን ጥረት እናድርግ….!
መልካም ቀን!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Bowcsa Ethics Officer Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share