Sidama Region Electric Utility - EEU - የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Sidama Region Electric Utility - EEU - የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Sidama Region Electric Utility - EEU - የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት 
This is the official page of Sidama Region Electric Utility, A regional branch of the EEU

የሀዘን መግለጫ በሲዳማ ክልል በምስራቃዊ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አሰቃቂ ትራፊክ አደጋ ከ71 በላይ ወገኖቻችን ህይወት በመቀጠፉ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ ...
31/12/2024

የሀዘን መግለጫ

በሲዳማ ክልል በምስራቃዊ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አሰቃቂ ትራፊክ አደጋ ከ71 በላይ ወገኖቻችን ህይወት በመቀጠፉ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማናጅመንት እና ሰራተኞች በደረሰው አደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች በሙሉ መፅናናትን ይመኛሉ።

የሲዳማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ታህሳስ/2017ዓ.ም

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል***********ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በ...
07/12/2024

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
***********

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

ክቡራን ደንበኞቻችንተቋሙን የተመለከቱ መረጃዎችን የማግኝያ ገፆችን እናስተዋውቅዎየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን የተመለከቱ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስ...
11/11/2024

ክቡራን ደንበኞቻችን

ተቋሙን የተመለከቱ መረጃዎችን የማግኝያ ገፆችን እናስተዋውቅዎ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን የተመለከቱ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUOfficial/
ቴሌግራም፡ t.me/eeuethiopia
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
ቲዊተር፡ https://twitter.com/EEUEthiopia
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility

በስራ ምክንያት የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ስለማሳወቅ***የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት  የመልሶ ግንባታ  ስራ ለማከናወን በሲዳማ ክልል በዳዬ ከተማ እና አካባቢው፣ በአቦስቶ ፣ በ...
09/11/2024

በስራ ምክንያት የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ስለማሳወቅ
***

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን

በሲዳማ ክልል በዳዬ ከተማ እና አካባቢው፣ በአቦስቶ ፣ በመሰንቀላ እና በአንፈራ ከተሞች እና በአካባቢው

ሕዳር 1 /2017 እሁድ እለት ከጥዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጥ በመሆኑ

በተጠቀሰው አካባቢ የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡


Follow ሀs
Telegram
https://t.me/SIDAMAEU
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61551030763514
ሕዳር/2017

24/10/2024
የኤሌክትሪክ ሃይል ሳያስሞሉ  #ለረዥም ጊዜ መጠቀም ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብ የሚዳርግ መሆኑን ያውቃሉ? እንግዲያውስ እናሳውቅዎ!! አንዳንድ  #የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎች ቴክኒካልና ቴክኒካል ባ...
16/10/2024

የኤሌክትሪክ ሃይል ሳያስሞሉ #ለረዥም ጊዜ መጠቀም ለተጠራቀመ የፍጆታ ሂሳብ የሚዳርግ መሆኑን ያውቃሉ?

እንግዲያውስ እናሳውቅዎ!! አንዳንድ #የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎች ቴክኒካልና ቴክኒካል ባልሆኑ ምክንያት ከተሞላላቸው የሃይል መጠን በላይ ለረዥም ጊዜ ሊያስጠቅሙ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ውድ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ሃይል ሳያስሞሉ ለረዥም ጊዜ መጠቀም ለተጠራቀመ የአገልግሎት ክፍያና የፍጆታ ሂሳብ የሚዳርግ መሆኑን አውቃችሁ የቆጣሪ ካርድ በየወሩ እንድትሞሉና የቆጣሪ ቴክኒካል ችግር ካጋጠማችሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

የቆጣሪ ደንበኝነት ውል እድሳት ጊዜው ተራዝሟል ተቋማችን የደንበኝንት ውል ከገቡ 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሞላቸው ደንበኞች የደንበኝነት ውላቸውን እንዲያሳድሱ ባሳወቅነው መሰረት በርካታ ደንበ...
11/10/2024

የቆጣሪ ደንበኝነት ውል እድሳት ጊዜው ተራዝሟል

ተቋማችን የደንበኝንት ውል ከገቡ 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሞላቸው ደንበኞች የደንበኝነት ውላቸውን እንዲያሳድሱ ባሳወቅነው መሰረት በርካታ ደንበኞች የቆጣሪ ደንበኝነት ውላቸውን እያደሱ ይገኛሉ::

ይሁን እንጂ በተለይ በአዲስ በአባባ አንዳንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚስተዋለውን መጨናነቅና የደንበኞችን እንግልት መነሻ በማድረግ የቆጣሪ አገልግሎት ደንበኝነት ውል ዕድሳት ጊዜው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ያራዘምን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስለሆነም የአገልግልት ደንበኝነት ውል ከገባችሁ 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሞላችሁ ውድ ደንበኞቻችን የውል ዕድሳት ጊዜው የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ ሳትጨናነቁ በተመቻችሁ ጊዜ ወደ አገልገሎት መስጫ ማዕከሎቻችን እየሄዳችሁ ያለምንም ክፍያ የደንበኝነት ውላችሁን እንድታሳድሱ እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

10/10/2024

የደንበኛ ቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓትን ለማሻሻል እየተሰራ ነው
***************
ደንበኞች በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸውን ቅሬታ በ905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማእከላት፣በአገልግልት መስጫ ማዕከላት፣በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እንዲሁም በተቀመጡ በሌሎች የቅሬታ መቀበያ መንገዶች ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህም ተቋሙም ከደንበኞች የሚደርሱትን ቅሬታዎች በየደረጃው ተመልክቶ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሆኖም በነዚህ የቅሬታ እና ጥቆማ ማስተናጋጃ ስርዓቶች ላይ ደንበኞች የሚያነሷቸው ውስንነቶች አሉ ከነዚህም በተለይ በ905 ነፃ የጥሪ ሲደወል ስልክ አይነሳም፣ ፈጣን ምላሽ አይሰጥም፣ ማዕከሉ በዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ብቻ የተወሰነ መሆኑ ከደንበኞች የሚነሱ ጥያቆዎች ናቸው፡፡

ተቋሙ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ደንኞች ቅሬታቸውን በሞባይል መተግበሪያው እንዲያቀርቡ ያመቻቸ ሲሆን፤መተግበሪያው የፍጆታ መጠንና የቀድሞ ክፍያ ታሪክን ለማየትም ያስችላል፡፡

መተግበሪያው ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ ደንበኞች ስልካቸውን ተጠቅመው የአዲስ ኃይል ጥያቄ እንዲያቀርቡ እና ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡

ተቋሙ በተያዘው በጀት ዓመት ከላይ የተጠቀሱትን የደንበኛ ጥያቄዎች ለመመለስ ተቋማችን ከያዛቸው እቅዶች መካከል 905 የጥሪ ማእከልን አገር ዓቀፍ ማድረግ አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር የአስቸኳይ ጥገናዎች በፍጥነት ለማከናወን የሚያስችል ፊልድ ኦፕሬሽን ሲስታንስ የተሰኘ ሥርት ተግባራዊ ለማድረግ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

ይህም ደንበኞች በተመቻቸው መንገድ የአስቸኳይ ጥገና ሲያመለክቱ የተመደቡ የጥገና ባለሙያዎች ሥራውን ስለመስራታቸው ለመከታተል የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡

ሥርዓቱ የጥገና ባለሙያው ባለበት ቦታ ሆኖ በሲስተም አማካኝነት ጥቆማው እንዲደርሰው ከማስቻሉም በላይ፤ባለሞያው ስራውን ካጠናቀቀ በኋላ ሲስተሙ በራሱ ወደ ደንበኛው በመደወል ቅሬታው ስለመፈታቱ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡

ይህም አመልክቼ አልተሰራልኝም እና ሳይሰራልኝ ተሰርቷል የሚል መልዕክት ደረሰኝ ለሚሉ የደንበኛ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

በዳዬና አካባቢው ለተወሰኑ ሰዓታት የሚኖር የኃይል መቋረጥን ስለማሳወቅየሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋራ አንፈራራ ድረስ የሚያከናውነው የመልሶ ግንባታ ስራ መስመር ከዳዬ ከተማ የኤሌክ...
09/10/2024

በዳዬና አካባቢው ለተወሰኑ ሰዓታት የሚኖር የኃይል መቋረጥን ስለማሳወቅ

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋራ አንፈራራ ድረስ የሚያከናውነው የመልሶ ግንባታ ስራ መስመር ከዳዬ ከተማ የኤሌክትሪክ መስመር አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በዳዬ ከተማ ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር ከይርጋለም እና ከአለታወንዶ ወንዶ ከተሞች ለብቻው ኃይል እንዲያገኝ የማድረጉ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ሆኖም ከዋራ ሰብስቴሽን እስከ አንፈራራ እየተከናወነ የሚገኘው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ ለአንድ ሳምንት ተሰርቶ እስከ ሚጠናቀቀ ድረስ በዳዬ ከተማ ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ የኃይል መቆራረጥ ሊፈጠር የሚችል በመሆኑ በዳዬ ከተማ እና በአካባቢው የምትገኙ ደንበኞቻችን በትዕግሥት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት
መስከረም/2017ዓ.ም

ተቋሙ በሲዳማ ክልል በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገየሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በወንሾ ወረዳ ሐምሌ 2...
02/10/2024

ተቋሙ በሲዳማ ክልል በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረገ

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በወንሾ ወረዳ ሐምሌ 2016ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መስከረም 21/2017ዓ.ም በቦታው ድረስ በመሄድ ህብረተሰቡን በማፅናናት የአይነት ድጋፍ አደረገ።

በተደረገው የድጋፍ ፕሮግራም የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አየለች ሌዳሞ፣ የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባንታየሁ ቀፀላ፣ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ፣ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማኔጅመንት ቡድን አባላት ተገኝተዋል።

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ ተቋሙ ለህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የበጎ ተግባር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በሲዳማ ብሄራዊ ክልል በተፈጥሮው አደጋ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ የወንሾ ወረዳ ነዋሪዎች ለአንድ አባወራ 20 ኪሎ ግራም ፉርኖ ዱቄት እና 3 ሊትር ዘይት በአጠቃላይ ለ112 ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ለእያንዳንዳቸው በነፍስ ወከፍ ድጋፍ ማድረጉን፤ እንዲሁም በይርጋለም ከተማ እና በወንሾ ወረዳ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 260 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሣሪያ ድጋፍ ማድረጉን የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው በአጠቃላይ 268,000.00(ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ብር) አዋጥተው በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን፣ በተደረገው ድጋፍም እያንዳንዱ የስራ ኃላፊና ሰራተኛ ለወገናቸው በችግራቸው ወቅት በመድረሳቸው ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን አቶ አበበ እድሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ መሆኑን በመጥቀስ በሲዳማ ብሄራዊ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በይርጋለም ከተማ እና በወንሾ ወረዳ ለሚገኙ 260 ተማሪዎች በአጠቃላይ 3,143 የመማሪያ ደብተሮችን ድጋፍ ማድረጉን አቶ አበበ እድሉ ገልፀዋል።

በድጋፍ ፕሮግራሙ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አየለች ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በሲዳማ ክልል በዜጎች የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ ተሰምቷቸው ድጋፍ ለማድረግ በመምጣታቸው፣ ለተጎዱት የህብረተሰብ ክፍሎችም ከደመወዛቸው አዋጥተው ድጋፍ በማድረጋቸው የተሰማቸው ደስታ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ፣ የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችን እና ሰራተኞችን አመስግነዋል።

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባንታየሁ ቀፀላ በድጋፉ ፕሮግራም ባደረጉት ንግግር የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የክልላችን ነዋሪዎች ቢሮው ድጋፍ እንዲያደርግ በተጠየቀው መሠረት ለጥያቄው ፈጣን ምላሽ በመስጠት እያንዳንዱ ሰራተኛና የስራ ኃላፊ ከወር ደመወዙ በማዋጣት ለተጎዱት ነዋሪዎች ድጋፍ በማድረጉ ያደረገው በጎ ተግባር የሚያስመሠግነው መሆኑን፤ የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ለህዝባችን ድጋፋችሁን በማሳየታችሁ፤ ለተማሪዎችም የትምህርት መርጃ መሣሪያ ድጋፍ በማድረጋችሁ የሚያስመሠግን ስራ ሰርታችኋል፤ ፈጣሪ ያክብራችሁ የሚል መልዕክትን አስተላልፈዋል።

የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ባደረገው የአይነት 268 ሺህ ብር፤ ለተማሪዎች በተደረገው የትምህርት መርጃ መሣሪያ ድጋፍ 168 ሺህ ብር ፤ በአጠቃላይ 436 ሺህ ብር ወጪ መደረጉን የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ እድሉ ገልፀዋል።

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የወንሾ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አካሉ አደም የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያመጣውን የአይነት ድጋፍ ከሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬተር አቶ አበበ እድሉ እጅ የተቀበሉ ሲሆን፣ ተቋሙ በወረዳቸው በመገኘት ላደረገው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የወንሾ ወረዳ ነዋሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ደስታቸው ታላቅ መሆኑን በመግለፅ ድጋፍ ያደረገውን የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችን እና ሰራተኞችን አመስግነዋል።


Follow ሀs
Telegram
https://t.me/SIDAMAEU
Facebook
መስከረም /2017

ቆጣሪ በወቅቱ አለመነበብ በደንበኞች ላይ ምን ያህል ጫና እንደሚያሳድር ያውቃሉ? እንግዲያውስ እናሳውቅዎ የሚጠቀሙበት ቆጣሪ ካልተነበበ ቢል ስለማይዘጋጅልዎ ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋሉ፡፡ ስለሆነም...
02/10/2024

ቆጣሪ በወቅቱ አለመነበብ በደንበኞች ላይ ምን ያህል ጫና እንደሚያሳድር ያውቃሉ? እንግዲያውስ እናሳውቅዎ የሚጠቀሙበት ቆጣሪ ካልተነበበ ቢል ስለማይዘጋጅልዎ ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋሉ፡፡ ስለሆነም ወድ #የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በተቀመጠለት የማንበቢያ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየወሩ መነበቡን ይከታተሉ፤ካልተነበበልዎትም ወዲያውኑ አገልሎት ወደሚያገሀኙበት ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ውድ #የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!! አንድ ደንበኛ በመኖሪ...
30/09/2024

ውድ #የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!!

አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም እና 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም ፤

በዚህም መሰረት፡-
1ኛ. 4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣
2ኛ. 3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት=60,000 ዋት.ሰ፣
3ኛ.1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣
ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡

ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት ሲቀየር 1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢጠቀም በተቀመጠው እርከን መሰረት በ2.46 ብር ይባዛል፡፡
በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 2.46 ብር= 622.872 ብር ይመጣል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.95 እና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ 10 ብር ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ 675 ብር ከ 80 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡

ይህ የፍጆታ ሂሳብ ስሌት የሚያገለግለው ለድህረ-ክፍያና ለመስከረም ወር ብቻ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Address

Menaherya, Next To The Bus Station
Awassa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Region Electric Utility - EEU - የሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share