Bahil Adarash Si/Quchumi Meentu Golaየባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የሴቶች ክንፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Bahil Adarash Si/Quchumi Meentu Golaየባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የሴቶች ክንፍ

Bahil Adarash Si/Quchumi Meentu Golaየባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የሴቶች ክንፍ Kuni Qooli Bahil Adarash sinu Quchumi Meentu Goola B/mine loonsanni looso egensiissannite.

ዛሬ በቀን 13/12/2018 ዓም በሀዋሳ ከተማ ባህል አደራሽ ክ/ከተማ አስተዳደር " በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በወጣቶችና በሴቶች  እየተተገበረ ባለው የክረምት በጎ ፍቃድ ስ...
19/08/2026

ዛሬ በቀን 13/12/2018 ዓም በሀዋሳ ከተማ ባህል አደራሽ ክ/ከተማ አስተዳደር " በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በወጣቶችና በሴቶች እየተተገበረ ባለው የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች አንዱ የሆነው የወጣቶች በጎነትን በሆሰፕታል ተግባር በሀዋሳ አዳሬ ሆስፕታል በመገኘት ተከናውኗል።

በዝህ መረሃ ግብር ህመሟንን የመጠየቅ ተግባር ከመፈፀምም ባሻገር ወጣቶቹ አቅማቸው የቻለውን ፤ ለህመሟኑ የሚያስፈለሰጋቸውን ፈሳሾችንን የንፅህና መጠበቅያ ቁሳቁሶችን ጭምር የማድረስ ስራ ሰርተዋል።

በቦታው በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ እና የሆስፕታሉ የቦርድ አባል የሆኑት ክብርት ፍሬህወት ወ/ፃድቅ ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ግብአቶችን በማሰባሰብ የተቸገሩትን፤የታመሙትን እና ጠያቂ ያጡ ህመሟንን የመጎብኘታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የማህበረሰብን እሴት የሚገነባ ተግባር እንደሆነ ገልፀው ትርፉ የህልውና እርካታ ከመሆንም ባሻገር ከፈጣር የሚገኝ በረከትም እንዳለ በማንሳት ምስጋናቸውን ለወጣቶቹ አቅርበዋል።
በመረሃ ግብሩ ላይ የባህል አደራሽ ክ/ከተማ የማህበራዊ ክላስተር አመራሮች እና የበጎ ፍቃደኛ ወጣት አደረጃጀቶች እና ሴቶች ተገኝተዋል።

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አመራሮች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማድረግ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገብተዋልየሲዳማ ክልል የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች "በጎነት እ...
19/08/2026

የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አመራሮች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማድረግ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገብተዋል

የሲዳማ ክልል የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች "በጎነት እና እህትማማችነት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማከናወን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገብተዋል።

አባላቱ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ሲደርሱ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በወላይታ ዞን አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ቡድኑ በሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ኤርሚያስ የተመራ ሲሆን በቆይታዉ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን እንደሚያከናዉን ተገልጿል።

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሁለቱን ክልል ሕዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነትና ትስስር ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል።

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሕዝቦች መካከል ያለዉን አብሮነት ይበልጥ ከማጠናከር ባለፈ እርስ በእርስ የመተባበርና የመደጋገፍ ባህልን የሚያዳብር ተግባር ነዉ።

በመርሃ ግብሩ የአቅመ ደካማ የቤት ግንባታ፣ የችግኝ ተከላ፣ ለተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ እንዲሁም የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ይጠበቃል።

ዛሬ በቀን 12/12/2018 ዓ/ም በባህል አደራሽ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች  ክንፍ ፅ/ቤት የክፍለከተማው አስፈፃማዎች በተገኙበት!!              የ2019 ፈፃሚ ማዘጋጃ እቅ...
18/08/2026

ዛሬ በቀን 12/12/2018 ዓ/ም በባህል አደራሽ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት የክፍለከተማው አስፈፃማዎች በተገኙበት!!
የ2019 ፈፃሚ ማዘጋጃ እቅድ እና
የክረምት በጎ ፍቃድ ሰራዎች ያሉበት ደረጃ በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ የትኩረት አቀጣጫዎች ላይ ተግባቦት ላይ ተደርሷል።

ዛሬ በቀን 9/12/2018 ዓም "‎“ብዝሀ የወጣቶች እውቀት፣ ለጋራ ትልም!” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በባህል አደራሽ ክፍለ ከተማ ተከበሮ ውሎዋል።‎‎ባህል አደራሽ ክፍለ ከ...
15/08/2026

ዛሬ በቀን 9/12/2018 ዓም "
‎“ብዝሀ የወጣቶች እውቀት፣ ለጋራ ትልም!” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በባህል አደራሽ ክፍለ ከተማ ተከበሮ ውሎዋል።

‎ባህል አደራሽ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት፤ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት እና ሴቶች ክንፍ በጋራ በመቀናጀት፣ “ብዝሀ የወጣቶች እውቀት፣ ለጋራ ትልም!” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን አክብሯል።
‎በዝግጅቱ የወጣቶች ሚና በሰላም ግንባታ፣ በሀገር ልማት፣ በበጎ ፈቃድ፣ በስፖርትና በፈጠራ ዘርፎች ላይ በሰፊው ተነስቷል። ወጣቶች ያላቸውን እውቀት፣ ችሎታና ፈጠራ በመጠቀም ለማህበረሰብና ለሀገር ዕድገት የሚጠቅም ተግባር እንዲያከናውኑም ተጠይቋል።

‎በተለይም የወጣቶች ተሳትፎን ከተሳታፊነት ባሻገር ወደ ባለቤትነትና ውሳኔ ሰጪነት ማሸጋገር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

‎የዘንድሮው የወጣቶች ቀን መርሃ ግብር ወጣቶች ያላቸውን ብዝሀ እውቀትና አቅም በማስተባበር ለጋራ ዓላማና ለሀገር ልማት ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው።

💪ባህል አዳራሽ ክፍል ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የሴቶች ማፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ እንድያደርጉ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሰ...
15/08/2026

💪ባህል አዳራሽ ክፍል ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የሴቶች ማፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ እንድያደርጉ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተሰርቷል።

የባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የ1ወር አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ 100 ቀን ዕቅድ ላይየከተማ ማእከል የተመደቡ የደጋፍ አመራሮችና አጠቃላይ የክ/ከተማ አመራሮች የቀበሌ አመራሮች  የአደረጃጀት መሪ...
12/08/2026

የባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የ1ወር አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ 100 ቀን ዕቅድ ላይ
የከተማ ማእከል የተመደቡ የደጋፍ አመራሮችና አጠቃላይ የክ/ከተማ አመራሮች የቀበሌ አመራሮች የአደረጃጀት መሪዎች በተገኙበት ጥልቅ ውይይት በማድረግና በመግባባት ወደ ተግባር ገብተናል።

11/08/2026
ዛሬ በቀን 04/11/2018 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ክንፍ  ፅ/ቤት የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክና  የ2019  ዓ/ም ዕቅድ  በተመለከተ!!!       የ ስምንቱም ክ/ከተማ  የ...
10/08/2026

ዛሬ በቀን 04/11/2018 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክና የ2019 ዓ/ም ዕቅድ በተመለከተ!!!
የ ስምንቱም ክ/ከተማ የሴቶች ክንፍ ኃላፊዎች በተገኙበት እያንዳንዱ ተግባር ላይ ተግባቦት በመፍጠርና የመፈፀም አቅማችንን ከወትሮ የላቀ አፈፃፀም ለመተግበር ጊዜ የለም በሚል ስሜት የጋራ በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል።

የክረምት ማጠናከርያ ትምህርት የሚሰጥበትን ብሩህ ተስፋ ት/ቤት በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና ሴቶች የማፅዳት ስራ ተሰርቷል፡፡
08/08/2026

የክረምት ማጠናከርያ ትምህርት የሚሰጥበትን ብሩህ ተስፋ ት/ቤት በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና ሴቶች የማፅዳት ስራ ተሰርቷል፡፡

Address

Awassa

Telephone

+251909162910

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahil Adarash Si/Quchumi Meentu Golaየባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የሴቶች ክንፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share