Sidama prison communication

Sidama prison communication government communication

31/05/2026
ማረሚያ
30/05/2026

ማረሚያ

ከማረም ባለፈ…አዘጋጅ፡ አበባ ተስፋዬ #ደሬቴድ የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከ...

30/05/2026

ከማረም ባለፈ…አዘጋጅ፡ አበባ ተስፋዬ #ደሬቴድ የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከ...

30/05/2026

ሥነ-ምግባራዊ ተቋም እንዴት ይገነባል?
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ጠንካራ እና አስተማማኝ ሥነ-ምግባራዊ ተቋም መገንባት ቀጣይነት ያለው ሥራ፣ ግልጽነት እና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ትልቅ ሂደት ነው። ተቋማዊ ብልሹ አሰራርን እና ሙስናን በመከላከል የህዝብ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ለመገንባት ወሳኝ ምሰሶዎች አለ።

👉ግልጽ የሥነ-ምግባር መርሆዎች እና ደንቦች ፦
በተቋሙ ውስጥ ምን መደረግ እንዳለበት እና ምን መደረግ እንደሌለበት በግልጽ የሚያስረዱ፣ ለአንባቢ በቀላሉ የሚገቡ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማዘጋጀት ተገቢ ነዉ። እነዚህ ደንቦች በወረቀት ላይ ብቻ ተጽፈው ከመቀመጥ ባለፈ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ፣ አመራር እና ለተገልጋዩ ህዝብ በግልጽ ሊታወቁና ሊደርሱ ይገባል።

👉የአመራር ቁርጠኝነትና አርአያነት፦
የላቀ ሥነ-ምግባር የሚጀምረው ከከፍተኛ አመራሩ ነው። መሪዎች ራሳቸው ለህግ እና ለሥነ-ምግባር ደንቦች ተገዢ በመሆን ለሰራተኛው ምሳሌ መሆን አለባቸው። የሥነ-ምግባር መመሪያዎች በሁሉም ሰራተኞች ላይ ከላይኛው አመራር እስከ ታችኛው ሰራተኛ ያለ አድልዎ እኩል ተፈጻሚ መሆን አለባቸው።

👉አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማገዝ፦
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማስገባት የአድልዎ እና የሙስና ቀዳዳዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይዘጋል። ቴክኖሎጂ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል፣ ፋይሎችን በግልጽ ለማስቀመጥ እና ማን ምን እንደሰራ በግልጽ ለማወቅ ስለሚረዳ ተጠያቂነትን ያሰፍናል።

👉ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ መፍጠርና ስልጠና፦
ሰራተኞች ስለ ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ ስለ ጥቅምና ፍላጎት ግጭት እና ስለ ጸረ-ሙስና ስልቶች ቀጣይነት ያለው ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ። ታማኝነትና ቅንነት የዕለት ተዕለት የሥራ ባህል እንዲሆኑ ተቋማዊ ንቅናቄዎችን መፍጠር።

👉ጠንካራ የሪፖርት ማድረጊያ እና የጥበቃ ሥርዓት፦
ሰራተኞችም ሆኑ ተገልጋዮች ያዩትን ሥነ-ምግባር የጎደለው ድርጊት ወይም ሙስና ያለ ፍርሃት የሚጠቁሙበት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊ የጥቆማ ሥርዓት መዘርጋት።

መረጃ አውጪዎች ወይም ጠቋሚዎች ከበቀል ወይም ከማንኛውም ጥቃት ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ።

👉ተጠያቂነት እና የማበረታቻ ሥርዓት፦
የሥነ-ምግባር ጉድለት ሲገኝ ፈጣን፣ ግልጽ እና የማስተማሪያ እርምጃ መውሰድ። በታማኝነታቸው እና በላቀ ሥነ-ምግባራቸው የተመሰከረላቸውን ሰራተኞች በማበረታታትና እውቅና በመስጠት ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑ ማድረግ።

በአጭሩ፡ ሥነ-ምግባራዊ ተቋም የሚገነባው ጠንካራ መመሪያዎችን በማውጣት፣ አሰራርን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ አመራሩ በተግባር አርአያ ሲሆን እና በሰራተኛው ዘንድ የውስጥ ስብዕና ለውጥ ሲመጣ ነው።(መልካም ቀን ይሁንላችው!!!)

27/05/2026
ግንቦት ፤16/2018ዓ.ም‎‎በግብርና ልማት እንቅስቃሴ ሞዴል ሥራዎች በመሥራት ለህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ከአዳዲስ ግብርና ልማት ቴክኖሎጂዎች ጋር የማስተዋወቅን ሥራ እየሠራ እን...
24/05/2026

ግንቦት ፤16/2018ዓ.ም

‎በግብርና ልማት እንቅስቃሴ ሞዴል ሥራዎች በመሥራት ለህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ከአዳዲስ ግብርና ልማት ቴክኖሎጂዎች ጋር የማስተዋወቅን ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ገለጸ::

ግንቦት 16፤2018 ዓ.ም

‎ በሲዳ/ብ/ክ/መ/ ማረሚያ ቤት ቤት ኮሚሽን ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ያሉ ዕድሎችን በመጠቀም የህግ ታራሚዎችን አንጾና አርሞ የሙያ ባለቤት እና የሥራ ሞራላቸውን አዳብረዉ እንድወጡ ለማድረግ የተለያዩ እንቀስቃሴዎችን እያደረገ በተለያዩ ሰብሎችን ለ
ልማልት እና እርባታ በሰፊው በቆሎ ልማትን ጨምሮ በዘመናዊ መንገድ እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል::

‎በመጨረሻም ተቋሙ የህግ ታራዎችን ማረምና ማነጽ ተልዕኮዉ መሠረት የሙያ ባለቤት እና የሥራዉ ሞራል ያለዉን የታረመ እና የተለወጠ ዜጋ አድርጎ ለማዉጣት የሚያደርገዉን ጥረት አጠናክሮ እንደምቀጥል ተገልጿል ::

‎** ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን **

‎ሀዋሳ
‎ለበለጠመረጃ-

‎Telegram_https://t.me/Hawayige
‎Facebook-https://www.facebook.com/profile.php?id=100075985375250

የሲ/ብ/ክ/መማረሚያ ቤት ኮሚሽን የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ:: ውይይቱም  በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ በስፋት በመዎያየት ከአባላቱ...
07/05/2026

የሲ/ብ/ክ/መማረሚያ ቤት ኮሚሽን የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ::

ውይይቱም በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ በስፋት በመዎያየት ከአባላቱ ገንቢ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ለሚሹት ምላሽ በመስጠት እና ወደድርጅት ማዕከል የሚቀርበውን እንደሚያቀርቡ ከመድረኩ በመግባት የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የኮሚሽኑ ክቡር ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ ውይይቱን አጠናቀዋል::

ሚያዛ 29/2018 ዓ ም

የሲ/ብ/ክ/መማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቀድሞው የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ስፍራ ተሹመው የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ሆነው የመጡትን ረ/ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ በይፋ ስራ እንዲጀምሩ የኮሚሽ...
04/05/2026

የሲ/ብ/ክ/መማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቀድሞው የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ስፍራ ተሹመው የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ሆነው የመጡትን ረ/ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ በይፋ ስራ እንዲጀምሩ የኮሚሽኑ ክቡር ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ በተገኙበት አጠቃላይ የኮሚሽኑ ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል ስርዓት ተደርጎ በይፋ ስራ ጀመሩ::

ሚያዛ 26/2018 ዓ ም

ማረሚያ ተቋማት የማረም፣ የማነፅና ብቁ ዜጋ የመፍጠር ኃላፊነታቸውን  እየተወጣ እንደሆነ ተገለፀ።የሲዳ/ብ/ክ/መ/ማረሚያ ቤት ኮሚሽንሚያዝያ/21/2018/ዓም/ሀዋሳየሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፍት...
29/04/2026

ማረሚያ ተቋማት የማረም፣ የማነፅና ብቁ ዜጋ የመፍጠር ኃላፊነታቸውን እየተወጣ እንደሆነ ተገለፀ።

የሲዳ/ብ/ክ/መ/ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
ሚያዝያ/21/2018/ዓም/ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ በሐዋሳ ከተማ ማእከላዊ ማረሚያ ተቋም የታራሚ አያያዝና አጠቃላይ ያለበትን ሁኔታ ምልከታ ዛሬ አካሂዷል።

በሀዋሳ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሹዱራ የተመራው የአመራርና ባለሞያዎች ቡድን በተቋሙ በነበረው ቆይታ የታራሚ አያያዝና የአጠቃላይ የገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን አጠቃላይ ምልከታ ሲሆን ቡድኑ በምልከታው ሂደት ላነሳቸው ጥያቄዎች የተቋሙ ኃላፊ ም/ኮማንደር ዮሴፍ ኤቢሶ ምላሽ ሰጥተዋል።

በእለቱ ያነጋገራቸው ታራሚዎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝና ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር የተሻለ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ጠቅሰው በትምህርት በስልጠናና በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተቋሙ በታራሚዎች አቅም ማጎልበት፣ የትምህርት የስልጠና እና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ የተሞክሮ ማእከል እንዲሆን ያስቻሉ ስራዎች መሰራታቸውን የሐዋሳ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሹዱራ አስረድተዋል።

በምልከታ ወቅት የታራሚዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ መኖሪያ ሁኔታ፣ የህክምናና የምግብ አቅርቦት፣ የስራ፣ ስልጠናና የትምህርት እድሎች እንዲሁም የተቋሙ አስተዳደር ቅንጅት በተለይ የግምገማው የትኩረት ነጥቦች መሆናቸውንም አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።

አቶ ሀብታሙ አያይዘው እንደገለፁት የፍትህ ተቋማት በቅንጅትና በጋራ በመስራት ከታራሚዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ አንፃር የተሻሉ አፈፃፀሞች መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን ተጨማሪ ማሻሻያ የሚጠይቁ ችግሮች ተለይተው የማስተካከያ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የመምሪያው ኃላፊ አመልክተዋል።

በተለይም የታራሚዎች መብት በሙሉ እንዲከበር እና አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ የድጋፍና ክትትል ስራ በላቀ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም የመምሪያ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

መምሪያው እንደገለጸው፣ እንዲህ ዓይነቱ ምልከታ የሕግ ተፈፃሚነትን ለማጠናከር፣ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት እና ክብር ለመጠበቅ እና የማረሚያ አገልግሎት ስርዓቱን ከማሻሻል ረገድ አስፈላጊ እና ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ም/ኮማንደር ዮሴፍ ኤቢሶ በበኩላቸው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውሳኔ አግኝተው የፍርድ ሂደታቸውን ለሚከታተሉ ከ3200 በላይ የህግ ታራሚዎች ተቋሙ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ተቋሙ የተጣለበትን የማረምና የማነፅ አደራ በተገቢው እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው ታራሚዎች በቆይታቸው ታርመው፣ ታንፀውና ተፀፅተው የበደሉትን ማህበረሰብ የሚክሱ ሆነው እንዲወጡ በላቀ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ታራሚዎች በቆይታቸው በትምህርት እውቀት ገብይተው፣በስልጠና እራሳቸውን አብቅተው እና ስራ ፈጣሪ ሆነው እንዲወጡ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አክለዋል።

ለታራሚዎች ከአንደኛ ክፍል እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት በተቋሙ እንደሚሰጥ የገለፁት ም/ኮማንደር ዮሴፍ ኤቢሶ 40 መምህራንና 20 ድጋፍ ሰጪ ባለሞያዎች እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የረዥም ዓመት ታራሚዎች ጊዜያቸውን በከንቱ እንዳያባክኑ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት በዲፕሎምና በዲግሪ መርሃግብር የትምህርት እድል መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

 #ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነውአዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ ለአምስት ተከታታይ ቀ...
23/04/2026

#ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ ለአምስት ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር።

ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል።

በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል።

Address

Sidama Rigen
Awassa

Telephone

+251949259686

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama prison communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidama prison communication:

Share