Awash Magaalah Xiinissok Leeda parti k/buxa

Awash Magaalah Xiinissok Leeda parti  k/buxa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Awash Magaalah Xiinissok Leeda parti k/buxa, Political Party, Awash.

የአዋሽ ከተማ አስተዳደር  የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምር...
03/06/2026

የአዋሽ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!

ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ጉዞ ለማፅናትና ለማስቀጠል ያለውን ፅኑ ፍላጎት በግልፅ ያሳየበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ይመዘገባል። ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጥንቃቄ አስቀምጦ በመያዝ በምርጫዉ እለት ድምፅ በመስጠት ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል።

የፖለቲካ ሥልጣን ምንጭ ሕዝብ ብቻ መሆኑንም ዳግም ለመላው ዓለም በማሳየት፣ ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ተችሏል። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው አሸናፊ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው። መራጩ ሕዝብ ሳይሰለች ከነጋት 10:00 ሰአት ጀምሮ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምፁን የሰጠው የፓርቲዎችን ድል ለመወሰን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ከፍ ለማድረግ ነው። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እድሜ ጠገብ አዛዉንቶች፣ ሙሽሮች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲን ለማፅናት ያሳዩት ትዕግስት የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነትና ጥንካሬ ለዓለም ያሳየ ታላቅ የድል ምዕራፍ ነው።

የዘንድሮው የምርጫ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ስልጡን እና ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለሀገራችን ትልቅ የሞራል ድል ሲሆን ሕዝቡ ያሳየው የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል፣ መቻቻልና እርስ በርስ የመከባበር እሴት ኢትዮጵያን ሊከፋፍሉና ሊያዳክሙ ለሚፈልጉ ሀይሎች ሁሉ ግልጽ ምላሽ የሰጠ ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ስልጡን የዲሞክራሲ ልምምድ አካሄድ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የደረሰችበትን ጀረጃ በተግባር ያሳየና የሀገሪቱን ገጽታ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ልዩ ክስተት ነው።

ይህ ምርጫ ለአዲሲቷና ለበለፀገችው ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት በመጣል ለነገዋ የበለፀገችና የተረጋጋች ሀገር ጠንካራ መሰረት የጣለ ታላቅ የስኬት ምዕራፍ ነው። 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የልዩነት ሳይሆን የኅብረት፣ የብጥብጥ ሳይሆን የሰላም መገለጫ በመሆኑ የሀገሪቱን የነገ ተስፋ ብሩህ አድርጎታል።

በመጨረሻም በተለያዩ ጫናዎች እና ፈተናዎች ሳይበገሩ ድምፄ ዋጋ አለዉ በማለት በታላቅ ሀገራዊ ክብር ፀንተዉ በመቆም በትዕግስት እስከ ሌሊት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለሰጡ እና የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ታላቅነት በተግባር ላገዘፉ ዜጎች ሁሉ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ መርጣለች!

26/05/2026

ግንቦት 24 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የስንዴ ነዶ ላይ ምልክት በማድረግ ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

በጥሞና ወቅት (ከምርጫው አራት ቀናት በፊት) በጥብቅ የተከለከሉ ተግባራትየተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም በሌሎች የቦ...
26/05/2026

በጥሞና ወቅት (ከምርጫው አራት ቀናት በፊት) በጥብቅ የተከለከሉ ተግባራት

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

Address

Awash

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awash Magaalah Xiinissok Leeda parti k/buxa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share