18/07/2026
የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ቃል 10 ደርዘን ደብተር ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ።
አጣዬ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. (አጣዬ ኮሙኒኬሽን)
የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ፣ የ2019 የትምህርት ዘመንን አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት እንዳይቸገሩ በማለት ዘመቻውን እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል።
መጪው የትምህርት ዘመን በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ያለባቸውን ተማሪዎች ለመደገፍ "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ቃል 10 ደርዘን ደብተር በመግዛት በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።
የአጣዬ ከተማ ከንቲባ እንደተናገሩት " በጎነት የማህበረሰብን አብሮነት እና መተሳሰብ የሚያጠናክር ከፍተኛ እሴት መሆኑን ገልጸው፣ ይህ የድጋፍ ዘመቻ በሌሎችም አካላት በስፋት እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በመሆኑም የከተማው ተቋማት ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ማህበረሰብ እና መላው የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" የሚለውን ዘመቻ በመቀላቀል አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።