11/06/2026
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ11 ወር ውስጥ ሁለቱን ወረዳዎች ጨምሮ 1,370,612,553.14 ብር ሰበሰበ።
*******
ሰኔ( አሶሳ 04/11/18 ዓ.ም)
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ሁለቱን ወረዳዎች ጨምሮ 1,308,714,901.81ለመሰብሰብ አቅዶ 1,370,612,553.14 በመሰብሰብ እቅዱን 100% በላይ ማሳካት ተችሏል።
እቅዱን ማሳካታችን እጅግ በጣም አመርቂ ቢሆንም ከተማው ካለው የመሰረተልማት ፍላጎትና ስፋት አንፃር በቂ ስላልሆነ በቀሪው ትቂት ወራቶች አቅማችን አሟጠን ከዚህ በላይ በመስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል ሲሉ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ አቶ አንዋር አስር ገልፀዋል።
ለእቅዳችን መሳካት ከጎናችን የነበሩትን ባለድርሻ አካላት ማመስገን ይገባል ያሉት አቶ አንዋር አስር በሰኔ ወር የሚሰሩ ስራዎች ቼክ ሊስቱን ገምግመው የስራ አቅጣጫ/ እና ሰምሪት ሰጥቷል።