የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የቤ/ጉ/ክ/መንግስት የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጅንሲ
(B/G/R/S Occupational Competency Assessment & Assurance Agency)

የቤ/ጉ/ክ/መንግስት የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጅንሲ
(Benishangul Gumuz Regional State Occupational Competency Assessment & Assurance Agency)

እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ የጥምቀት በዓል ከሀይማኖት ትምህርትና ስርዓት ባሻገር ማህበረሰቡ መልካም ማህበራዊ እሴቶች የሚያበለጽግበትና ለወዳጁ መልካም ምኞቶችን የሚመ...
18/01/2025

እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የጥምቀት በዓል ከሀይማኖት ትምህርትና ስርዓት ባሻገር ማህበረሰቡ መልካም ማህበራዊ እሴቶች የሚያበለጽግበትና ለወዳጁ መልካም ምኞቶችን የሚመኝበት ትልቅ ሀይማኖታዊ በዓል ነው። መላ የክልላችን የክርስቲያን እምነት ተከታዮችም ይህንን ተወዳጅ በዓልና እሴት አጠናክረን ለትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል።
እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!!

የቤ/ጉ/ክ/መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ ኃላፊ አቶ አብዲ ዳንጊ

14/01/2025
ከሰኔ 03/2016 ጀምሮ በአሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ እና በማንቡክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የሚያደርጉ ተመዛኞች ምዘና ተጠናቀቀ፡፡ የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙ...
20/06/2024

ከሰኔ 03/2016 ጀምሮ በአሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ እና በማንቡክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የሚያደርጉ ተመዛኞች ምዘና ተጠናቀቀ፡፡

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙ/ብ/ም/ማ/ኤጀንሲ ከሰኔ 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ለሚያደርጉ 260 ተመዛኞች የብቃት ምዘና በአሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ እና በማንቡክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው ምዘና በሰላም መጠናቀቁን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢዶሳ ጎሹ ገለጹ፡፡

ሥራና ክህሎት ሚኒስተር በሀገር ውስጥ ያለውን ስራ አጥ ወጣቶችን ከመቅረፍ አንጻር ከውጭ ሀገሮች ጋር የስራውል በመዋዋል ዜጎችን የስራ እደል ተጠቃሚ ለማድረግ አያሌ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ይህን ራዕይ ታሳቢ በማድረግ የበቃ የሰው ሀይል በማቅረብ ረገድ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ ከክልላችን ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ተመዝነው የበቁት ተመዛኞች በአቅራቢያቸው በሚገኘው የአሻራ መስጫ ማዕከል በመሄድ Labor ID በማውጣት ወደ ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመምጣት ኦን ላይን እንድታስደርጉ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ በዲጂታል እና ኦንላይን የምዘና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው የምዘና ማዕከላት አካላት የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ ፦************...
01/05/2024

የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ በዲጂታል እና ኦንላይን የምዘና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው የምዘና ማዕከላት አካላት የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ ፦
*********************
(አሶሳ)፤ ሚያዝያ 23/08/2016 ዓ.ም የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ በዲጂታል እና ኦንላይን የምዘና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው የምዘና ማዕከላት አካላት የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጥቷል ።

ሠልጣኞች በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ያካበቱትን ልምድ እውቀትና ዝንባሌን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ወቅቱ በሚጠይቀው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አተገባበር ዙሪያ ኤጄንሲው በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተገልጿል ።

ስልጠናው በመሠረታዊነት በማዕከላት ላይ ለሚደረገው የድጂታልና የኦንላይን የምዘና አተገባበር ስርዓትን የሚያሳልጥ ተግባር በመሆኑ ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ በውይይቱ ተጠቅሰዋል ።

አቶ አብዱልሙንያ ሀሊፋ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት እንደገለፁት ፦የድጂታል ቴክኖሎጂ ምዘና አጠቃቀም አስፈላጊነቱ ሀገርን እየፈታተና ያለውን የኪራይ ሰብሳቢነት ችግርን የሚቀርፍ ሲሆን ኦንላይን ምዘናም የስራ ጫና፤የቁሳቁስ እና ጊዜን ለመቆጠብ ጉልህ ሚና እንዳለው በመጥቀስ አስገንዝበዋል ።

በውይይቱ የኮሌጅ ዲኖች ፤ የምዘና ፎካል ፕረሰኖች እና የኤጄንሲው ባለሙያዎች በተገኙበት በማካሄድ ዜጎችን በቴክኖሎጂ ለማብቃት ለሚደረገው እርብርብ ሁሉ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር እንደሚጠይቅ ጭምር ዳይሬክቶሬቱ ጠቅሰዋል ።

በቀን 23/08/2016 በአሶሳ ግብርና ቴክኒክና  ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ በከተማ ዉበትና ችግኝ ልማት እና ፣ በሌሎችም ከተለያዩ ወረዳዎች የተዉጣጡ ስራ አጥ ወጣቶችን ከGIZ-QEP ፕሮ...
01/05/2024

በቀን 23/08/2016 በአሶሳ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ በከተማ ዉበትና ችግኝ ልማት እና ፣ በሌሎችም ከተለያዩ ወረዳዎች የተዉጣጡ ስራ አጥ ወጣቶችን ከGIZ-QEP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለ1ወር ስልጠና ሲወስዱ የነበሩትን ሰልጣኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና በኤጀንሲው በተወከሉ አስተባባሪ በ አቶ አብዱ ድርሻ ፣ በኤጀንሲዉ መዛኞችና በኮሌጁ አስተባባሪዎች ምዘናው እየተከናወነ ነው።

ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናን በመውሰድ ከሙስና የፀዳ አሰራር መዘርጋት እንደሚጠበቅ የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ አስታወቀ ።*****...
20/03/2024

ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናን በመውሰድ ከሙስና የፀዳ አሰራር መዘርጋት እንደሚጠበቅ የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ አስታወቀ ።
*******************
ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናን በመውሰድ ከሙስና የፀዳ አሰራር መዘርጋት እንደሚጠበቅ የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ አስታወቀዋል ።

አቶ አብዱልሙንያም ሀሊፋ የኤጄንሲው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት እንደገለፁት መንግስት ወጥነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት እንዱስትሪዎች የሙያ ደረጃን የስራ መመሪያ አድርጎ መጠቃምና መለካት በምያስችል ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል ።
ኤጄንሲው ለስምንቱ እንዱስትሪ ትኩረት ዘርፍ መሪ መስሪያቤቶች ተሳታፊ ባለሙያዎች በተፈጠረው የግንዛቤ መድረክ በክልሉ ባሉ እንዱስትሪዎች መካከል የሙያ ደረጃ አተገባበር እና አለካክ ወጥነት ችግርን በመቅረፍ አዳዲስ አሰራር መዘርጋት ተገቢ መሆኑን በውይይቱ ተጠቅሰዋል ።

በአድሱ ሙያ ደረጃ ምዘና (EXit Assessment) የፌድራል ሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር በተለያዩ ሙያዎች የምዘና መሳሪያዎችን አዘጋጅቶ የላከልን በመሆኑ፣ከዚህ ቀደም እውቅና በተሰጣችሁበት ...
26/02/2024

በአድሱ ሙያ ደረጃ ምዘና (EXit Assessment) የፌድራል ሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር በተለያዩ ሙያዎች የምዘና መሳሪያዎችን አዘጋጅቶ የላከልን በመሆኑ፣ከዚህ ቀደም እውቅና በተሰጣችሁበት የምዘና ማእከልነት አዲሱ ሙያ ደረጃ ምዘና መስጠት የማይቻል ስለሆነ እና መዛኞችም ሙያ ደረጃ በሚቀየርበት ጊዜ በአድስ ተመዝናችሁ መብቃት እንዳለባችሁ በመመሪያ ላይ የተገለጸ በመሆኑ የምዘና ማእከሎችም ሆነ መዛኞች ኤጄንሲው በገለጻቸው ደብዳቤ እና ማስታወቂያ መሰረት ተግባራዊ እንድታርጉ እንገልፃለን።

"ሁሉን አቀፍ የህዝብ ተሳትፎ ለብልፅግና ጉዟችን ስኬታማነት"በሚል ርዕስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ እና የስራና ክህሎት ቢሮ እንድሁም ለአሶሳ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ሠራ...
25/01/2024

"ሁሉን አቀፍ የህዝብ ተሳትፎ ለብልፅግና ጉዟችን ስኬታማነት"በሚል ርዕስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ እና የስራና ክህሎት ቢሮ እንድሁም ለአሶሳ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ የግንዛቤ መድረኩ ተጀመረ።

********************************************
ስልጠናው ከጥር 16-17/5/2016 ዓ.ም ተጠናክሮ የሚሰጥ ሲሆን በዛሬው ዕለት "ሀብትና ብልጽግናን መፍጠርና ማስተዳደር" በሚል ሰነድ ዙሪያ በአቶ ሀብታሙ ውባልታ የክልሉ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አማካኝነት ቀርቦ ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው ሲቪል ሠርቫንቱ አባላት ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሀብትን በአግባቡ በማስተዳደር ጠንካራ የአገልጋይነትና የማስፈፀም አቅም ለመፍጠር በሚያስችል ሁኔታ ግንዛቤው እየተፈጠረ ይገኛል።

ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት ተጠናክሮ እንደሚሰጥ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አክለው ገልፀዋል::

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በአሶሳ ከተማ አካሄደ።********************************************(አሶ...
16/01/2024

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በአሶሳ ከተማ አካሄደ።
********************************************
(አሶሳ፣ጥር 7/2016 ዓ/ም የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ለተቋሙ ሰራተኞች በአሶሳ ከተማ እያካሄ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ውባልታ የተቋሙን የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ስትራቴጅክ ግቦችን አካቶ የቀረበዉን የተጠቃለለ ሪፖርት መነሻ በማድረግ፣ በዕቅድ አፈፃፀም እና የበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ ዉይይት የተደረገ ሲሆን፤ በቀጣዩ ሩብ አመት መከናወን ስለሚገባቸዉ ቀሪ ተግባራት አቅጣጫ ተመላክቷል፡፡ ይህንንም በተጠቃለለ መንገድ ያስረዱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ውባልታ “ሁሉም ስራዎች በበጀት ብቻ የሚከናወኑ አለመሆናቸውን በመግለጽ ያለበጀት የሚተገበሩ ተግባራትን በመለየት መፈጸም እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
በግምገማው መድረክ ላይ የተሳተፉ አካላቶች የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው በዳይሬክቶሬቶችና በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በተጨማሪም ስለተከናወኑ ተግባራት እና በቀጣይ ሊከናወኑ በታቀዱ ሥራዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ
ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም ፤አሶሳ

በፓዊ ጤና ሳይንስ ምዘና ማዕከል የብቃት ማረጋገጫ ምዘና እየተሰጠ መሆኑን የቤ/ጉ/ክ/መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ውባልታ ገለፁ።***አሶሳ ፡-(ታህሳ...
11/12/2023

በፓዊ ጤና ሳይንስ ምዘና ማዕከል የብቃት ማረጋገጫ ምዘና እየተሰጠ መሆኑን የቤ/ጉ/ክ/መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ውባልታ ገለፁ።
***
አሶሳ ፡-(ታህሳስ 1,2016 ዓ/ም ) በፓዊ ጤና ሳይንስ ምዘና ማዕከል በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች የተግባር ምዘና(practical assessment) እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ከነገ ጀምሮ የንድፈ-ሀሳብ ምዘና(knowledge assessment) የሚሰጥ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል ።

የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ እና የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች ወደ ውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና እየወሰዱ ያሉትን ስልጣኞችን ጎበኙ።*****************...
03/11/2023

የቤ/ጉ/ክ/መ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ እና የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች ወደ ውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና እየወሰዱ ያሉትን ስልጣኞችን ጎበኙ።
********************************************
አሶሳ)፡-ጥቅምት 23/2016 የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክቶር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ውባልታ እንደገለፁት መንግሥት ባመቻቸው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና እየወሰዱ ያሉትን ስልጣኞች ብቃታቸውን በማረጋገጥ ወድ ስራ ለማስማረት የተደረገ ጉብኝት ነው ብለዋል።
ጥቅምት 30/2016 የስለጠኑ ሙሉ ስልጣኞች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና እንደሚወስዱ የቢሮው ኃላፊ አክለው ገልፀዋል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Address

አሶሳ መድን ድርጅት ህንጻ
Asosa
246810

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የቤ/ጉ/ክ/መ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ:

Share