የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት/Arerti Town Administrator/

  • Home
  • Ethiopia
  • Arerti
  • የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት/Arerti Town Administrator/

የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት/Arerti Town Administrator/ አረርቲ ከተማ ለመኖር ተስማሚ፣ ለስራ ምቹ የሆነች ከተማ ነች!
(1)

05/04/2026

መጋቢት 24 ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው። የመላ ኢትዮጵያውያን ለውጥ የመሻት ፍላጎት ምላሽ ያገኘበት ዕለት ነው። የሁሉም ዜጋ ሕብረት የታየበት፤ ትብብርና አንድነት የተረጋገጠበት ዕለት ነው።

ለውጡ ኢትዮጵያዊያንን በሕብረት አስተባብሮ በጋራ አሻግሯል። ሀገርንም አጽንቷል። ለውጡ ትናንትን እያደሰ፣ ዛሬን እየለወጠ ጠንካራ ሀገር የመገንባት ሕልሙንና ትልሙን በተግባር እውን በማደረግ ቀጥሏል።

ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የሀገር እና የሕዝብን ክብር ከፍ የሚያደርጉ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል። የተጀመሩ ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የሀገራችንን ከፍታ የሚያረጋግጡ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አብስሯል። በሁሉም የልማት ዘርፎች አመርቂ ውጤት ተገኝቷል።

ሀገራዊ ለውጡ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተግባራዊ በማድረግ የሀገራችን የፖለቲካ አውድና ባሕል ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እድል ፈጥሯል። ለውጡ ፈተናዎችን ወደ እድል የቀየረ፣ ወረትን ያዳበረ፣ የሀገራችን የቆየ አይበገሬነት ታሪክ ያረጋገጠ ሆኗል።

ከጠብመንጃ ይልቅ ምክክር እና ወይይትን፣ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሐሳብ ብዝሃነትን በማስቀደም በሀገራዊ ጉዳይ ላይ በትብብር አብሮ የመቆም አዲስ እሳቤን ፈጥሯል።

በመጭው ዘመንም ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ጠብቀን የጀመርነውን የሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በጋራ ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል።

Address

አማራ
Arerti
ARERTITOWN

Telephone

+251222230643

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት/Arerti Town Administrator/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category