አረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Areka City First Instance Court

  • Home
  • Ethiopia
  • Areka
  • አረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Areka City First Instance Court

አረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Areka City First Instance Court Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Areka City First Instance Court, Public Service, Wolaita Zone Areka City Administration, Areka.

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ደ/ደ/ም/ሪ ሪጂን ከመጡ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ ‎‎ግንቦት፣27/2018 ዓም ሣውላ‎...
05/06/2026

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ደ/ደ/ም/ሪ ሪጂን ከመጡ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

‎ግንቦት፣27/2018 ዓም ሣውላ

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ ለማድረግ ከኢትዮ ቴለኮም ደ/ደ/ም/ሪ ሪጂን ልዑካን እና በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ የBusiness Admnistration and Information system ስራ ክፍል ጋር ውይይት አካሂዷል።

‎የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቦጋለ ፈይሳ የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ በመቆጠብ ፍርድ ቤቶችን ከቀደመው አሠራር በማላቀቅና በዘመናዊ ተክኖሎጂ በማስተሳሰር የመረጃ አያያዝ ለማዘመንና ወረቀት አልባ ፍርድ ቤቶችን ለመፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አውስተው፤ ዲጂታላይዜሽን ቅንጦት ሳይሆን ሰው ተኮር አገልግሎት በላቀ ደረጃ በማዘመን ማህበረሰቡን መድረስ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

‎በኢትዮ ቴሌኮም ደ/ደ/ም ሪጂን የድርጅት ደምበኞች ሥ/አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ሞላ በበኩላቸው ድርጅቱ ፍርድ ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን በባለፉት ጊዜያት በጎረቤት ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችም ጋር ሰፊ ስራ እየሰራ የነበረና ከደ/ኢ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋርም ወደፊት በሚደረሰው ስምምነት አግባብ ጥራትን መሠረት ያደረገ ፍርድ ቤቶችን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ ኃላፊነቱን በብቃት እንደምወጣ ተናግረዋል።

‎በተጨማሪም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሳውላ ካምፓስ የBusiness Admnistration and Information system የሥራ ክፍል ኃላፊ፣ መምህራንና ባለሙያዎች ጋርም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዌብሳይት ማልማት ሥራ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

‎በፍርድ ቤቶቹ የሚለማው ዌብሳይት ተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚፈልገውን መረጃ በቀላሉ እና በማንኛውም ስፍራ ሆኖ እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

‎ይህ ትብብር የዳኝነት ሥርዓቱን ወደ ዲጂታል ለውጥ በማሸጋገር ፈጣን፣ ግልጽ እና ተደራሽ የፍትሕ አገልግሎት ለማረጋገጥ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑም ተጠቅሷል።

‎በዉይይቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱና የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

👇 Follow & Share us 🙏
የአረካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

05/06/2026

👇

‎ዜና ችሎት

በሙስና ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ!

‎ #አረካ፦| ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም

‎የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በንብረት ክፍል ሰራተኛ በነበረው ተከሳሽ ሐብቴ ዳንጋርሶ ላይ የቀረበውን የሙስና ወንጀል ክስ መዝገብ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል።
‎ተከሳሹ በአረካ ከተማ አስተዳደር ሀንጋዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የንብረት ክፍል ሠራተኛና ቁልፍ ያዥ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት፣ ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ላይ ከተቋሙ ንብረት ክፍል 16 ካርቶን የዋጋ ግምቱ 585,738 (አምስት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት) ብር የሆነውን የተማሪዎች እና የመምህራን መጻሕፍትን ለግል ጥቅሙ ለማዋል በባጃጅ ሲጭን እጅ ከፍንጅ ተይዞ በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
‎የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የክስ ማስረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እና በ5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
‎ይህ የቅጣት ውሳኔ ለሌሎች መሰል የጥፋት ድርጊት ለሚፈጽሙ አካላት አስተማሪ እንዲሆን ታስቦ የተላለፈ ነው!"
‎የሙስና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል እና አጥፊዎችን ወደ ሕግ ፊት ለማቅረብ እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን ኃላፊነትና ድርሻ ሊወጣ ይገባል።

  ✅የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ግንቦት 24/9/2018 ዓ/ም ለሚካሄደው 7ኛው  ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ በምርጫ ዙሪያ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ለማየት...
31/05/2026



የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ግንቦት 24/9/2018 ዓ/ም ለሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ በምርጫ ዙሪያ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ለማየት ስል ተዘዋዋሪ ችሎት የሚካሄድባቸው ሁሉም ቦታዎች እና በመደበኛው ፍርድ ቤት ግቢ አቋቁመን ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን መሆኑን
እንገልፃለን ።
የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት
ፍትህ የሰፈነባት ከተማ በጋራ
እውን እናደርጋለን 🙏

👇
የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

27/05/2026
በሕጻናት ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ ለዳኞችና ለማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ‎‎​ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 15/2018 ዓ.ም‎‎​ስልጠናው የተዘጋጀው ሕጻናት ከሕግ ጋር በሚገናኙበት ወቅ...
23/05/2026

በሕጻናት ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ ለዳኞችና ለማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

‎​ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

‎​ስልጠናው የተዘጋጀው ሕጻናት ከሕግ ጋር በሚገናኙበት ወቅት መብታቸውና ደህንነታቸው በተሟላ መልኩ እንዲጠበቅና የፍትህ ስርዓቱ የሕጻናትን ሥነ-ልቦናዊ ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ለማስቻል ነው።

‎​በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አንዱአለም አምባዬ ሕጻናት በባህሪያቸው ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ የሚሹ በመሆናቸው፣ በሕጻናት ችሎት የሚሰሩ ዳኞችም ሆኑ ማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ከህግ እውቀት ባለፈ በሕጻናት መብቶች ስምምነቶች፣ በሥነ-ልቦና አያያዝ እና በማህበራዊ ድጋፍ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

‎​በስልጠናው "የሕጻናት መብት ጥበቃ ላይ የሕግ ማዕቀፎችን በሚመለከት" እና "በፍርድ ቤቶች የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ያላቸው ሚና" በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ የስልጠና ሰነዶች ቀርበዋል።

‎​በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ክቡር አቶ ጰጥሮስ ብንኤ ፣ ክቡር ዳኛ አቶ አለማየሁ አልታዬ እና ክብርት ትህትና ያዕቆብ መድረኩን በጋራ መርተውታል።

‎​በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፤ የተገኘው እውቀት በችሎት ውስጥ የሚደረጉ ሂደቶችን ይበልጥ ለሕፃናት ምቹ (Child-friendly) ለማድረግና ፈጣንና ቀልጣፋ ፍትህ ለመስጠት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

‎የተለያዩ ወቅታዊ የፍርድ ቤት መረጃዎችን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ መስፈንጠሪያዎችን በመንካት ይከታተሉን!

👇
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት / Wolaita S**o City High Court

‎ዘወትር ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
‎ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ለሕግ የበላይነት!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከወላይታ ዞን ፍትህ አካላት ጋር በመተባበር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ነው።አረካ፤ግንቦት 11/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ...
20/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከወላይታ ዞን ፍትህ አካላት ጋር በመተባበር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ነው።

አረካ፤ግንቦት 11/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከወላይታ ዞን ፍትህ አካላት ጋር በመተባበር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

የወላይታ ዞን ፍትህ አካላት ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በጋር በመተባበር "የምርጫ አለመግባባት አፈታት፣ የምርጫ ወንጀሎች ምርመራ ፣ ክስ አመራር እና ቅንጅታዊ አሰራርን በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና በአረካ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሉቀን ታደሰ እንደተናገሩት 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ዲሞክራሲና ፍትሐዊ እንዲሆን የፍትህ አካላት ጥምረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርጫ የዲሞክራሲ መገለጫ እንደመሆኑ፣ ይህ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ የፍትህ አካላት የሕግ የበላይነትን የማስከበርና የዜጎችን መብት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል አቶ ሙሉቀን።

ቅድመ ምርጫ፣ ድህረ ምርጫ እና ምርጫ ወቅት የፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግ ፣የሠላምና ፀጥታና ፍርድ ቤቶች ፍትህ የማስፈን ሚና የጎላ መሆኑን አንስተው ምርጫ የሀገር መንግሥት ግንባታ ምሶሶ ከመሆኑ አንጻር የፍትህ ተቋማት ገለልተኝነት የተጠበቀ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በምርጫ ወቅት ወንጀሎች ስከሰቱ የሰብአዊ መብት በማይጋፋ መንገድ እንዲሆንና የፀጥታ አካላት ገለልተኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸጋው ስምዖን ናቸው።

የምርጫ ወንጀሎች በመለየት ፈጣን ፍትህ እንዲሰጥ ጊዚያዊ ችሎት መዘጋጀቱን ያነሱት ኃላፊው ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን የፍትህ ተቋማት ቁርጠኝነት ወሣኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሉቀን ታደሰ፣ የወላይታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ምህረቱ ኩኬ፣የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ፍቅሬ አካለወልድ ፣የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምዖን እና የተለያዩ ወረዳ/ከተማ ፍትህ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

📢 ለሁሉም የወላይታ ዞን ነዋሪዎች እና ተገልጋዮች!የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድህረ-ገጽ በመጠቀም የመዝገባችሁን ቀጠሮ፣ የቀጠሮ ምክንያት እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ...
11/05/2026

📢 ለሁሉም የወላይታ ዞን ነዋሪዎች እና ተገልጋዮች!
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድህረ-ገጽ በመጠቀም የመዝገባችሁን ቀጠሮ፣ የቀጠሮ ምክንያት እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
🌐 ድህረ-ገጹ፦
www.whc.gov.et
ወይም “Wolaita Zone High Court” በማለት search በማድረግ ማግኘት ይችላሉ።
📝 የመዝገብ ቁጥራችሁን በማስገባት፦
✔️ የቀጠሮ ቀን
✔️ የቀጠሮ ምክንያት
✔️ ሌሎች አገልግሎቶችን ማወቅ ይችላሉ።

የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቪዲዮ ችሎት በማስጀመር አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ በማድረጉ እውቅና አገኘ።አረካ፤ግንቦት 2/2018 ዓ.ም የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቪዲዮ...
10/05/2026

የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቪዲዮ ችሎት በማስጀመር አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ በማድረጉ እውቅና አገኘ።

አረካ፤ግንቦት 2/2018 ዓ.ም የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቪዲዮ ችሎት በማስጀመር አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ በማድረጉ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የምስጋናና ዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየሠራ ባለው ተግባር የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለቴክኖሎጂ ትግበራ ትልቅ ድርሻ በመወጣቱ ነው ተሸላሚ መሆን የቻለው።

በተያያዘ ዜና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባካሄደው የተለያዩ ቴክኖሎጂ ስራዎች ማስመረቂያ መርሃግብር ላይ ነው ከተማ አስተዳደሩ ግንባር ቀደም በመሆን እውቅና ያገኘው።

10/05/2026
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መስመረቂያ መርሃ ግብር እያካሄደ ነው።የሚመረቁ ቴክኖሎጂዎች የዌብ ሳይት፣ የጉዳይ...
09/05/2026

የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መስመረቂያ መርሃ ግብር እያካሄደ ነው።

የሚመረቁ ቴክኖሎጂዎች የዌብ ሳይት፣ የጉዳይ ፍሰት አስተዳደር ሥርዓት(case flow management system) እና የቪዲዮ ኮንፈረንስ ችሎት(virtual court) ቴክኖሎጂዎች ናቸው።

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (ወዞመኮአ)

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈር ቀዳጅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን የማዘመን ብቻ ሳይሆን ተቋሙ መዘመኑን እና በሪፎርም ተግባራዊነት የፍትህ እምርታ መረጋገጡን ያሳያል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

የተሠራው ሥራ የመሰጠ፣ የአንድነት እና በጋራ የመሥራት ውጤት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ፍትህ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የህይወት ጉዳይ ነው ያሉት አቶ ቦጋለ ከወረቀት ሥራ በመላቀቅ የመዝገብ መሰወርን ጭምር ለማስቀረት ያግዛል ብለዋል።

በቴክኖሎጂ ማዘመን ህዝብን ማዕከል ያደረገ ነው ሲሉም ተናግረው ቴክኖሎጂ ግብአት እንጂ ግብ አይደለም በማለት አስረድተው ዳኞች ለፈጣሪ በመፍራት የህዝብን እንባ ለማበስ በቅንነት እና ለፍትህ በመቆም መሥራትን ይጠይቃል ሲሉ ተናግረው ሁሉም

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ የፍርድ ቤት ሥራ ከሰውም ከፈጣሪ የተሰጠ አደራ ነው ሲሉ ተናግረው ፍርድ ቤትን ማዘመን ለነገ የሚባል ተግባር አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።

ማዘመኑ የተገልጋዩን ጊዜ ገንዘብና ጉልበት ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

የዞኑ መንግሥት የተሻለ የፍትህ አገልግሎት መስጠት እንዲችል አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ሲሉ ተናግረው በቀጣይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሻለ የሥራ ቦታ አገልግሎት እንዲሰጥ የራሱ ዘመናዊ ቢሮ ለመገንባት የሚያስችል የዲዛይን ሥራ መጠናቀቁን አብራርተዋል።

በቀጣይ የሪፎርም ተግባራት ጥልቀት እያገኙ እንዲሄዱ በትኩረት ክትትል ይደረጋል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቮችን ቀድመን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጣችንን ማዘመን ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ለቴክኖሎጂ አገልግሎት እውን መሆን የድርሻቸውን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ ምህረቱ ኩኬ የፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት ዛሬ የሚመረቁ ቴክኖሎጂዎች የባለ ጉዳይን እንግልት በመቀነስ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ያቀላጥፍልናል ሲሉ ተናግረዋል።

የዳኞች እና የመዝገብ ጥምርታ ለማመጣጠን የዳኞች ቅጥር መፈጸሙንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂ ተገልጋዩ ፍትህ በጊዜ እንዲያገኝ ከማድረግ ባሻገር ከሙስና የፀዳ አገልግሎት እንድንሰጥ ያስችላል ሲሉም ተናግረዋል አቶ ምህረቱ።

ለቴክኖዎሎጂዎች አቅርቦትና ሥራ ላይ መዋል አበርክቶ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

Address

Wolaita Zone Areka City Administration
Areka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት Areka City First Instance Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category