ጨንቻ ማረሚያ ተቋም/ Chencha Prison Institution

ጨንቻ ማረሚያ ተቋም/ Chencha Prison Institution ማረምና ማነጽ እንዲሁም የታራሚዎችን ሰብአዊ መብቶች መጠበቅ

Permanently closed.
የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተፈቱ።ጨንቻ  ቀን 03/08/2018 ዓ/ም። //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የ2018 ዓ/ም በጄት ...
11/04/2026

የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተፈቱ።

ጨንቻ ቀን 03/08/2018 ዓ/ም። //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የ2018 ዓ/ም በጄት አመት የትንሳኤ በዓል ምክኒያት በማድረግ 3ኛ ዙር በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው የህግ ታራሚዎች መካከል ከጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ሙሉ ይቅርታ የተደረገላቸው ወንድ 39 ሴት -- ጠ/ድ 39 መሆናቸውን የተቋሙ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ገልፀዋል።

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ለህግ ታራሚዎች ከማህበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ወቅት በማረሚያ ተቋም ቆይታ ጊዜ የተማሩትን ትምህርት በተግባር ማሳየት ይገባቸዋል ወንጀል አስከፊ መሆኑን መኮነን ይገባቸዋል በማለት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰተዋል።

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ተወካይ ረ/ኢ/ር ሙሉቀን ያጌ ወንጀል አስከፊ መሆኑን በመጥቀስ ዛሬ የተፈታችሁ ከማህበረሰቡ ጋር ዕርቅ በመፈፀም በሰላም ልትኖሩ ይገባል በማረሚያ ቆይታችሁ የተማራችሁትን ወደ ተግባር የምትቀይሩበት ጊዜ በመሆኑ ወንጄልን ለመከላከል አንበሳውን ድርሻ ትወስዳላችሁ በማለት አሳስበዋል።

ጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለለውጥ እንተጋለን።

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትየጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመዳኅኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለ...
10/04/2026

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመዳኅኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የትንሳኤ በዓል የሕይወት ድል፣ የተስፋ መነሻ እና ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያመራ ታላቅ መልዕክት ያለው ቀን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር በመስቀል ላይ ሕይወቱን በመስጠት አሳይቶናል፤ በትንሳኤውም ሞትን ድል አድርጎ አዲስ ተስፋ አጎናፅፎና።

ዛሬ በሀገራችን በብዙ ትግል ከትናንት ጥላቻና መጠፋፋት በመላቀቅ በመደመር መንገድ ተምሳሌት ኢትዮጵያን ለመገባት የተጀመረው ብልጽግና ጉዞ ምንም ዓይነት ፈተና ቢገጥም ከዳር እንደሚደርስ እና በእውነት ተጀምሮ የቆመና በመንገድ ላይ የቀረ አንድም ነገር እንደሌለ ይህ አንዱ ማሳያ ነውና ከእውነት ጋር በመተባበር አንድነት ይበልጥ በማጠናከር የውሸት መልዕክቶችን ለአፍተም ሳናዳምጥ በቁርጠኝነት መቆም ይኖርብናል።

ይህ ታላቅ በዓል ትጋት፣ ፅናት፣ ትዕግስትና መተሳሰብ እንዲሁም አንዱ ለሌላው መረዳዳት እንዳለብን ያስተምረናል። በሕይወታችን ያጋጠሙንን ፈተናዎችና ችግሮች በአንድነትና በመተሳሰብ በመተጋገዝ እንደምንሻገር ያሳያል።

በተጨማሪም ሰላም ሲኖር በመሆኑ ማንኛውንም ኩነት መፈፀም የሚቻለውና በአከባቢያችን በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ በዓሉን እንዲያከብር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመጠየቅ፣ ያዘኑትን በማጽናናት አቅም የሌላቸው በጋራ ማዕድ በመካፈል ምንም ዓይነት ባዶነት እንዳይሰማቸው በማድረግ በዓሉን እንድናከብር በማክበር እየጠየኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር የስኬት የድል የማሸነፍ በዓል እንድሆን እመኛለሁ።

በመጨረሻም ይህ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል ለሁላችን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የደስታ እንዲሆን እየተመኙ በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ብለዋል።
መልካም የትንሳኤ በዓል!
ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ
የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ።

ሚያዝያ 2/2018 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርትኳን መንግስቱ የተመራ ልዑክ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የስራ ጉብኝት አደረገ።ጨንቻ:-  ሚያዝያ 01/2018 ዓ/ም  //የተቋሙ ...
09/04/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርትኳን መንግስቱ የተመራ ልዑክ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የስራ ጉብኝት አደረገ።

ጨንቻ:- ሚያዝያ 01/2018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//

በማረሚያ ተቋማት በመታረም ላይ የሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጥራት ያለው የተሟላ የጤና አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባ የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርትኳን መንግስቱ ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ብርትኳን መንግስቱ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የሚገኘውን ክሊኒክ ወደ ጤና ጣቢያ ለማሳደግ እየተሰራ ያለውን የማስፋፊያ ግንባታ የተመለከቱ ሲሆን አፈፃፀም ያለበት ደረጃ መልካም መሆኑ ጠቅሰዋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግሎባል ፈንድ ፕሮጄክት አስተባባሪ ዋ/ኢ/ር (ዶ/ር) ሄኖክ አበበ የዛሬ ጉብኝታችን ያቶከረው የማረሚያ ቤት ጤና አገልግሎት ከማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ለማቆራኘት ያለመ መሆኑና ታራሚዎቻችን እኩል የጤና አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባ ድጋፍ ለማድረግ ነው በማለት ገልፀዋል።

የተቋሙ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ በበኩላቸው ክሊኒኩን ወደ ጤና ጣቢያ ለማሳደ ተቋሙ አቅሙን አሟጦ እየሰራ እንደሚገኝና የሚመለከታቸው የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እንግዶችን በተቀበሉበት ወቅት ገልፀዋል።

በጎብኝቱ የክልሉ ማረሚያ ኮሚሽን በሽታ መከላከል ዳይሮክቴሬት ዳርክቴር ሲ/ር መታሰቢያ አራጋው እና የልማት ዕቅድ በጄት ዝግጅት ዳሮክቴሬት ዳይርክቴር ተመስገን ያዕቆብ ተገኝተዋል።
የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ። ለለውጥ እንተጋለ!!

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አጠቃላይ ሰራተኞች 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ።ጨንቻ:- 25/072018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//የጨ...
03/04/2026

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አጠቃላይ ሰራተኞች 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ።

ጨንቻ:- 25/072018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ለለውጥ እንተጋለን!!

03/04/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ እና የክፍያ ባለሞያዎች በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ድጋፋዊ ምልከታ አደረጉ።ጨንቻ 24/07/2018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነ...
02/04/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ እና የክፍያ ባለሞያዎች በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ድጋፋዊ ምልከታ አደረጉ።

ጨንቻ 24/07/2018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ባለሞያ አቶ ሀምሳሰው ደማ እና የክፍያ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሞገስ ጥላሁን በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የ2018 ዓ/ም በጄት አጠቃቀም ላይ ምልከታ እና የ2019 ዓ/ም የበጄት ዕቅድ ዝግጅት ምልከታ አድርገዋል።

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ። ለለውጥ እንተጋለን!

‎መጪውን የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ከወትረው በበለጠ ጥበቃ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።‎‎ጨንቻ 24/07/2018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//‎‎ የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት...
02/04/2026

‎መጪውን የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ከወትረው በበለጠ ጥበቃ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።

‎ጨንቻ 24/07/2018 ዓ/ም //የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት//

‎ የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ከወትረው በበለጠ የጥበቃ ስራ ማጠናከር እንደሚገባ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ገለፁ።

‎የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ የተቋሙን አጠቃላይ የፖሊስ አባላትና ሲቭል ሰራተኞችን በወቅታዊ ሁኔታና ጥበቃን ማጠናከር ላይ ያለመ ውይይት አድርገዋል።

‎መጪው የበዓል ወቅት በመሆኑ ከውጭና ከውስጥ ሊከሰት የሚችልን አደጋ ከመከሰቱ በፊት አስቀድመን መከላከል ስለሚገባ የጥበቃ ፣የእጄባ እና የፍተሻ ስራ ከወትረው በላይ ማጠናከር ይገባል በማለት ገልፀዋል።

‎በተጨማሪ ከሰራተኞች ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡ ሲሆን 7ኛውን ሀገራ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብታችንን ለመጠቀም ሁሉም ሰራተኛ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል።

‎ የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም። ለለውጥ እንተጋለን!

የህግ ታራሚዎች የዕርቅ ሰነድ ትክክለኛነቱን ማጣራትና ምልከታ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ተካህዷል።ጨንቻ:- መጋቢት 10/2018 ዓ/ም/የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት/በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ...
19/03/2026

የህግ ታራሚዎች የዕርቅ ሰነድ ትክክለኛነቱን ማጣራትና ምልከታ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ተካህዷል።

ጨንቻ:- መጋቢት 10/2018 ዓ/ም/የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት/

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወንድማገኝ ሰለሞን የተመራ የህግ ታራሚዎች የዕርቅ ሰነድ አጣሪ ኮሚቴ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በመገኘት የይቅርታ ተጠቃሚ ለመሆን ከተጎጂ ቤተሰብ ጋር ዕርቅ በመፈፀም የዕርቅ ሰነድ ያቀረቡ ታራሚዎችን ሰነድ አጣራ።

የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወንድማገኝ ሰለሞን ይህ የዕርቅ ሰነድ የማጣራት ስራ ዋናነኛነ ሀሰተኛ እና የተጭበረበሩ ሰነዶች በመለየት በትክክል ከተጎጅ ቤተሰብ ጋር የታረቁትን መንግስት የሚሰጠውን ይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው በማለት ገልፀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ፍሰሐ በበኩላቸው የዕርቅ ሰነዶችን የማጣራት ስራ ከወትረው ለየት ባለ መልኩ እስከ ታችኛው እርከ ወደ ተቋማት በመውረድ ተባዳይና በዳይን በአካል በማግኘት ከቀበሌያት የመጡ የዕርቅ ሰነዶች ትክክል ስለመሆናቸው በቪድዮ በማስደገፍ ለለሚመለከተው በማቅረም ትክክለኛ ሰነድ ያቀረበ የህግ ታራሚ ይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆንና አጭበርባሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪ ኮሚቴው በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም እየተሰሩ ያሉትን የልማት ስራዎች በተቋሙ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ አማካይነት ጉብኝት አድርገዋል።

ጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ። ለለውጥ እንተጋለን!!

መጋቢት 10 በዚህች ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል የተገለጠበትና የተገፕበት ዓመታዊ ክብር በዓል በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን በጨንቻ ማረሚያ ፓሊስ ተቋም መስቀለ...
19/03/2026

መጋቢት 10 በዚህች ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል የተገለጠበትና የተገፕበት ዓመታዊ ክብር በዓል በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን በጨንቻ ማረሚያ ፓሊስ ተቋም መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ያን በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

መጋቢት 10/2018 ዓ/ም የጨንቻ ማረሚያ ፓሊስ ተቋም ህዝብ ግንኙነት።

በበዓሉ የተገኙት የጨንቻ ወረዳ እና ቆጎታ ወረዳዎች ቤተክህነት አስዳዳሪ ሊቀ ብራናት ዳዊት መርዕድ ፣ የአራቱ አድባራት አስተዳዳሪ መላከ ብስራት መንግስቱ እዳላማው በተቋሙ ተገኝተው ከህዝበ ምዕመናን እና ከህግ ታራሚዎች ጋር በዓሉን አክብረዋል።

ሊቀ ብራናት ዳዊት መርዕድ እንደገለፁት ከዋዜማው አንስቶ ሌሊት በማህሌቱ ዛሬ ደግሞ ታቦቱን በማንገስ በመጨረሻ እስከ ቅዳሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ ያለ አንዳች ችግር በሰላም እንድንፈፅም ለተባበራችሁ የተቋሙ ማህበረሰብ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በአባታዊ ቡራኬ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል።

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በጋጮ ባባ ወረዳ በማዞ ዶይሳ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ምግብ ነክ ቁሳቁስና አልባሳት  ድጋፍ አደረገ።‎‎​ጨንቻ፦...
15/03/2026

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በጋጮ ባባ ወረዳ በማዞ ዶይሳ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ምግብ ነክ ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

‎​ጨንቻ፦ 6/7/2018 ዓ.ም የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት።

የ‎ጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በጋጮ ባባ ወረዳ በማዞ ዶይሳ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ምግብ ነክ ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ አደርጓል።

‎በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለፁት የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ለተጎጅዎች ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል።

‎​ለተጎጅዎች የሚውል ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ፣ ብርድ ልብስ፣ ፍራሽ የተለያዩ አልባሳት እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና የበቆሎ ዱቄትና ስንዴ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ገልፀዋል።

በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በሚችለው አቅም ለተጎጅዎች የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

‎ድጋፉን የተቀበሉት የዞኑ ም/አስተዳዳሪና ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀኪሜ አየለ ላሳዩት አጋርነትና ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ።ለለውጥ እንተጋለን!

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የታራሚዎችን ወቅታዊ ፀጥታና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንድሁም ልከናውን የሚገቡ ቅደሜ ጥንቃቄ ሊደረግ በሚገባቸው ተግባራት ላይ በተዘጋጄው ሰነድ ላይ በጨንቻ ማረ...
11/03/2026

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የታራሚዎችን ወቅታዊ ፀጥታና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንድሁም ልከናውን የሚገቡ ቅደሜ ጥንቃቄ ሊደረግ በሚገባቸው ተግባራት ላይ በተዘጋጄው ሰነድ ላይ በጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ውይይት ተደረገ ።

ጨንቻ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የህዝብ ግንኙነት)

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የታራሚዎችን ወቅታዊ ፀጥታና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ልከናውን የሚገቡ ቅደመ ጥንቃቄ ላይ ያቶከረ ሰነድ የተቋሙ ጥበቃ ደህንነት ታራሚዎች አስተዳደር ድቭዥን ኃላፊ የሆኑት ኮ/ር አበባው ሶርስ አቅርበዋል።

በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ በማረሚያ ተቋማችን ላይ ልፈጠሩ የሚችሉ ደህንነት ስጋቶች ቢያጋጥሙ ለመከላከል የሚያስችል የጥንቃቄ ቅድሜ ዝግጅት ማድረግ እና ሁሉም የስራ ክፍል መንግሥት የጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ዝግጅት እንድኖረን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ እንደሆነ የተቋሙ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ገልፀዋል።

ወቅታዊ ሠላምና ፀጥታ ጋር በተገናኘ በጥበቃ ደህንነት ስራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ማንኛውም በማረሚያ ፖሊስ ተቋም እርምት ላይ ያለ የህግ ታራሚ በማረሚያ ተቋም ውሰጥ እያለ ማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት ማራመድ በመደገፍ ወይም በመቃወም እንድሁም መልዕክት በማስተላለፍ ወይም ተቃውሞ እንቅስቃሴ የማድረግ መብት እንደሌለው በቂ ግንዛቤ ሰነዱ ፈጥራል ።

በስተመጨረሻ የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ም/ኮሚሽነር አጥናፉ አሰፋ ከተሰብሳቢዎች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተጨማሪ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በአከባቢያችን መከሰቱን አስታውሰው ሊደርስ ከሚችል የጎርፍ አደጋ መከላከልና የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች መጠረግ እንደሚገባ የስራ መመሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል ።

የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ።ለለውጥ እንተጋለን።

ከጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የተሰጠ የሀዘን መግለጫ።​በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህ...
11/03/2026

ከጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የተሰጠ የሀዘን መግለጫ።

​በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የተሰማውን ጥልው ሀዘን ይገልፃል።

​በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ የአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች ወዳጆችና ለመላው የዞኑ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

​የጨንቻ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም።

Address

Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጨንቻ ማረሚያ ተቋም/ Chencha Prison Institution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share