የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው።

በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ በ 24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ተመረቀ‎አርባምንጭ ግንቦት 7 /2018 ዓ.ም ‎በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ካራ ቆ...
15/05/2026

በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ በ 24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ተመረቀ

አርባምንጭ ግንቦት 7 /2018 ዓ.ም ‎በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ካራ ቆርጮ የተገነባዉ የአንደኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ኤካል ነትር ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ እና የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሳሙኤል ጋርሾ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

‎በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር ማዕከሉ በክልሉ ቆላማ አከባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) ፕሮጀክት ድጋፍ መገንባቱን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱ እንዳስደሰታቸዉ ኃላፊዉ ገልፀው ይህም መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረትና የኢኮኖሚ አካታችነት ማሳያ መሆኑን አስሴድተዋል።

‎አያይዘውም በካራ ቆርጮ የተገነባው ዘመናዊ ደረጃ አንድ የእንሰሳት የገበያ ማእከል ህገወጥ የንግድ ግብይትን ከማስቀረት እና ከመቆጣጠር አንፃር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል ።

‎በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የካራ ቆርጮ የአንደኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል በሐመር ወረዳ በኛንጋቶም ወረዳ ኬንያ ቱርካና ደረጃ የሚታየውን የገበያ መሰረተ ልማት ስብራት ለመሙላት ትስስሩን ለማጠናከር የተያዘው ዕቅድ አካል መሆኑን ተገልጿል ።

‎የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሳሙኤል ጋርሾ እንደገለጹት፣ የገበያ መሰረተ ልማት "ስብራትን" መጠገን የንግድ ትስስርን ማጠናከር በመንግስት የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ውስጥ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የህብረተሰብ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፣ ማዕከሉ ለደቡብ ኦሞ ዞን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ በራፂ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ የተገነባውን የቆቃ መብራት ዝርጋታና የመንገድ ፕሮጀክት ...
15/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ በራፂ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ የተገነባውን የቆቃ መብራት ዝርጋታና የመንገድ ፕሮጀክት መርቀው ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ክፍት አደረጉ

አርባምንጭ ፤ግንቦት 7/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፌ-ጉበኤ የተከበሩ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ ለሎች የክልል፤የዞንና የወረዳ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ በራፂ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ የተገነባው የቆቃ መብራት ዝርጋታና ከገሊላ-ዋላ-ራፂ የመንገድ ፕሮጀክት ተመርቋል።

በራፂ ማዘጋጃ ከተማውና በአከባቢው ማህበረሰብ ለረጅም አመታት መልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ሲስተዋል የነበረው የመብራትና የመንገድ ጥያቄ በፌዴራልና በክልል መንግስት ብሎም በዞንና በወረዳ የጋራ ቅንጅት በተደረገው ሁለቱም ፕሮጀክቶች አልቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

በመሆኑም የለውጡ መንግስት ለማህበረሰቡ እያዳረሰ ካለው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የመብራት መስመር ዝርጋታና መንገድ ልማት ፕሮጀክት ነው። ይሄም ዛሬ ላይ ተጨባጭ ፍሬ አፍርተው ለህዝብ አገልግሎት በመብቃት ላይ ይገኛል።

በምርቃ መርሃ-ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተካለኝ ጋሎ፤የኣሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፤የወረዳውና የገሊላ ከተማ አስተዳደሩ ባለድርሻ አካላት ፤የአከባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘገባው የወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ የተገነባውን ከገሊላ-ጎዛ መንገድ የሳላ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት መርቀው ለአገ...
14/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ የተገነባውን ከገሊላ-ጎዛ መንገድ የሳላ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ

አርባምንጭ ፤ግንቦት 06/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ የተገነባውን ከገሊላ-ጎዛ መንገድ የሳላ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት ምረቃ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በወረዳው አላ ጊቻ ፤ሻንጋማ ፃክ፤ዶላ ማሽቶል፤ጎዛ ባልክሽንና ለሎች ቀበሌያት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ከገሊላ-ጎዛ መንገድ የሳላ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት የዘመናት የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየው ጥያቄ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

ይሄም ተጠቃሚውን ማህበረሰብ በማህበራዊ ፤ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ስስተዋል የነበረውን ችግር በውኑ የቀረፈ እንደመሆኑ አሁን ላይ ህዝቡ ያለምን ስጋት የራሳቸውን ምርት ለገቢያ ከማቅረቡም ባለፈ ህዝብ ለህዝብ የሚገናኙበትን መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረም ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉበኤ ክብር አቶ አለማየሁ ባውዲ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተካለኝ ጋሎ፤የኣሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፤የወረዳውና የገሊላ ከተማ አስተዳደሩ ባለድርሻ አካላ፤የአከባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው :- አፈ ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ ግንቦት 05/2018 ዓ.ም የጂንካ ግብርና...
13/05/2026

የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው :- አፈ ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ

ግንቦት 05/2018 ዓ.ም

የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ማገዙን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አለማየሁ ባውዲ ገልጸዋል።

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አለማየሁ ባውዲና ሌሎች አመራሮች የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት አፈ ጉባኤው እንዳሉት፣ የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል የአርሶና የአርብቶ አደሩን ችግር የሚፈቱና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው።

ማዕከሉ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው የጥናትና ምርምር ሥራ በክልሉ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ገልጸዋል።

ማዕከሉ ያፈለቃቸውን የግብርና ቴክኖሎጂዎች ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ በማውረድ ግብርናውን ለማዘመንና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንም አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ወላይቴ ቢቶ በበኩላቸው፣ የምርምር ማዕከሉ ተግባር በተለይም በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ልማት የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ልማት የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ በማስፋት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ማዕከሉ የጀመረውን እገዛ ሊያጠናክር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዮት ሙላቴ (ዶ/ር) የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ እያገዘ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ቀደም ሲል በሰብል ልማት በሄክታር ከ30 ኩንታል ያነሰ ምርት ይገኝ እንደነበር አስታውሰው፣ የምርምር ማዕከላት የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ማላመዳቸውን ተከትሎ በሄክታር ከ40 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

ለውጤቱ በአነስተኛ ቦታ ብዙ ምርት ማግኘት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ ሌላው ምክንያት መሆኑንም ጠቅስዋል።

እንደ አብዮት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ማዕከሉ የሩዝ ምርት ባልተለመደባቸው አካባቢዎች ጭምር የሩዝ ልማትን በማላመድና በማስፋፋት ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል።

የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተርና የሰብል ተመራማሪ ተክሌ ዮሴፍ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ማዕከሉ የተጣለበትን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከማዕከሉ የሚወጡ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የምርምር ውጤቶችን በአርሶና አርብቶ አደሩ መሳ በማስፋት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደተቻለም አመልክተዋል።

ማዕከሉ በተለይም በዝናብ አጠር አካባቢዎች በመስኖ የሚለሙ እና ምርትን በእጥፍ የሚያሳድጉ የሰብል ዝርያዎችን እያላመደ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በአርብቶ አደሩ አካባቢ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል ብለዋል ።

ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የቀይ አፈር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት  ተመረቀ ግንቦት 04/2018 ዓ.ም መላው የሀገሪቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ...
12/05/2026

ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የቀይ አፈር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተመረቀ

ግንቦት 04/2018 ዓ.ም

መላው የሀገሪቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ እስኪሆኑ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም የኢፌድሪ ዉሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ገልጿል

የኢፌድሪ ውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ድኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዜጎችን የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መላው የሀገሪቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ እስኪሆኑ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የገለፁት ሚንስትር ድኤታዉ የቀይ አፈር ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለቀጣይ 20 ዓመታት ለህብረተሰቡ በቂ አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው ብለዋል።

የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ የክልሉ መንግስት ባለፉት 8 ዓመታት ለህብረተሰቡ ማህበራዊ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ ባከናወነው መጠነ ሰፊ ስራ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በርካታ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ጥያቄዎች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው ደረጃ በደረጃ ምላሽ የመስጠት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝን ውሃ የልማቶች ሁሉ ቅድሚ ልማት መሆኑን ገለፀው ይህን ልማት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ አበክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የቀይ አፈር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል መገንባቱን የገለፁት የቢሮው ኃላፊ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ ከ15 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን የገለፁት ኢንጂነር አክሊሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ የድእሻቸውን የተወጡ አካላትን አመስግነዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ በከተማዉ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንደነበር አስታውሰዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀርፍም አብራርተዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ለማስቻል ከፍተኛ ሀብት ከመፍሰሱ ባሻጋር ብዙ ውጣ ውረድ መታለፉን የገለፁት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጥ በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሃንስ ጋሻው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ፕሮጀክቱ የህብረተሰቡን ከፍተኛ ችግር እና በውሃ ወለድ በሽታ የመጠቃት ዕድል ከመቀነስ ባሻገር የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 42 በመቶ እንዳደርስ አስችሏል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ኃላፊዎች አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ ግብርም አከናውነዋል።

በክልሉ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ እና 180 ሺህ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ5 ከተማዎች የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ምረቃ መርሃ ግብር እየተካሄደ እንደሚገኝም ይታወቃል።

ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የተጠርጣሪ ማቆያና የቢሮ ህንጻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት  አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና ...
09/05/2026

ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የተጠርጣሪ ማቆያና የቢሮ ህንጻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በተገኙበት በደማቅ ሥነ ስርዓት በይፋ ተመረቀ

በማህበረሰብ ተሳትፎ በተገነባው ህንጻ ምረቃ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ የጸጥታ ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።

በህዝብ ተሳትፎ የተገነባው የጂንካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ለዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የፖሊስ ተቋም በአዲስ መልክ መቀየር ያስችላል ተብሏል።

ከ21 ሚሉዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው ህንጻ በልዩ የባዛር ዝግጅት በድምቀት የመረቁት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በጋራ በመሆን ነው።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ አመራሮች በልዩ የባዛር ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት ታድመዋል።

ለ3 ቀናት በሚቀጥለው የባዛር ዝግጅት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን ይህም የተቋሙን የውስጥ ግብዓት ለማሟላት በማለም የተሰናዳ መሆኑን ከአስመራቂ ኮሚቴ አመራሮች መረዳት ተችሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ በላይ ወጪ የተገነቡ የ5 ከተማዎችን መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ሊያስመርቅ ነውአርባምንጭ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ...
06/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ በላይ ወጪ የተገነቡ የ5 ከተማዎችን መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ሊያስመርቅ ነው

አርባምንጭ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ከ180 ሺህ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የአምስት ከተማዎችን የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ለማስመረቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ክቡር ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለምረቃ የተዘጋጁ እነዚህ ፕሮጀክቶች ከግንቦት ወር ጅማሮ ባሉት ቀናት ውስጥ የምረቃ መር
ግብራቸው ይከናወናል።

ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑት ፕሮጀክቶች በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ፣ በወላይታ ዞን የሆቢቻ ወረዳ ብዝሀ-ቀበሌ፣ በጋሞ ዞን የዘፍነ ከተማ፣ በደቡብ ኦሞ ዞን የቀያፈር ከተማ እንዲሁም በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ለእነዚህ ፕሮጀክቶች ግንባታ ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ የፌዴራል፣የክልል እና የዞን መንግስት መዋቅሮች ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያስገነቧቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሉ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት፤ ቢሮው ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ አቅሙ ከአመት አመት እያደገ መምጣቱን የገለጹት ኢንጂነር አክሊሉ፤ ይህም በአዲሱ ክልል የተመዘገበ ትልቅ ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በተመሳሳይ ሁኔታ የአምስት ከተማዎች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ያስታወሱት ኃላፊው፤ ይህም በክልሉ የውሃ ሽፋን ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በተያያዘም እንደ ቢሮው ሪፖርት ባለፉት አሥር ወራት ብቻ በከተማና በገጠር 65 የውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ከ321 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በሌላ በኩል ተገንብተው አገልግሎት የጀመሩ የውሃ ተቋማት ከመሰረታዊ አገልግሎት ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

ለዚህም ውጤታማነት ከከተማ ውሃ አገልግሎቶች፣ ከገጠር የውሃ ማህበራትና ፌዴሬሽኖችን ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በዚህም ቢሮው ማህበራትንና ፌደሬሽኖችን የማደራጀት፣ በክህሎት ስልጠናዎች አቅም የማጎልበትና ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ መቆየቱንም ኃላፊው ገልጸዋል።

ይህም ለተቋማት ባለቤትን የመፍጠር፣ ተቋማቱ ራሳቸውን ችለው ለአከባቢው ማህበረሰብ የገቢ ማስገኛ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለዘሌቄታዊ አገልግሎት ሚናው የጎላ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በአዲሱ የስራ መደቦች ጥናት መሠረት ድልድል ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን አሰመልክቶ ከሠራተኞቹ ጋር በሠራተኛ ድልድል ዙሪያ ተወያዩ...
04/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በአዲሱ የስራ መደቦች ጥናት መሠረት ድልድል ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን አሰመልክቶ ከሠራተኞቹ ጋር በሠራተኛ ድልድል ዙሪያ ተወያዩ

አርባምንጭ ​ሚያዝያ 26/2018 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የአዲሱ የክልል ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሠራተኛ ድልድል መመሪያ ቁጥር 145/2018ን አስመልክቶ ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄዷል።

አዲሱ የመዋቅር ማሻሻያና መሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት (BPR) መነሻ በማድረግ በምክር ቤቱ ደረጃ በአዲሱ የሠራተኞች ድልድል ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ገልጿል።

​የምክር ቤቱ ምክትል ኃላፊና ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማሩ ሀቱዬ በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፦ይህ የድልድል ሂደት የምክር ቤቱን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣትና የሰው ኃይል አጠቃቀሙን ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ መኖሩን ተናግሯል።

አቶ አማሩ አክሎም የድልድል መመሪያው ግልጽነትን የተከተለና በታማኝነት የአሰራር ሥርዓትን በማይጣረዝ መልክ በግልጽነት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚከናወንም አብራርተዋል።

አዲሱ የሠራተኞች ድልድል በእውቀትና በጥበብ ተቋሙን በሚመጥን መልኩ ይከናወናል ያሉት አቶ አማሩ፦ይህንን ሥራ በቅርቡ ለማጠናቀቅ መታቀዱን በመገለጽ እንደ ተቋም የተጀመረው አዲሱ የሠራተኞች ድልድል ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ አሳስበዋል።

በክልሉ ምክር ቤት የሰው ሀብት ሥራ አመራር ​አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥበቡ በቀለ በኩል ዝርዝር መመሪያውን አስመልክቶ አጠቃላይ የምክር ቤቱ ሠራተኞች በተገኙበት ለውይይት በሚመች መልክ ማብራሪያና ገለፃ አድረጓል።

አዲሱ የሠራተኞች ድልድል የትምህርት ዝግጅትና ሥራ ልምድ፣ የማኅደር ጥራት፣ የአፈፃፀም ምዜና ውጤት፣ ለደረጃው ያለው ቅርበት፣ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ሰርቲፍኬት እና ሌሎች የመወዳደሪያ መስፈርቶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን አቶ ጥበቡ አብራርቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሠራተኞች ድልድል አዲሱ የመዋቅር ማሻሻያና መሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት በየተቋማቱ ክልሉን የሚመጥን የሰው ኃይል አደረጃጀት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግሯል።

በመጨረሻም የተቋሙን ሠራተኞችን የሚወክሉ 2 የድልድል ኮሚቴ እና 2 የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን በማዋቀር መድረኩ ተጠናቋል።

የነዳጅ አቅርቦት ማነስን ምክንያት በማድረግ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስተጓጎል በሚሞክሩ አካላት ላይ አስተማሪ ተመጣጣኝና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ  መምራት እንዳለበትአፈ ጉባኤ አ...
29/04/2026

የነዳጅ አቅርቦት ማነስን ምክንያት በማድረግ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስተጓጎል በሚሞክሩ አካላት ላይ አስተማሪ ተመጣጣኝና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መምራት እንዳለበት
አፈ ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ አሳሰቡ

አርባምንጭ ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በወቅታዊ የነዳጅ አቅርቦት ሥርጭት እና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላይ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ትራስፖርትና መንገድ መሠረተ ልማት ቢሮ ጋር በክልሉ ምክር ቤት ጠርተው መክረዋል።

በክልላችን በሁሉም ከተሞች ህግ በማስከበር ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡን በማስተባበር በየደረጃው ያሉትን ግብረሃይል አካላትን አቀናጅቶ ሥምሪት በመስጠት ወቅታዊ የትራንስፖርት እና ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ ሂደቱን በህግ አግባብ ማስቀረት እንዳለበት አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ አሳስበዋል።

ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ምክንያት በማድረግ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስተጓጎል በሚሞክሩ አካላት ላይ የተቋማት ኃላፊዎች ህብረተሰቡን ከወቅታዊ ችግር ለመላቀቅ በአሠራር መመሪያ መሠረት ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ሊመራ እንደሚገባም አፈ ጉባኤው አጽንኦት ሰጥቶ ተናግረዋል።

ቢሮዎቹ በተለይ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቁጠባና በአግባቡ እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራ፣የናፍጣና የቤንዚን አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎች በፍትሃዊ መንገድ ስርጭት እንዲካሄድ፣በብላክ ማርኬት ተዘዋውሮ የሚሸጡ ህገ ወጥ አካላት ላይ ከህግ ተቋማት ጋር ተቀናጅተው መልክ የማስያዝ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አንስተዋል።

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለህዝብ ውግንና ስባል የአግልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ወቅቱን በሚመጥን መልክ የህብረተሰቡን ችግር በማዳመጥ የፍጆታ እና የሸቀጦች ዋጋ ከልክ በላይ ጭማሪ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ማህበራት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፈ ጉባኤው በአጽንኦት አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህንን ግዛዊ ችግሩን ለመቅረፍ ከትራንስፖርት ማህበራትና ከባለንብረቶች ጋር በጋራ በመወያየት በተዘጋጀ ሁኔታ በደንቡ መሠረት ህገ ወጥ ድርጊቱን የሚፈፅሙ አካላት ላይ ቢሮው በተቀናጀ መልክ በየደረጃ ያሉ ተቋማት በአቅርቦትና ስርጭት፣ ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ፣የብላክ ማርኬቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ እንዲመራ መመሪያ ተዘጋጅቶ መሰጠቱን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰሎሞን ተናግረዋል።

የነዳጅ እጥረትን ምክንያት በማድረግ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ ተሽከርካሪዎች ላይ በሚወስደው ህግ የማስከበር ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

ማደያ የሌላቸው አንዳንድ የዞንና የወረዳ ከተሞች ላይ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ስላለ ቢሮው ግዛዊ መፍትሔ በማበጀት የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን ተጠቅሞ ኮሚቴ በመዋቀር እና ሥምሪት በመስጠት ችግሩን ለመፍታት ከታችኛው መዋቅሮች ጋር በቅንጅት መስራት ላይ መሆኑን ወይዘሮ ሰናት አብራርቷል።

የትራስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የትራስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ጌቦ በበኩላቸው፦ የአቅርቦትና የስምሪት ችግሮችን በየደረጃው ካሉ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት መስራት በእጅጉ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል፡፡

ህግ በማስከበር ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡ በመንግሥትን ጎን ሆኖ በአገባቡ መርጃ በመስጠት ሂደት ላይ ተግዳሮት እየገጠሙ መሆኑን ኃላፊው ጨምሮ ገልጸዋል።

የደቡብ  ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎች ተከታታይ ለሁለት ቀናት ስካሄድ የቆየው የአስፈፃሚ ተቋማትን የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ ክንው...
28/04/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎች ተከታታይ ለሁለት ቀናት ስካሄድ የቆየው የአስፈፃሚ ተቋማትን የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል

አርባምንጭ፡ ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም በክልሉ ምክር ቤት አራቱም ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚከታተሏቸውን የአስፈፃሚ ተቋማትን የ9 ወር ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም የፅሁፍ ሪፖርት ከተመላላሽ ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ለሁለት ቀናት ስካሄድ የነበረው ግምገማ መድረክ መጠናቁን ቋሚ ኮሚቴዎች ገልጿል።

የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የፕላን መሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች፣ የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች እንዲሁም የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በስራቸው የሚገኙ ሁሉም የአስፈፃሚ ተቋማት የ2018 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ አጠናቋል።

በመሠረተ ልማት ዘርፍ፦በክልላችን በሁሉም አከባቢዎች በገጠርም በከተማ እየተሰሩ ያሉ የልማት አውታሮችን፣ የአርሶአደሩና የአርብቶ አደሩን የልማት ተጠቃሚነት፣የምርት ተደራሽነት፣የከተማ መሠረተ ልማት ሥራዎች፣ ወጪ ቆጣቢ የበጀት አጠቃቀም ሁኔታና ብልሹ አሰራሮችን የማረም አሰራር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መገምገሙን ቋሚ ኮሚቴዎች አስረድቷል።

በማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎች፦በት/ት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ፣በት/ት ቤቶች የሚገባ አገልግሎት፣በጤና ኬላዎች፣በጤና ጣቢያቸውና በሆስፒታሎች የህክምና ጥራትና የመድኃኒት አቅርቦት፣በክረምቱ የወባ ወረረኝ ለመከላከል የሰጥበት ትኩረት፣የአቅመ ደካማ ህብረተሰብ ክፍሎችን በበጎ አገልግሎት የማገዝ ተግባር እና ሌሎችም የሴቶችና ሕፃናት ጉዳዮችን በማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መገምገሙን አብራርቷል።

በመልካም አስተዳደር ዘርፍ፦ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ሥራዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣የሰባዊ መብት አያያዝ ጉዳዮች፣ የፍትህ ተደራሽነት ሥራዎች እና የፀጥታ ጉዳዮችን ትኩረት ሰጥቶ ማየት መቻሉንም ጠቁመዋል።

የክልሉን የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና የሠላም ግንባታ ሥራዎችን እንዲሁም እምቅ የቱባ ባህሎችና የብሔረሰቦችን ቋንቋ እሴት የማስተዋወቅ ሥራዎች በዘገባና በፕሮግራም በተሻለ ሁኔታ በዘጠኝ ወሩ ማስተዋወቅ መቻሉን አንስቷል።

አስፈፃሚ ተቋማት በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማስመዝገብ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት አበረታች መሆኑን ቋሚ ኮሚቴዎቹ ጠቅሰው፦ዘላቂ ሠላምን በማስፈን የፊታችን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ተቋማት የበለጠ ጠንክሮ በቅንጅት መስራት እንዳለበት አጽንዖት ሰጥቶዋል።

Address

Arba Mintch

Telephone

+251951450475

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share