Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት

Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት ❤ Give blood save life ❤

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አርባ ምንጭ ከቅርንጫፍ ጋር በመተባበር  የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።‎‎አርባ ምንጭ ነሀሴ 1...
23/08/2026

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አርባ ምንጭ ከቅርንጫፍ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።

‎አርባ ምንጭ ነሀሴ 17/2018 (የአርባ ምንጭ)

‎መርሃ-ግብሩ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግቢ "እያንዳንዱ ለጋሽ ህይወት አዳኝ ነው" በሚል መሪ ቃልም የተከናወነ ሲሆን በሂደቱም ለተቋሙ ሠራተኞች ስለ ደም ልገሳ ሠፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ከተሠጠ በኋላ የደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ የቀጠለ ሲሆን በዚህም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሹፌሬ ሙሳን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

‎የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ተቋሙ መረሃ-ግብሩን በማመቻቸት ላደረገው መልካም ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ ሁሉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

‎ድንቅ ተሞኩሮ ነው የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ሙስሊም ወጣቶች ከአንዋር መስጂድ የወጣት ጀማልን አራአያ በመከተል ከዚህ ቀደም በአርባ ምንጭ ከተማ የተለያዩ መስጂዶች ያካሄዷቸዉን የደም ልገሳ ...
22/08/2026

‎ድንቅ ተሞኩሮ ነው የአርባ ምንጭና አካባቢዋ ሙስሊም ወጣቶች ከአንዋር መስጂድ የወጣት ጀማልን አራአያ በመከተል ከዚህ ቀደም በአርባ ምንጭ ከተማ የተለያዩ መስጂዶች ያካሄዷቸዉን የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ካለፈው ጊዜ በተሻለ በማስለገስ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ በጠንካራና ትንታገግ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ሙሉ እምነት አለን ፡፡

21/08/2026

#ሰበር ዜና #

‎ከቀን 16-17/12/2018 ዓ.ም ሊካሄድ የታሰበዉ መርሃ-ግብር ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ በመሆኑ በቀጣይ ትክክለኛዉን ቀን የምናሳዉቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን ።

 # አስደሳች ዜና #‎‎የአርባ ምንጭ ደምና ሕ/ህ/ባ/አገልግሎት ከኢትዮጵያ ስኳር ሕመም ማህበር፣ከአርባ ምንጭ ስኳር ሕመም ማዕከል፣ ከአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት...
20/08/2026

# አስደሳች ዜና #

‎የአርባ ምንጭ ደምና ሕ/ህ/ባ/አገልግሎት ከኢትዮጵያ ስኳር ሕመም ማህበር፣ከአርባ ምንጭ ስኳር ሕመም ማዕከል፣ ከአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ከተማ ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር በአይነቱ ልዩ የሆነ መርሃ -ግብር አዘጋጅቷል

‎ # የመርሃ-ግብር አይነቶች ፦

‎ 🌹>>> ነፃ የጤና ምርመራ
‎ 🌹>>> የደም ልገሳ
‎ 🌹>>> የምክር አገልግሎት

‎ # ቀን ፦ ከነሀሴ 16-17/2018 ዓ.ም
‎ # ቦታ ፦ ሲቀላ ጋሞ አደባባይ
‎ ፦ ሴቻ ጋሞ ባህል አዳራሽ ፊት ለፊት

‎ሁላችሁም በክብር እንዲሁም በፍቅር ተጋብዛችኋል 🙏

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገልግሎት ከገንታ በር ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን  ጋር በመተባበር  የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።‎‎አርባ ምንጭ ነሀሴ 09/2018 (የአርባ ምን...
16/08/2026

የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገልግሎት ከገንታ በር ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።

‎አርባ ምንጭ ነሀሴ 09/2018 (የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገ/ት)

‎የገንታ በር ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን በአርባ ምንጭ ከተማ ወደ ገንታ ቀበሌ መዉጫ አካባቢ ባዘጋጀው የጎዳና ላይ ወንጌል ስርጭት ጎን ለጎን የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ያከናወነች ሲሆን በዚህም ከቤተክርስቲያኗ ለአገልግሎት ከተሰማሩ ምእመናን በተጨማሪ ሌሎች በወንጌል ስርጭት አገልግሎቱ የታደሙ ምእመናንም ተሳትፈዋል።

‎የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ቤተ ክርስቲያኗ ከወንጌል ስርጭት ጎን ለጎን የደም ልገሳ መርሃ -ግብሩን በማቀናጀት ላደረችዉ በጎ ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ምእመኖች በሙሉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ ለሌሎች ብረሃን መሆን ይችላል!
15/08/2026

የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ ለሌሎች ብረሃን መሆን ይችላል!

የሌሎችን ህይወት በብርሃን ይሙሉ!
❤️❤️❤️
ህይወት በሞት አትጨርስም፤ ሌሎችን በብርሃን በመሙላት ስሟን ማራዘም ትችላለች። ዛሬ በሰጡት ውሳኔ የሌሎችን ህይወት ከጨለማ አውጥተው ወደ ብርሃን መመለስ ይችላሉ።
ሰው ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ውብ አካሉ አብሮ ይቀበራል፤ ነገር ግን የዓይን ብሌን (ኮርኒያ) በመለገስ ብቻ በሁለት ሰዎች ህይወት ውስጥ ዳግም መነሳት እና ማየት ይቻላል።

ለምን የአይን ብሌን እንለግስ?
• በዓይን ህመም ምክንያት በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ ወገኖቻችን ዳግም እንዲያዩ እድል ይሰጣል።
• ከእኛ ማለፍ በኋላም ስማችን በበጎ ስራ እንዲታወስ እና በሌሎች ህይወት ውስጥ በሰላም እንድንኖር ያስችለናል።
• ከህይወት በኋላ የሚደረግ ትልቁ የርህራሄ እና የልግስና ስራ ነው።
ብርሃን አይቅበሩ! ከህልፈት በኋላ የአይን ብሌን በመለገስ በጨለማ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን እይታ ይመልሱ።
ቃል ይግቡ! ለተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ በ8040 ነፃ የስልክ መስመር መረጃ ያግኙ!እኛንምያግኙን።

ደም በመለገስ ህይወት ለታደጉ ደጋግ ወገኖቻችን ከልብ ምሥጋና ይገባቸዋል።
15/08/2026

ደም በመለገስ ህይወት ለታደጉ ደጋግ ወገኖቻችን ከልብ ምሥጋና ይገባቸዋል።

የሕይወት አድን ጀግኖቻችን እናመሰግናለን!
*****
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሃገር አቀፍ ደረጃ በበጎ ፈቃደኞች ርብርብ 474,935 ዩኒት (87.5%) ደም በመሰብሰብ በርካታ ሕይወቶችን ማትረፍ ችለናል!
ይህ ድል የናንተ የክቡራን በጎ ፈቃደኞች ለወገን በመቆም የተገኘ ትልቅ ውጤት ነው። በፈቃደኝነት በመነሣት የብዙዎችን ተስፋ ላስቀጠላችሁ፣ ውድ ጀግኖቻችን ሁሉ ከልብ የመነጨ የከበረ ምስጋና እናቀርባለን!

ደግነታችሁ የብዙዎች ሕይወት ቀጥሏል እናመሰግናለን! ✨

በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ተከናወነ።‎‎አርባ ምንጭ: ነሀሴ 05/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ) ‎‎ከክረምት የበጎ ፈቃድ አገል...
11/08/2026

በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ተከናወነ።

‎አርባ ምንጭ: ነሀሴ 05/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት )

‎ከክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት አንዱ የሆነዉ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በቦንኬ ወረዳ ጋዜሶ ከተማ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ የወረዳ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

‎በእዚህም የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት የቦንኬ ወረዳ አስተዳደር ከዘርፉ አካላት ጋር በመቀናጀት ላደረጉት ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ ሁሉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያስተላልፋል።

ለእኒህ አንጋፋ የሀገር ባለዉለታ ወዳጆችና  ዘመዶቻቸዉ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን!!
10/08/2026

ለእኒህ አንጋፋ የሀገር ባለዉለታ ወዳጆችና ዘመዶቻቸዉ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን!!

በዚህ የክረምት የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር ላይ በመሳተፍ፦‎‎ # ለተቸገሩ ወገኖችዎ የሕይወት ሰንሰለት ይሁኑ።‎ # በጎ ፈቃደኝነትን እና አብሮነትን በተግባር ያሳዩ።‎ # ጤናማ ስ...
09/08/2026

በዚህ የክረምት የበጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር ላይ በመሳተፍ፦

‎ # ለተቸገሩ ወገኖችዎ የሕይወት ሰንሰለት ይሁኑ።
‎ # በጎ ፈቃደኝነትን እና አብሮነትን በተግባር ያሳዩ።
‎ # ጤናማ ስለመሆንዎ ነጻ የሕክምና ምርመራ ያድርጉ።

‎አርባ ምንጭ ነሀሴ 03/2018 (የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገ/ት)

‎ >>> ልብ ማለት ያለብዎት >>>

‎ # ጤናማ የደም ለጋሽ ከሆኑ
‎ # ዕድሜዎ ከ18 እስከ 65 ዓመት መካከል ከሆነ፤
‎ # ከ45 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ካለዎት፤
‎ # ደም ለመለገስ ፈቃደኛና ዝግጁ ከሆኑ:-

‎ከሰኞ እስከ እሁድ በቋሚነት ዘወትር በሥራ ስዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6:30 ከሰዓት ከ7:30 - 11:30 በአርባ ምንጭ ደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ቅጥር ግቢ በሚገኘዉ የልገሳ ማዕከል።

‎በተጨማሪም በተንቀሳቃሽነት በምንሰራባቸዉ ሴቻና ሲቀላ አደባባዮች በቀለ ሞላ እና መድሕን ህንፃ አካባቢ በመገኘት በሚተካ ደም የማይተካዉን ክቡሩን የሰው ልጅ ህይወት ይታደጉ።

Address

Arba Minch
Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share