የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት

የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ''We make a living by what we get, but we make a life by what we give." — Winston Churchill

አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነአርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ሆኗል።በ37ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግ...
19/05/2026

አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ

አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ሻምፒዮን ሆኗል።

በ37ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ማንቼስተር ሲቲ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ መድፈኞቹ አንድ ጨዋታ እየቀራቸው የዋንጫው ባለቤት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

"  ደስታ  #የወላይታውም ነው!" ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማለጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓትና የእራት ግብዣ ተደረገ​የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ...
08/05/2026

" ደስታ #የወላይታውም ነው!" ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ

ለጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓትና የእራት ግብዣ ተደረገ

​የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቀላቀሉን ተከትሎ፣ በጎረቤት ወላይታ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወላይታ ሶዶ ደማቅ አቀባበልና የክብር የእራት ግብዣ ተደረገለት።

​በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የክለቡ ስኬት ለጋሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለወላይታ ህዝብም ጭምር ታላቅ የደስታ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል።

"ደቡብ ኢትዮጵያ የስፖርተኞች መፍለቂያ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጣችኋል፤ በዚህም ታላቅ ኩራት ተሰምቶናል" ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉም ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

​ረዳት ፕሮፌሰሩ አክለውም፣ ጋሞ ጨንቻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው የፕሪሚየር ሊግ ተወካይ መሆኑ በክልሉ ስፖርት ላይ ያለውን ተስፋ እንደሚያለመልም ጠቁመዋል።

በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩና በሁለቱ ህዝቦች መካከል ጥርጣሬን ለመፍጠር የሚሞክሩ አፍራሽ መልዕክቶች፣ የሁለቱን ህዝቦች እውነተኛና ጥልቅ ግንኙነት የማይወክሉ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

​የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም በበኩላቸው "ያለ አስተርጓሚ የሚግባቡና የታሪክ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ነን" በማለት፣ ይህ አንድነት ለሀገር ብልፅግና በጋራ ለመስራት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

​የጨንቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይስማ ከተማ ከዲምቱ ከተማ ጀምሮ ለተደረገላቸው የክብር አቀባበል በጋሞ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል። ወደ ወላይታ ዞን እንደገባን የተደረገልን አቀባበል ወደ ቤታችን እንደገባን ያህል ስሜት ፈጥሮብናል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ ሁለቱ ህዝቦች በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ ሁሌም የማይነጣጠሉ መሆናቸውን መስክረዋል።

​ይህ የአቀባበል ስነ-ስርዓት በሁለቱ ዞኖች መካከል ያለውን ህዝባዊ ትስስር ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ስፖርት የሰላምና የአብሮነት ድልድይ መሆኑን በተግባር ያሳየ ሆኗል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ እየተወጡ ያሉትን ኃላፊነት አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የክልሉ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን አመል...
08/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ እየተወጡ ያሉትን ኃላፊነት አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የክልሉ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን አመልክቷል።


በክልሉ ለሚገኙ የወጣት ተወካዮች፣ ለወጣት አደረጃጀቶች፣ ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና በጂንካ ከተማ እየተሰጠ ነው።

የክልሉ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማርቆስ ማቲዮስ በወቅቱ የክልሉ ወጣቶች ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ እየተወጡ ያሉትን ኃላፊነት አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በክልሉ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ መውሰዳቸውንና ሀገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ምዕራፍ ለመሸጋገር በምታደርገው ጥረት ሚናቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በክልሉ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች የምርጫ ሂደቱን ለመታዘብ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ማግኘታቸውን ጠቁመው ወጣቶች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ ምርጫው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በአቅም ግንባታ ስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እንደሚወጡም ገልጸዋል ።

በአቅም ግንባታ ስልጠናው በምርጫው የወጣቶች ሚና፣ የምርጫ ስነ-ምግባርና ህጎች ዙሪያ የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በአቅም ግንባታ ስልጠናው በክልሉ ከሚገኙ ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ ወጣቶች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ተሳትፈዋል።

ዘገባው የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው

የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት የይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛልየጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክን...
06/05/2026

የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት የይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛል

የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭከተማ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት "ወጣቱ ይመርጣል ሀገርን ያፀናል" በሚል መሪ ቃል የይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በይምረጡኝ ቅስቀሳው የክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የእግር ጉዞ በማድረግ ላይ ናቸው።

ወጣቶቹ በቅስቀሳው ወቅት "ብልጽግና መደመርና አንድነት ነው፣ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቱን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፓርቲ ነው፣ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ! ፣ ኢትዮጵያዊንን በአንድ ላይ ያስተሳሰረ ብልጽግና ፓርቲ ነው!፣ መጪውን ዘመን በላቀ ከፍታ ለመድረስ ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ የሚሉና ሌሎች መፈክሮች በድጋፍ ሰልፉ እየተደመጡ ነው ነው።

በመርሃ-ግብሩ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛና የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን ጨምሮ የክልሉ፣ የዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንሰል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምስረታ በዓል ፕሮግራም በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ...
03/05/2026

በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንሰል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምስረታ በዓል ፕሮግራም በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ህዝበ ሙስሊሙን በአንድ ጥላ ስር የማስተሳሰር፣ ወጣቶችን በትምህርት እና ስልጠና የማጎልበት፣ አንድነትን የማጠናከር እና የሀገር ኢኮኖሚን የማሳደግ አላማን ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣የደቡብ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ በቀለ ሎኮርማ፣የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ሀጂ ያሲን ከድር፣ የጋሞ ዞንና አርባምንጭ ከተማ የመንግሥት ፓርቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ፣ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

"አመራሩ ከምንግዜውም በላይ የውስጥ አንድነትቱን በማጠናከር፤ በአከባቢው የልማት ስራዎች ላይ በግምባር ቀደምትነት በመሳተፍ እና ለችግሮች ሀገር በቀል መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ሀገር የማሻገር ...
29/04/2026

"አመራሩ ከምንግዜውም በላይ የውስጥ አንድነትቱን በማጠናከር፤ በአከባቢው የልማት ስራዎች ላይ በግምባር ቀደምትነት በመሳተፍ እና ለችግሮች ሀገር በቀል መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ሀገር የማሻገር ተግባሩን ማጠናከር ይገባዋል!" - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የጋሞ ዞንና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የዞኑ ተወላጅ የክልል ከፍተኛ አመራሮች በልማትና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄዱ

በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ "አመራሩ ከምንግዜውም በላይ የውስጥ አንድነትቱን በማጠናከር፤ በአከባቢው የሰላምና ልማት ስራዎች ላይ በግምባር ቀደምትነት በመሳተፍ እና ለችግሮች ሀገር በቀል መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ሀገር የማሻገር ተግባሩን ማጠናከር ይገባዋል" ብለዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም አመራሩ በአከባቢው ሰላም፣ ልማት እና እድገት ግምባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ለሌላው ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው እንዲሁም ከፊት የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሀዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በሁሉ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አስታውሰዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ ከዓመቱ መግቢያ ጀምሮ ዘንድሮ በሚካሄደው በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ የተቀመጡ ሁለት መንታ ግቦች ለማሳካት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መቆየታቸው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የቅድመ ምርጫ ተግባራት እየተጠናቀቁ መሆናቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው በቀሪ ጊዜያት ምርጫው ነፃ፣ ሠላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና ሌሎች መንግስታዊ ሥራዎችንም በተመለከተ በጋራ ገምግሞ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ በበኩላቸው አመራሮቻችን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በሚገባ በመረዳት እና ተግባራትን በተቀመጡ መንታ ግቦች መሠረት ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት ሊሰራ ይገባዋል ያሉ ሲሆን፤ ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ ብሎም የተጣሉ የሂደትና የውጤት ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኝነታችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመቀመጡ መንታ ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ በአካባቢያቸው የሰላም፣ የልማት እና የእድገት ስራዎች ላይ ከፊት ሆኖ በመሳተፍ ለሌሎች ተምሳሌት እንደሚሆኑ ገልጸው፤ ከፊታችን የሚካሄደው ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሀዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ተግባብተዋል።

በመድረኩ የዞኑ ተወላጅ የሆኑ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የጋሞ ዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ተመራጮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋሞ ዞን በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገአርባምንጭ፦ ሚያዚያ  21/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)  የኢትዮጵያ ፌ...
29/04/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋሞ ዞን በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

አርባምንጭ፦ ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ርዕስቱ ይርዳው በወገኖች ላይ በተከሰተው አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት በመቀጠፉ በሰራዊቱ ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።

ሰራዊቱ አደጋው ከተከሰተበት ዕለት አንስቶ ተጎጅ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማጽናናት በመደገፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱን ጀነራሉ አስረድተዋል።

በህይወት በተረፉ ወገኖቻችንን ላይ መሰል አስከፊ አደጋ እንዳይከሰት እና በዘላቂነት ለማቋቋም የክልሉ እና የዞኑ መንግስት ህብረተቡን በማስተባበር እየሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ ፌደራል ፖሊስም የድርሻውን እንደሚወጣ አሳውቀዋል።

የፌደራል ፖሊስ ህይወቱን እየሰዋ የህዝብን ደህንነትና ሰላም እያስጠበቀ ይገኛል ያሉት ጀነራሉ ለሰው ልጅ ደራሽ መሆኑንና አጋርነቱን ለመግለጽ የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለተጎጅዎች መቋቋሚያ ማበርከቱን ገልፀዋል።

መንግስት በመላው የሀገራችን ክፍሎች አደጋን በመከላከል በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እየሰራ ያለውን መልካም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል።

የአከባቢው ማህበረሰብም ከሀዘን ወጥቶ የተፈጠረውን አስከፊ ችግር በጋራ በመተባበርና በጽናት ለመሻገር መጠንከር እንደሚገባው አቶ ርዕስቱ አሳስበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) የፌደራል ፖሊስ አደጋው በተከሰተበት አከባቢ በአካል በመገኘት ህብረተሰቡን በገንዘብና በጉልበት ሲደግፍ መቆየቱን ገልፀዋል።

አያይዘውም ዋና አስተዳዳሪው ለተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጎጅዎች በዞኑ ህዝብ ስም አመስግነው አጋርነታቸው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በኮሚንስት ታደሰ

የ1  ❗️በጋሞ የካምባ ዙሪያ  ወረዳ ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ አዴ አለሙና የወረዳው ስራ አስፈጻሚዎች በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የ1ሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ሶ...
26/04/2026

የ1 ❗️
በጋሞ የካምባ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ አዴ አለሙና የወረዳው ስራ አስፈጻሚዎች በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የ1ሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ሶርባ ቀበሌ ተገኝተው አጽናንተዋል ።

በወረዳው የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው በዚህ አደጋ የ1ሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አቶ አዴ አለሙን፣የካምባ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አባይነህ ደቻሳን ጨምሮ የወረዳ ስራ አስፈጻሚዎች ፣የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎቹ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

በተለይ የወቅቱን ዝናብ ሁኔታን ተከትሎ መሰል አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ስጋት ያሉባቸው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለወረዳችን ደጋ አከባቢ ህዝብ መልዕክት አስተላልፏል::

የጋሞ ዞን አስተዳደር በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ በሁለት ቀበሌያት የጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል በወላይታ ...
25/04/2026

የጋሞ ዞን አስተዳደር በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ በሁለት ቀበሌያት የጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል

በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 10:00 ጀምሮ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በዳሞታ ተራራ ግርጌ ባሉ በወሽ ጋሌ እና በኮናሳ ፑላሳ ቀበሌያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።

የጋሞ ዞን አስተዳደርም ለአደጋው ተጎጂዎች ቤተሰቦችና ለመላው የዞኑ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።

ተጎጂዎችን ለመደገፍ የወላይታ ዞን አስተዳደርና ህብረተሰቡ በሚያደርገው ጥረት የጋሞ ዞን አስተዳርም ከጎናቸው እንደሚሆን አሳውቋል።

የኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወጣቶች የሰላምና ደህንነት ድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አካሄደ በኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ...
23/04/2026

የኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወጣቶች የሰላምና ደህንነት ድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አካሄደ

በኢፌድሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች የብሔራዊ ዜግነት እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብይ ኃይለመለኮት የመድረኩ ዋና ዓላማ በብሄራዊ ደረጃ በወጣቶች ሰላምና ደህንነት ዙሪያ ለሚዘጋጀው የድርጊት መርሃ ግብር ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው ብለዋል።

ሐገራችን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የፈረመችው 22/50 የተሰኘ ስምምነት እንዲጠበቅ የሚያስችል ተግባራትን ለማከናወን የሚያግዝ መርሃ ግብር መሆኑን መሪ ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ወጣቶች የሰላምና ደህንነት ጉዳይን ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ የጠቀሱት አቶ አብይ ከመንግስትና ከማህበረሰብ ጋር በመተባበርና ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር የአከባቢያቸውን ብሎም የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በብሄራዊ ደረጃ ለሚዘጋጀው የሰላም ደህንነት ድርጊት መርሃ ግብር ግብዓት የማሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ እንደሚገኝም መሪ ስራ አስፈፃሚው አመላክተዋል።

የክልሉ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ኮሚሽን ኮሚሽነር ማርቆስ ማቴዎስ በበኩላቸው ወጣቶች አንድነታቸውን በማጠናከር ለሀገር ሰላምና ደህንነት መጠበቅ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ለሀገር ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ምሰሶዎች ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ በመድረኩ ከወጣቶች የተሰበሰቡ ግብዓቶች በሀገር ደረጃ ለሚቀረፁ የሰላምና ደህንነት ፖሊስና ስትራቴጂዎች በግብዓትነት እንደሚያገለግሉም አብራርተዋል።

በተለይ ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ምክንያቶችን ከመነሻቸው በመለየት እስከ ግጭት አፈታት ድረስ ያለውን ሂደት በተመለከተ ግብዓት የመሰብሰብ ስራ በመድረኩ መከናወኑንም ኮሚሽነር ማርቆስ ጠቅሰዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው ስልጠናው ወጣቶች በሀገር ሰላምና ደህነት ዙሪያ ያላቸውን አስተዋፅኦ በሚገባ እንዲገነዘቡ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስልጠናው የሀገር ሰላምና ደህንነን ለማስጠበቅ የሚረዱ 5 ምሰሶዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ያደረገ መሆኑንም ተሳታፊ ወጣቶች አመላክተዋል።

በመርሃ ግብሩ ከጋሞ ዞን እና አርባምንጭ ከተማ ከሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች የተውጣጡ ከ60 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

በሩፋኤል ግርማይ

የሀገሪቱ የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በወጣቱ ትውልድ ነው - አቶ ተፈሪ አባተ አርባምንጭ: ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ )በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 7ኛው ሀገራዊ ም...
23/04/2026

የሀገሪቱ የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በወጣቱ ትውልድ ነው - አቶ ተፈሪ አባተ

አርባምንጭ: ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ )

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊና ስኬታማ እንዲሆን ወጣቶች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

በክልሉ ''የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ'' በሚል መሪ ሃሳብ ክልል አቀፍ የወጣቶች የንቅናቄ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት ሲሉ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በወጣቱ ትውልድ ስለመሆኑ የገለፁት አቶ ተፈሪ በሀገር ጉዳይ የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል።

ጀግኖች አባቶች ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር አስጠብቆ ያቆዩትን ሀገር ይህ ትውልድ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጠቁመው ፥የሀገር ቀጣይነት የሚወሰነው በዜጎች በሚመሰረተው መንግስት ስለመሆኑ ጠቁመዋል ።

ለዚህም ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን እንዲወጣ ኃላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ እንደተናገሩት ፣ወጣቱ የእምቅ አቅም ችሎታና የፈጠራ ባለቤት ስለመሆኑ አስረድተዋል ።

በክልሉ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ካሰች የወጣቶች የፖለቲካና ውሳኔ ሰጪነትን ለማሳደግ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።

ወጣቶች በፖለቲካ ፣በዴሞክራሲና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በግምት ውስጥ በማስገባት ለተጠቃሚነታቸው እየተሰራ ስለመሆኑ ወ/ሮ ካሰች አስገንዝበዋል ።

የክልሉ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ኮሚሽን ኮሚሽነር ማርቆስ ማቴዎስ በበኩላቸው ፣ወጣቶች የውስጥ አንድነትን በማጎልበት ለሀገር ሰላምና አንድነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

7ተኛ ሀገራዊ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ፣ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ ማርቆስ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የወጣቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለመሆኑ አስረድተዋል ።

የክልሉ ወጣቶች ከመንግስት ጎን በመሆን ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኮሚሽነር ማርቆስ ጥሪ አቅርበዋል ።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የክልሉ ወጣቶችና ሌሎች ለባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

Address

Arba Mintch
485882

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share