ጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ/Gamo Zone Justice Department

ጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ/Gamo Zone Justice Department To all Werda/Ketma Justice Office & Stakeholders to forward info.wnd receives any constractive idea

08/12/2023

ዜ ና ፍ ት ህ
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱ 4 ግለሰቦች በሕግ ተቀጡ፡፡
👉1ኛ ተከሳሽ አቶ መለሰ መስቀለ የተባለው በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የምዕራብ አባያ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የደንበኞች አገልግሎት ኦፊሰር ሆኖ በሚሠራበት ወቅት ያንቀሳቀሰው ሂሳብ በኦዲት ሲመረመር ከ30 ደንበኞች ቁጠባ ሂሳብ ላይ ደንበኞቹ ሳያውቁና ሳይፈቅዱ ብር 211,300.84 (ሁለት መቶ አሥራ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማኒያ አራት ሳንትም) ተቀናሽ በማድረግ ወንድሙ ወደሆነው 2ኛ ተከሳሽ አቶ መድን መስቀለ ሂሳብ ቁጥር በማዛወር እንዲሁም ከ2 ደንበኞች ሂሳብ ቁጥር ብር 34,000 (ሳላሳ አራት ሺህ ብር) ወደ ራሱ ሂሳብ ቁጥር ካዛወረ በኃላ መልሶ ወደ 2ኛ ተከሳሽ አካውንት ቁጥር በማዛወር፣2ኛ ተከሳሽም ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር በራሱ አካውንት ያልቆጠበውንና የራሱ ያልሆነውን ገንዘብ በድምሩ ብር 245,300.84 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማኒያ አራት ሣንትም) ወጪ በማድረግ የማይገባ ጥቅም ማግኘታቸው በኦዲት የተረጋገጠ በመሆኑ፣
👉እንዲሁም 1ኛ ተከሳሽ ተቋሙ የአሠራር ለውጥ በማድረግ የደንበኞችን ሂሳብ ወደ ኮር ባንክንግ (ኦን ላይን ሲስተም) ማስገባቱን አጋጣሚ በመጠቀም ደንበኞች ገንዘብ ወጪ ለማድረግ ሲመጡ የወጪ ማዘዣ ሰነድ ራሱ በማዘጋጀት ደንበኞች ከሚፈልጉት ገንዘብ መጠን በላይ እየመዘገበ ወይም እየጻፈ በማስፈረም እና አስመስሎ በመፈረም ቁጥራቸው 166 በሆኑ ደንበኞች ሂሳብ ላይ በትርፍነት የገባ ብር 741,638 (ሰባት መቶ አርባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሳላሳ ስምንት ብር) ወጪ በማድረግ በድምሩ 1ኛ ተከሳሽ ብር 986,938.84 (ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሳላሣ ስምንት ብር ከሰማኒያ አራት ሳንትም) ለግል ጥቅሙ በማዋል በድርጅቱ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ፣
👉2ኛ ተከሳሽም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ብር 245,300.84 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማኒያ አራት ሣንትም) ወጪ በማድረግ የተጠቀሙ በመሆናቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በክስ አንድ የኢፌዲሪ የወ/ህ/ቁ 32 (1) (ሀ) ፣ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 በአንቀጽ 4 (1) እና 31 (2) በመተላለፍ በፈጸሙት ከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል፣
👉 3ኛ ተከሳሽ አቶ አድማሱ ጃጃርሶ የተባለው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የውስጥ ኦዲተር ሆኖ በሚሠራበት የገንዘብ ዝውውር ከደንበኞች ሂሳብ ቁጥር ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ቁጥር የገንዘብ ዝውውር የሚፈጸመው የውስጥ ኦዲተር ሲያረጋግጥ ብቻ ሆኖ ሳለ 1ኛ ተከሳሽ ብር 245,300.84 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማኒያ አራት ሣንትም) ከደንበኞች አካውንት ደንበኞች ሳይፈቅዱና ሳያውቁ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ራሱ እና ወደ 2ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ቁጥር ዝውውር ሲያደርግ ዝውውሩን በማረጋገጥና በቸልተኝነት በመፍቀድ፤
👉4ኛ ተከሳሽ አቶ ደበላ ደባልቄ የተባለውም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት በኃላፊነቱ ከተቋሙ ደንበኞች ሂሳብ ቁጥር ወደ ሌላ ደንበኞች ሂሳብ ቁጥር የገንዘብ ዝውውር የሚፈጸመው ሥራ አስኪያጁ ሲያፀድቅ ብቻ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ብር 245,300.84 (ሁለት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማኒያ አራት ሣንትም) ከደንበኞች አካውንት ደንበኞች ሳይፈቅዱና ሳያውቁ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ራሱ እና ወደ 2ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ቁጥር ዝውውር ሲያደርግ ዝውውሩን በማፅደቅ በቸልተኝነት በመፍቀዱ ደንበኞች ገንዘብ ባልተገባ መንገድ እንዲመዘበር በማድረጋቸው 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በክስ 2 እና በክስ 3 የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 በአንቀጽ 13 (7) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸሙት የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሥራን በማያመች አኳኃን በመምራት የሙስና ወንጀል በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ በኩል ክስ ቀርቦባቸው፣
👉 ግራ ቀኙን ሲያከራክር የቆየው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ያቀረበው ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ ተከሳሾችን በተከሰሱበት የሕግ ድንጋጌ ሥር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ፍርድ በመስጠት፣
👉 ዛሬ 26/03/2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽን በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ15,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንድቀጣ፣
👉 2ኛ ተከሳሽን በ9 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፣
👉 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ቀላል እስራትና በ5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ቅጣት ጥሎባቸዋል፡፡
አንድ የመንግሥት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ የመንግስትን ወይም የሕዝባዊ ድርጅትን ሥራ በሚያከናውንበት ጊዜ ሕግንና የተዘረጉ የአሠራር ሥርዓትን ጠብቆ ተግባራትን መፈጸም የሚጠበቅ ሲሆን ተከሳሾች ይህንን የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ በመሆናቸው እነሱን የሚያርም መሠሎችን የሚያስተምር ቅጣት አግኝተዋል፡፡
🙏ስለሆነም ይህ ቅጣት ሌሎች ከእንደዚህ ዓይነት መሰል የወንጀል ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠቡ የሚያደርግና ሁሉም ዜጋ ህግን በማክበርና በማስከበር ረገድ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

14/11/2023

ዜና ፍትህ

በጽንስ ማስወረድ ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
ግዛቸው ነጋሽ የተባለው ተከሣሽ በአ/ምንጭ ከተማ በመሃል ከተማ ቀበሌ በሚገኘው ኤልሻዳይ የመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒክ ባለቤት እንዲሁም የህክምና ባለሙያ ሲሆን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ህግ 535(1) የተመለከተውን በመተላለፍ በመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒክ እንዲሰራ ከተፈቀደለት የሕክምና አገልግሎቶች ውጪ በሆነ መንገድ እንዲሁም ሥልጣን ካለው አካል አግባብነት ባላቸው ደንቦች መሠረት በግልጽ የጽንስ ማስወረድ ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሳይሰጠው ሁለት ነብሰጡር ሴቶችን ጽንስ የማስወረድ ተግባር ያከናወነ በመሆኑ በህክምናና በጤና አጠባበቅ ሙያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ መስራት ወንጀል፣ በተጨማሪ ክስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ህግ 548(3) በመተላለፍ የግል ተበዳይ ወ/ሮ ጥሩነሽ ለማ የተባለችው የጸነሰችውን ከ13/አሥራ ሶስት እስከ 14/አስራ አራት ሳምንት የሆነውን ጽንስ በወንጀል ህጉ ጽንስን ለማቋረጥ ከተፈቀደላቸው ሁኔታዎች ውጪ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ 14000/አስራ አራት ሺህ/ ብር እንድትከፍል በማድረግ ክፍያውን በመቀበል የጽንስ ማስወረጃ መድሐኒት በመስጠት ጽንሱ እንዲወጣ በማድረጉ በፈፀመው በሌላ ሰው የሚፈፀም ጽንስ የማስወረድ ድርጊት ወንጀል ተከሷል፡፡ እንዲሁም የኢ.ፌዲ.ሪ.ወንጀል ህግ አንቀጽ 552(3) እና የፌደራል ጤና ጠበቃ ሚንስቴር ደህንነቱን የጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀ አፈፃፀም መመሪያ አንቀጽ 5 (3) (4) አንቀጽ 6(5) ፓራግራፍ አንድ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በመተላለፍ የተለያዩ ሴቶች ላይ የወንጀል ህጉ እና የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ያወጣዉን የአፈፃፀም መመሪያ ባልተከተለ መንገድ በመመሪያው ሰንጠረዥ 2 ገፅ 37 ላይ የግል የመጀመሪያ ደረጃ ክሎኒኮች እስከ 9(ዘጠኝ) ሳምንት ላሉ እርግዝናዎች ብቻ የመድኃኒት ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መሆኑ ተደንግጎ ባለበት ከ13 እስከ 14 ሳምንት በላይ የሆነ ጽንስ የማስወረድ አገልግሎት የሰጠበመሆኑ በፈፀመዉ ፅንስ የሚቋረጥበት ሥነ-ሥርዓት እና የጤና ጠበቃ ሚንስቴር ያወጣዉን አፈፃፀም መመሪያ መጣስ ወንጀል ተከሶ መዝገቡ ሲመረምር የቆየው የአ/ምንጭ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የሴቶችን ህፃንት ልዮ ምርመራና ክስ ጉዳዮች ክትትል ሥራ ሂደት በተጠርጣሪው ላይ ተደራራቢ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ክስ መስርቶ ሲከታተል ከቆየ በኋላ የአ/ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀን 09/10/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሣሹ ላይ ከቀረበበት ወንጀሎች መካከል በወንጀል ህግ አንቀጽ 535(1) ሥር በነፃ በማሰናበት በሌሎቹ ክሶች የጥፋተኝነት ውሳኔ በማሳለፍ በአንድ ዓመት ቀላል እስራትና በብር 1500 መቀጮ እንዲቀጣ እንዲሁም ከሞያዊ አገልግሎቱ ለአንድ ወር አንዲታገድ ወስኖበታል፡፡
ዐ/ህግ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ በዞኑ የሴቶችና ህፃናት ልዮ ምርመራና ክስ ጉዳዮች ክትትል ዋና ሥራ ሂደት በይግባኙ ላይ ክርክር ሲደረግ ቆይቶ በቀን 26/02/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀን 09/10/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት (ዕገዳውን ሳይጨምር) በክስ አራት እና አምስት ከጥፋተኝትም ሆነ ከቅጣት ያሳለፈው የ1 (አንድ) ዓመት ቀላል እስራት እና 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) መቀጮ ፀንቷል፡፡ መልስ ሰጪ የኢፌዲሪ ወ/ሕ/አንቀፅ 535(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከተፈቀደለት የህክምና አገልግሎት ውጭ በሆነ መንገድ እና ሥልጣን ካለው አካል አግባብነት ባላቸው ደንቦች መሠረት በግልፅ ፅንስ ማስወረድ ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሳይሰጠው ሁለት የግል ተበዳዮችን ፅንስ ያስወረደ ስለመሆኑ ተመስክሮበት በአግባቡ ሳይከላከል ከክሱ በነፃ በማሰናበት ያሳለፈው ውሳኔ ስህተት ሆኖ በመገኘቱ ተሽሮ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በመሆኑም መልስ ሰጪ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በ2 (ሁለት) ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ በስር ፍርድ ቤት ከተወሰነው የገንዘብ መቀጮ በተጨማሪ በ1‚000 (አንድ ሺህ) ብር መቀጮ እንዲቀጣ እንዲህም ለአንድ ዓመት ከሙያ ሥራው እንዲታገድ ተወስኗል፡፡ በመሆኑም የግል ሆነ የመንግስት ጤና ተቋማት ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ እንዲሁም ህብረተሰቡ ወንጀሎቹ መፈፀማቸውን ሲያውቅ የተለመደውን ጥቆማ ለፍትህ ተቋማት እንዲሰጥ እናሳውቃለን፡፡

የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ከባለድርሻ/ህዝብ ክንፍ ጋር ተወያየ፣የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለ...
01/11/2023

የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ከባለድርሻ/ህዝብ ክንፍ ጋር ተወያየ፣
የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ/ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር ዛሬ 21/2/2016 ዓ/ም እየተወያየ ይገኛል፣

ይበልጥ በጋራ በመስራት ውጤታማነትን እናሳድጋለን!!
01/08/2023

ይበልጥ በጋራ በመስራት ውጤታማነትን እናሳድጋለን!!

ባሳለፍነው 2015  በጀት ዓመት በቀድሞው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲሱ ኦሞ ባንክ በኩል  በስራ እድል ፈጠራና በመደበኛ ብድር ያሰራጫቸውን በወቅቱ መክፈል ባልቻሉ ማህበራትና ግለሰቦች ላይ ...
01/08/2023

ባሳለፍነው 2015 በጀት ዓመት በቀድሞው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲሱ ኦሞ ባንክ በኩል በስራ እድል ፈጠራና በመደበኛ ብድር ያሰራጫቸውን በወቅቱ መክፈል ባልቻሉ ማህበራትና ግለሰቦች ላይ ለዐቃቤያን በቀረቡ አቤቱታዎች በድርድርና በክስ 27,000,000.00 ብር/ሃያ ሰባት ሚሊዮን ብር/ ማስመለስ ችለናል በዚህም ኦሞ ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በኩል ለመምሪያችን የዋንጫና ሰርተፍኬት ተበርክቶልናል ።
ለዚህ ተግባር ስኬታማነትና ለመጣው ውጤት እንደየ ድርሻችሁ የተጋችሁ የዞን ፍትህ መምሪያ አመራርና ባለሙያዎች የወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ታላቅ ምስጋና እያቀረብን በያዝነው በጀት አመትም የህዝብና የመንግስት ጥቅም ባለባቸው የፍታብሔር ጉዳዮች ላይ ከነበረው በተሻለ በበለጠ ትኩረት ርብርብ እንድታደርጉ መልእክታችን ነው ።

28/07/2023

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ፣

ተከሳሾች፣- 1ኛ. ኢዮብ እማሞ የወረዳው ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ 2ኛ.መንግስቱ ማኬ የመጋዘን ኃላፊ 3ኛ. መውጫ ዲሊያስ የመጋዘን ኃላፊ በመሆንኑ በጋሞ ዞን ደራማሎ ወረዳ ለወረዳው አርሶ አደር እንዲደርስ የተላከውን የአፈር ማዳበሪያ እንደተሰራጨ በማስመሰል በፈጸሙት የመንግስትን ሥራ በማያመች ሁኔታ በመምራት ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸው የዞኑ ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13(1) እና 31(2) ጠቅሶ ባቀረቀው የሙስና ወንጀል ክስ ለጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 45267 ያቀረበ ሲሆን መዝገቡን ሲመረምር የቆየው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ተከሳሾችን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል ያለውን በተከሳሾች ላይ 1ኛ.ኢዮብ እማምን በ1 ዓመት ከ5 ወር አስራት እና ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/፣
2ኛ.መንግስቱ ማኬን በ4ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 2000.00/ሁለት ሺህ ብር/፤
3ኛ.ማውጫ ዲሊያንስን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 2000.00/ሁለት ሺህ ብር/፤ ቅጣት ተቀጡ።

ከሙስናና ብልሹ አሰራር እራሳችንን እንጠብቅ!!

የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ!!

28/07/2023

ዜና ፍትህ፣
በሙስና ወንጀል የተከሰሰው በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፣

ተከሰሽ ጴጥሮስ ጳውሎስ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ውስጥ የአይላ ጤና ጣቢያ የዕለት ገንዘብን ሰብሳቢ ሆኖ ሲሰራ ብር 130,000/አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር/ በማጉደል እና ለገንዘብ መሰብሰቢያነት የወሰዳቸውን ደረሰኞች በማጥፋት በመንግስት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ የዞኑ ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31(2) እና 24 (2) ጠቅሶ በከባድ እምነት ማጉደል እና የመንግስትን ሰነድ መጥፋት ወንጀል ክስ ለጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 46138 ያቀረበ ሲሆን መዝገቡን ሲመረምር የቆየው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ተከሳሽን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል ያለውን በተከሳሽ ጴጥሮስ ጳውሎስ ላይ የ10/አስር ዓመት/ጽኑ እስራትና በብር 4000.00/አራት ሺህ ብር/ ቅጣት ተቆርጧል።

ጉባዔ መራዘሙን ስለመግለጽ ይሆናል፣
10/10/2022

ጉባዔ መራዘሙን ስለመግለጽ ይሆናል፣

👉 የመምሪያችን ኃላፊ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት             የተወደዳችሁ በዞናችን  ስር የምትገኙ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ፣ የመምሪያች...
12/09/2022

👉 የመምሪያችን ኃላፊ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት

የተወደዳችሁ በዞናችን ስር የምትገኙ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ፣ የመምሪያችን ስራ ሂደት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ/ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ አዲሱ አመት የሰላም የጤና የፍቅር የአንድነት የመደጋገፍ የመደማመጥ እንዲሁም የብልጽግና እንዲሆንልን እየተመኘሁ ። በአሉን ስናከብር አሸባሪው ህውሀት በመንግስት የቀረበውን የሰላም ጥሪ ወደጎን በመተው ሀገራችን ላይ ለ ሶስተኛ ጊዜ የከፈተብንን ጦርነት በግንባር ተሰልፈው ተጋድሎ እየፈፀሙ የሚገኙ የጸጥታ ሀይሎችን በማሰብና የሚጠበቅብንን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ እንዲሆን ጥርዬን አስተላልፋለሁ። ሰላም ለኢትዮጵያ ፈጣሪ ሀገራችንንና ህዝቦቿን ይባርክ በድጋሚ መልካም አዲስ አመት::

👉 አቶ ሽመልስ ጮራ የጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ

13/08/2022

Address

SNNPRS
Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ/Gamo Zone Justice Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share