Department of Agriculture Gamo zone

Department of Agriculture Gamo zone ይህ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው። ገጹን follow, like, comment and share በማድረግ ትኩስና ወቅታዊ መረጃ ይከታተሉ።

04/06/2026
በጋሞ ዞን በካምባ ዙሪያ ወረዳ በዶ/ሳሌ ቀበሌ የእንስሳትን ጤና እና ምርታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የክትባት ዘመቻ ተካሂዷል።በዚህም ክትባት ከብቶችን ከከባድ ተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ (...
03/06/2026

በጋሞ ዞን በካምባ ዙሪያ ወረዳ በዶ/ሳሌ ቀበሌ የእንስሳትን ጤና እና ምርታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የክትባት ዘመቻ ተካሂዷል።

በዚህም ክትባት ከብቶችን ከከባድ ተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ (L*D) እና የ(Bovine Pasteurellosis) ክትባቶች መሰጠታቸውን የሚያሳይ ምስል!

#ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)

31/05/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
//////////////////
በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጁን የመጀመሪያው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡

 #ጋሞ ዞን በዳራማሎ ወረዳ  በበልግ ወቅት  በትላሌ ቀበሌ በአርሶ አደር ማስልጠኛ ማዕከል "NURU ETHIOPIA" በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ እየለማ የሚገኝ ሰብል በምስል
29/05/2026

#ጋሞ ዞን በዳራማሎ ወረዳ በበልግ ወቅት በትላሌ ቀበሌ በአርሶ አደር ማስልጠኛ ማዕከል "NURU ETHIOPIA" በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ እየለማ የሚገኝ ሰብል በምስል

29/05/2026
‎ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት  በማምረት ለሀገር ውስጥና  ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል :-ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ‎ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ይህን...
28/05/2026

‎ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል :-ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ

ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ይህንን የተናገሩት የክልሉ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP) ሥራ ማስጀመሪያ መድረክ በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው።



ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ‎በምክትል ርዕሰ -መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ አሳሰቡ።

‎አቮካዶ ለዘመናት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ሲለማ የነበረ ተክል ቢሆንም ትኩረት ባለማግኘቱና በምርምር የተሻሻሉ ምርታማና የተሻለ የዘይት ይዘት ያላቸው ዝርያዎችን ለይተን ማልማት ባለመቻላችን ያለንን ዕምቅ የመልማት ሳንጠቀም ኖረናልም ብለዋል።

‎ዶ/ር መሪሁን አክለውም በቀጣይ ጊዜያት እንደ ሀገር በጠቅላይ ሚኒስትራችን ድጋፍ ይህ ፕሮግራም (NADP) የሚሠራ ሲሆን በክልላችን ለ15 ዓመታት በአቮካዶ ልማት ላይ የሚተገበር በመሆኑ ከፍተኛ የማምረት አቅም ካላቸው አካባቢዎች በተጨማሪ በሁሉም ዞኖች ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

‎አቮካዶ ላይ መሥራት ደቡብ ኢትዮጵያን ማሻገር ነው ያሉት ኃላፊው በስፋትና በጥራት በማምረት ፣ገበያን በማረጋጋት በከተማ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ገጠሩን በመናፈቅ ንፁህ አየር የምናገኝበት የፍራፍሬ ገነት በመፍጠር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎በቀጣይም የተሻለ ይዘት ያለው አቮካዶ በመምረጥ፣ አዳቃይ ባለሙያዎችን በማሰልጠን፣ በእንዳስትሪ ልማቱ የተሠማሩ የግል ባለሀብቶችን በማሳተፍ፣ አመራሩና ባለሙያው በመቀናጀት ሞዴል ችግኝ ጣቢያዎችን ለማፍራት ቢሮው በማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ዶ/ር መሪሁን አስታውቀዋል።

‎በዕለቱም የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ የዛሬው መድረክ ዋነኛ ዓላማ በክልላችን አቮካዶን በስፋትና በብቃት በማምረት ከምግብነትና ከእንዳስትሪ ግብአትነት ባሻገር የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ በሚያስችሉ መርሆች ላይ ለመምከር እንደሆነ ገልፀዋል።

‎ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም እንደ ሀገር ከ38 ቢሊየን ብር በላይ ከመደበኛ በጀት ተመድቦ ለ15 ዓመታት በመቆየት የሚሠራ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቢሮው ችግኝ በማፍላትና በማቅረብ ሲደግፉ የነበሩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በመቀናጀት የተሻለ ሥራ የሚሠራ መሆኑን ተናገግረዋል።

‎የክልሉ ብሔራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP)ማናጀር ወ/ሮ አበበች ደሳለኝ የፕሮግራሙን ዓላማ ፣በቀጣይ በፕሮግራሙ ሊሠሩ የታቀዱ ሥራዎችንና በፕሮግራሙ የሚደገፉ ወረዳዎችን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሰነድ አቅርበዋል።

‎የአቮካዶ ተክል ከሌሎች ፍራፍሬዎች ልዩ የሚያደርገው በየትኛውም እድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ምግብ ከመሆኑ ባሻገር ለምግብ ዘይትና ለስነ ውበት ያለው አስተዋፅኦ የጎላና እጅግ ተፈላጊ የሆነ የፍራፍሬ ዓይነት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራበታል ብለዋል።

‎ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ ከፍተኛ አቮካዶ የማምረት አቅም ባላቸው አካባቢዎች (በወላይታ፣ጋሞ፣ጌዴኦ፣ ጎፉ፣አሪ ፣ደ/ኦሞ፣ ባስኬቶ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 12 ዞኖች ላይ እንደሚሠራ ተገልጿል።

‎በዕለቱም ከቤቱ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሡ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

‎በመድረኩም የክልሉ ግብርና ቢሮ ሴክተር ማናጅመንት አባላት፣ የፕሮግራሞና ፕሮጀክት አስተባባሪዎች የቢሮው እርሻ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ፕሮግራሙ ከሚሠራባቸው ዞኖች(ከ7ቱ ዞኖች) ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ከ12ቱ የፕሮግራሙ ወረዳ አስተዳደሪዎችና የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ እና በክልሉ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP) ትብብር በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ አራት ቀበሌያት ላይ ለአርሶ አደሮ...
25/05/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ እና በክልሉ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP) ትብብር በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ አራት ቀበሌያት ላይ ለአርሶ አደሮች በአቮካዶ አመራረት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

#ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

በወረዳዉ ለመጀመሪያ ዙር በፕሮግራሙ ለታቀፉ 200 አልሚ አርሶ አደሮች ሰለአቮካዶ አመራረት እና ኩታ ገጠም እርሻ በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር የተደገፈ ሥልጠና በወረዳና ቀበሌ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

በጋሞ ዞን የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የፕሮጀክቱ ፎካል አቶ መኮንንን ተስፋዬ ስልጠናዉ ለአከባቢው አርሶ አደር በጣም ጠቃሚና ለወደፊት የአቮካዶ ምርትን ለተለያዩ ለዓለም ገበያ በበቂ መጠን እንድናቀርብ እድል የሚሰጥ ነዉ ብለዋል።

በፕሮግራሙ የታቀፉ አርሶ አደሮች ስልጠናዉን በትክክል በመከታተልና አስልጣኞች የምሰጡትን ስልጠና ትኩረት በመስጠት በማዳመጥ መተግበር ከቻሉ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርሱ አስረድተዋል።

በወረዳዉ በክላስተር ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለዉ አአቮካዶ በማምረት ለሀገር ዉስጥና ለዉጪ ገበያ በዛላቂነት በማቅረብ ጠንካራና ተወዳዳሪ የአቮካዶ እንዱስትሪ ለመመስረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአቮካዶ እሴት ዙሪያ ለአርሶ አደሮች የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

!!

25/05/2026
በበልግ ወቅት በክላስተር የለማው የበቆሎ ሰብል ከፍተኛ ምርታማነት እንደሚያስገኝ ተጠቆመ​ #ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)​አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ...
25/05/2026

በበልግ ወቅት በክላስተር የለማው የበቆሎ ሰብል ከፍተኛ ምርታማነት እንደሚያስገኝ ተጠቆመ

​ #ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)

​አርሶ አደሮችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ የተቀናጁ ስራዎች፣ በ2018 የበልግ ወቅት በበቆሎ ክላስተር እየለማ ያለው ሰብል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) እና የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በምዕራብ አባያ ወረዳ ፉራ ቀበሌ በበልግ ወቅት በክላስተር የለማውን የበቆሎ ሰብል በጎበኙበት ወቅት ነው።

​የዞኑ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በስፍራው ሲደርስ የምዕራብ አባያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ወልዴን ጨምሮ የወረዳው የስራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

​የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በበልግ ወቅቱ በበቆሎ ክላስተር አማካኝነት ከ37 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የበቆሎ ሰብል እየተመረተ ይገኛል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ ዘመናዊ የመካናይዜሽን የአተራረስ ዘዴዎችን መጠቀም፣ የግብርና ግብዓቶችን በወቅቱና በጥራት ማቅረብ፣ ለአርሶ አደሮች የተሰጡ የክህሎት ስልጠናዎች እንዲሁም የእርሻ ካላንደርን በአግባቡ መከተል የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በወቅቱ በክላስተር ለማልማት የታቀደው ስራ ሙሉ በሙሉ መሳካቱን የገለጹት ከግብርና መምሪያው አቶ ለማ ናቸው።

እንደ አቶ ለማ ማብራሪያ፤ በበልግ ምርት ዘመን 2,030 ሄክታር መሬት በክላስተር ለመደገፍ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት እቅዱ 100 በመቶ ተሳክቶ መሬቱ በበቆሎ ሰብል ለምቶ ይገኛል።

​የምዕራብ አባያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ወልዴ በበኩላቸው አርሶ አደሩን ከተጠቃሚነት አንጻር በማሰብ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ጥረትና እየታየ ያለው ተስፋ ሰጭ ውጤት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

Address

Arbaminch
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Department of Agriculture Gamo zone posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share