Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office

Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office Communication ,follow us!

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል 'የመርካቶ ገበያ ማዕከል' ምርጫ ጣቢያ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል 'የመርካቶ ገበያ ማዕከል' ምርጫ ጣቢያ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል 'የጎርማ ቀበሌ ኖክ መደያ' ምርጫ ጣቢያ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።‎
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል 'የጎርማ ቀበሌ ኖክ መደያ' ምርጫ ጣቢያ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫው ያለምንም ፀጥታ ችግር ተጠናቋል። የድምፅ ቆጠራም እየተጠቃለለ ይገኛል - ረ/ኢንስፔክተር አለማዬሁ ዱርቁላ‎‎የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር...
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫው ያለምንም ፀጥታ ችግር ተጠናቋል። የድምፅ ቆጠራም እየተጠቃለለ ይገኛል - ረ/ኢንስፔክተር አለማዬሁ ዱርቁላ

‎የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር አለማዬሁ ዱርቁላ በምርጫ ክልሉ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠቃለሉን ጠቅሰው ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ችግርም ሆነ ወንጀል የለም ብለዋል።

‎ከዞን ለድጋፍ ከመጡ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የገለፁት ረዳት ኢንፔክተር አለማዬሁ የምርጫ ተግባራት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ወደ ምርጫ ቦርድ መድረስ የሚገባቸው ሁሉም ጉዳዮች እስኪደርሱ ፓሊስ በተጠንቀቅ እየሰራና ዝግጁም እንደሆነ ተናግረዋል።

በቁጫ ምርጫ ክልል የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ።በቁጫ ምርጫ ክልል በሠላምበር ምርጫ ማዕከል ካምብ ቀበሌ 'ጊዶ ዎባ' ምርጫ ጣቢያና 'ጥንጋሌ አላ...
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ።

በቁጫ ምርጫ ክልል በሠላምበር ምርጫ ማዕከል ካምብ ቀበሌ 'ጊዶ ዎባ' ምርጫ ጣቢያና 'ጥንጋሌ አላዴ' ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርገዋል።

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል ዳንባየዬ ቀበሌ ግሪን ኤሪያ 2 ን/ምርጫ ጣቢያም ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል ሠላምበር ማዕከል ዳንባየዬ ቀበሌ ግሪን ኤሪያ 2 ን/ምርጫ ጣቢያም ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በቁጫ ምርጫ ክልል ዳንባየ መስጊድ ምርጫ ጣቢያም ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
02/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል ዳንባየ መስጊድ ምርጫ ጣቢያም ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በቁጫ የምርጫ ክልል ሰላምበር ከተማ ከመቸውም ጊዜ የተለየ ሰላማዊ ምርጫ አካሂዳለች - አቶ ዳርዛ ደምሴበጋሞ ዞን ሰላምበር ከተማ አስተዳደር ባሉ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሰላማዊ መንገድ ሲካ...
01/06/2026

በቁጫ የምርጫ ክልል ሰላምበር ከተማ ከመቸውም ጊዜ የተለየ ሰላማዊ ምርጫ አካሂዳለች - አቶ ዳርዛ ደምሴ

በጋሞ ዞን ሰላምበር ከተማ አስተዳደር ባሉ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሰላማዊ መንገድ ሲካሄድ መዋሉን የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳርዛ ደምሴ ገልፀዋል፡፡

መራጩ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከሌሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየሰጠ መዋሉን የገለፁት ከንቲባው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል ያለውን ፓርቲ ያለምንም ተፅዕኖ እየመረጠ ውሏል ብለዋል፡፡

እኔም ይበጀኛል ያልኩትን ፓርቲ መርጫለሁ ያሉት ከንቲባው ህዝብ የሰጠው ድምፅ ምንም ይሁን ምን ለመቀበል እኔም ፓርቲዬም ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ተዟዟሪ ታዛቢ ወ/ሮ መነን ዘውዱ ተዘዋውረው ባዩዋቸው በቁጫ የምርጫ ክልል እና በዛላ - ዳራማሎ የምርጫ ክልሎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ ያለማንም ጣልቃ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ተዟዟሪ ታዛቢ ወ/ሮ መነን ዘውዱ ተዘዋውረው ባዩዋቸው በቁጫ የምርጫ ክልል እና በዛላ - ዳራማሎ የምርጫ ክልሎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ ያለማንም ጣልቃ ገብነትና ተፅዕኖ ድምፁን በሰላማዊ ሁኔታ ሲሰጥ መዋሉን እና መራጩ ህዝብም መርጦ እስከሚጨርስ ምርጫ ቦርድ ባወረደው መመሪያ መሠረት ምርጫው ለሰዓታት መራዘሙን አስታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ መነን ዘውዴ እንደገለፁት ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ የሁሉም ፓርቲዎች ታዛቢዎች ተገኝተው ቃለጉባኤ ከያዙና ከተፋራረሙ ኋላ ምርጫው መጀመሩን መታዘባቸውን ገልፀው የሲቪክ ማህበራት ታዛቢዎችን ጨምሮ ሌሎችም ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ምርጫውን ሲታዘቡ ነበር፡፡ ምርጫውም ነፃና ሰላማዊም ሆኖ ውሎ አሁንም ሰላማዊ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በምርጫ አካባቢዎችም ህዝቡን ሊረብሽና ሊያደናግር የሚችል ተፅዕኖ ፈጣሪ ነገር እስካሁን እንደሌለም አክለዋል፡፡

በቁጫ ምርጫ ክልል በርካታ ህዝብ በተመዘገበባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው ከምሽቱ  እስከ 6:00  ድረስ መራዘሙ ተገለፀበጋሞ ዞን ቁጫ ምርጫ ክልል በዛሬው ዕለት ሲካሔድ የቆየው የ7ኛው ሀገራ...
01/06/2026

በቁጫ ምርጫ ክልል በርካታ ህዝብ በተመዘገበባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው ከምሽቱ እስከ 6:00 ድረስ መራዘሙ ተገለፀ

በጋሞ ዞን ቁጫ ምርጫ ክልል በዛሬው ዕለት ሲካሔድ የቆየው የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ማጠቃለያ ሰዓት ላይ ቢደርስም የመራጭ ብዛት ባለባቸው ጣቢያዎች ምርጫው ከምሽቱ እስከ 6:00 ድረስ መራዘሙን የቁጫ ምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ጋኔቦ ገልፀዋል።

የቁጫ ምርጫ ክልል ሀላፊ አቶ ኤልያስ ጋኔቦ እንዳሉት በምርጫ ክልሉ ባሉ 102 የምርጫ ጣቢያዎች 84 ሺህ 514 መራጮች በዛሬው ዕለት በሠላማዊ ሁኔታ ድምጻቸውን ለፈለጉት ፓርቲ ሲሰጡ ውለዋል።

በቁጫ ምርጫ ክልል 9 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን አስመዝግበው የምርጫ ሂደቱ የተካሔደ ሲሆን የተፎካካሪ ፓርቲዎች ታዛቢዎች እና የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት ታዛቢዎች በአግባቡ ሀላፊነታቸውን መወጣታቸውን አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።

በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ካለው ከመራጭ ብዛት የተነሳ በተያዘው ሰዓት የድምጽ አሰጣጡ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ለምርጫ ቦርድ ሪፓርት ተደርጎ ከምሽቱ እስከ 6:00 እንዲራዘም መፈቀዱን ሀላፊው ተናግረዋል።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሠላማዊ መሆኑንም ሀላፊው ገልጸዋል።

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስ...
01/06/2026

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።

Address

Arba Minch'

Telephone

+251910720746

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share