Arba Minch College of Health Science

Arba Minch College of Health Science Arba Minch College of Health Science one of Health Science Collages in the region striving to produce competent health professionals for the country

ይነበብ!
04/05/2026

ይነበብ!

የሀዘን መግለጫ፤አርባ ምንጭ መጋቢት 02 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)በጋሞ ዞን ደጋማ አከባቢዎች በሰሞኑ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክኒያት በወገኖቻችን ላይ በተከሰተዉ ሞት...
11/03/2026

የሀዘን መግለጫ፤

አርባ ምንጭ መጋቢት 02 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)

በጋሞ ዞን ደጋማ አከባቢዎች በሰሞኑ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክኒያት በወገኖቻችን ላይ በተከሰተዉ ሞት እና ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፡፡

የኮሌጃችን ማኔጅመንት ለተጎጂ ቤተሰቦች እንዲደርስ ለጋሞ ዞን አስተዳደር 100000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ሃምሳ ፍራሾችን ድጋፍ ለማድረግ የወሰነ ሲሆን በቀጣይም ለወገኖቻችን የሚደረገዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን!!

ነፍስ ይማር!

የምርምር ንድፈ ሀሳብ አጻጻፍ እና ተማሪዎችን ማማከር ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለኮሌጁ መምህራን ተሰጠአርባ ምንጭ የካቲት 20 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)በአርባ ም...
28/02/2026

የምርምር ንድፈ ሀሳብ አጻጻፍ እና ተማሪዎችን ማማከር ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለኮሌጁ መምህራን ተሰጠ

አርባ ምንጭ የካቲት 20 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)

በአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ለተዉጣጡ የኮሌጁ መምህራን ለተከታታይ ሁለት ቀናት በምርምር ንድፈ ሀሳብ አጻጻፍ እና ተማሪዎችን ማማከር ክህሎት ላይ በማተኮር ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናዉ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እና የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የምርምር ጽሑፎችን የኮሌጁ ተመራማሪዎች ማቅረብ እንዲችሉ ለማድረግ የሚያግዝ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በምርምር ዙሪያ መምህራኑ ተማሪዎቻቸዉን በአግባቡ የሚያማክሩበት ክህሎት ከፍ እንዲል ታስቦ የተሰጠ ነዉ፡፡

ኮሌጁ በምርምር ስራዎች ዙሪያ የኮሌጁን ተመራማሪዎች አቅም ለማጎልበት መሰል ስልጠናዎችን መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርመራ መርሃ-ግብር ተከናወነአርባ ምንጭ የካቲት 21 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ...
28/02/2026

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርመራ መርሃ-ግብር ተከናወነ

አርባ ምንጭ የካቲት 21 ፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የኮሌጁን በጎ ፍቃደኛ መምህራን እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመጡ የህክምና ተማሪዎችን በማስተባበር በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ለኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርመራ መርሃ-ግብር አከናዉኗል፡፡

በመርሃ ግብሩ የደም ስኳር ምርመራ፤ የደም ግፊት ምርመራ ፤ የዉፍረት መጠን ልኬት (BMI በመጠቀም) እና የምክር አገልግሎቶች በነጻ ተሰጥተዋል፡፡

መርሃ-ግብሩ ኮሌጁ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፋ በየሩብ አመቱ ለማከናወን ከያዛቸዉ ተግባራት አንዱ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ለጀመረዉ የአንድሮ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡አርባ ምንጭ የካቲት 03፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮ...
10/02/2026

በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ለጀመረዉ የአንድሮ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

አርባ ምንጭ የካቲት 03፤ 2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)

ለበርካታ አመታት ግንባታዉ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየዉ እና በቅርቡ ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ለጀመረዉ የአንድሮ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በምረቃዉ ወቅት ቃል በተገባዉ መሰረት ለጤና ተቋሙ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ በኮሌጁ በኩል ተደርጓል፡፡

ድጋፉን ለጤና ተቋሙ ያስረከቡት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አዳነ አልቶ እንደተናገሩት በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን በመስራት የሚታወቀዉ ኮሌጃችን ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸዉ ጥያቄዎች አንዱ የሆነዉ የአንድሮ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግንባታ በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በመጠናቀቁ እጅግ በጣም ደስተኛ በመሆን ጤና ተቋሙን በግብአት ለማጠናከር ቃል በተገባዉ መሰረት የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በድጋፉም የተለያዩ መድሐኒቶች ፤ ማይክሮስኮፕ፤ የህሙማን አልጋ ፤ ፍራሽ ፤ እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉሉ ወንበሮች ተካተዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡

“ክብር ለህዝባችን”

03/01/2026

የአርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ባለበት ሰዓት በአዳራሹ አንደኛ ፎቅ ላይ ያለው የመከላከያ ብረት ተሰብሮ ጉዳት ደረሰ።

ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ የጋሞ ባህል አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ በነበረው የምረቃ ስነ-ስርዓት በአዳራሹ ላይኛው መድረክ ላይ የነበሩ ሰዎች ብረቱ መሸከም ከሚችለው በላይ በመደገፋቸው ብይዱ ለቆ ጉዳት በመድረሱ በአ/ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ፣ድልፋና መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና አ/ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ኮምፕርሄንስቭ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ታካሚዎችን በምረቃው ላይ የነበሩ የክልል እና የጋሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣የኮሌጁ ሀላፊዎች፣የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ እና የአ/ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ ተዘዋውሮ ጎበኝተዋል።

በጉዳቱ ስድስት ሰዎች ላይ መካከለኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አስራ ሶስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት በመድረሱ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና አግኝተው ወደቤታቸው መሄዳቸውን በጉብኝት ወቅት ማረጋገጥ ተችሏል። መካከለኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጅዎች በሆስፒታሎች ላይ አስፈላጊው ህክምና እየተደረገላቸው ያለ ሲሆን ኮሌጁ የሚጠበቅበትን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

26/12/2025

Address

Konso Sefer
Arba Minch'

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251468812572

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch College of Health Science posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Arba Minch College of Health Science:

Share