Geresse zuria woreda police office

Geresse  zuria woreda police office Police

17/03/2026
08/03/2026

እናትን የገደለዉ አባትህ ነዉ ሲባል የሰማዉ ወጣት የገዛ አባቱን ገደለ

አቢቲ ገልማ የተወለደው እና ያደገው በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነው፡፡ አቢቲ ገልማ አሁን ላይ የአስራ ዘጠኝ አመት ወጣት ሲሆን በአብዛኛው አባትዉ ያሣደገው ከእናቱ እናት ከአያቱ ጋር ነው።

አቢቲ ነፍስ አውቆ ወደ ወጣትነት እድሜ እስኪደርስ ድረስ ስለወላጅ እናቱ ሲጠይቅ በቤተሠቡ በኩል የሚነገረው እናቱ እሱን ስትወልድ በወሊድ ጊዜ እንደሞተች ስለተነገረው ስለ እናቱ ሞት ምክንያት እሱ መሆኑ እየተሰማው ጥያቄውን ሳያነሣ ቆይቷል፡፡

ታሕሣስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ግን አንድ ለዓመታት ያልተፈቱ ጥያቄዎችን የሚፈታ ነገር አቢቲ ገልማ ይሰማል።

ይህውም የእናቱ እናት አያቱ ከአብቲ አባት ገልማ በረ ባሮ ከተባለው ጋር ያለመግባባት ፈጥረው ሲጨቃጨቁ በመሐል የአቢቲ አያት የአቢቲ አባት ገልማን ፣ና እኔንም እንደ ልጄ ግደለኛ ፣ለዓመታት የደበኩል ሚስጥር አፍኜ በያዝኩ ፣ብለው ሲናገሩ አብቲ ይሰማል።

በዚህ ጊዜ አባት፣ ይህንን ሚስጥር ይህ ልጅ ይስማና፣ በማለት አስጠንቅቆ ከቤት ይወጣል።አቢቲ ከዚያን እለት ጀምሮ የእናቱ ሞት በወሊድ አለመሆኑን ሲያውቅ በአባቱ ላይ ጥላቻ እያሳየ መጣ።

በዚህም አባትና ልጅ ቅራኔ ውስጥ ገቡ።አብቲም የእናቱን ሞት ምክንያት ለማወቅ አያቱን በተደጋጋሚ ቢጠይቅም መልስ በማጣቱ አያቱን ለመጨረሻ ጊዜ ካልነገሩት አገር ጥሎ እንደሚሰደድና እንደሚጠፋ ሲነግራቸው ለአመታት የደበቁት ሚስጥር ነገሩት።

እናቱ ድንገት በአባቱ እጅ እንደጠፋች ይሕንንም ሚስጥር ከአባቱና ከእሣቸው በስተቀር ማንም እንደማያቅ አስረዱት።

አብቲ ለአመታት የተደበቀውን የእናቱን አሟሟት ሚስጥር እንዳረጋገጠ በቀጥታ አባቱን ለመበቀል ጊዜና ወቅት ሲጠብቅ አንድ ቀን አባት ና አያቱ ተጋጭተው ባለበት ሠዓት አብቲ ፣እናቴን እንደ ገደልክ አያቴንም ግደላታ፣በማለት በያዘው የብረት ዱላ የተለያየ የሰውነት ክፍላቸውን በመምታት ጉዳት ካደረሰባቸው በኃላ ጥሏቸው በመሔድ በቀጥታ እጁን ለፖሊስ ይሰጣል።

ፖሊስ ጉዳት የደረሠባቸው ገልማ በረ ባሮ በማንሣት ወደ ሆስፒታል በመላክ የሕክምና እርዳታ እንዲደረገላቸው ቢያደርግም ከአራት ቀን ቆይታ ጥር፣28 ቀን 2018 ዓም በሕክምና ላይ ሕይወታቸው ያልፋል።

በዚሁ መሠረት ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራ ና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሠው መግደል ወንጀል ክስ ይመሠርታል።

የአቃቢ ሕግን ክስ የተመለከተው የቦረና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 10 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ አቢቲ ገልማ፣ከዚሕ ፊት የወንጀል ድርጊት የሌለበት፣ ተፀፅቶ እጁን ለሕግ አካላት የሠጠ መሆኑ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመውም አስገዳጅ የእድሜ ሁኔታ ውስጥ በመግባት በመሆኑ የክስ ማቅለያ ተደርጎለት በዘጠኝ አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Bisrat Fm

23/02/2026
28/01/2026
21/01/2026

ዶሮ ወጥ ዝም ብሎ አይሰራም ያለችውን የትዳር አጋሩን በሽጉጥ የገደለ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ አስታወቀ፡፡

በትዳር ሕይወት ውስጥ ግጭቶች ሊፈጠሩ ቢችሉም፣ መጨረሻቸው እንዲህ ይዘገንናል ተብሎ አይታሰብም። በሰሜን ሸዋ ዞን፣ ፍታል ከተማ ውስጥ የሚኖሩት የአቶ ቦጋለ ኃይሉና የወይዘሮ አባይቱ ከበደ ትዳር ለዓመታት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ በአርአያነትና በምሳሌነት የሚጠቀስ ነበር።

ሆኖም ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተው ድንገተኛ ክስተት፣ ያን ሁሉ ዓመት የተገነባውን ክብርና ፍቅር በአንድ ጀንበር አፈረሰው።

የ75 ዓመቱ አዛውንት ከገበያ የገዟት አንዲት ዶሮ፣ የባለቤታቸውን ሕይወት ለመቅጠፍ ሰበብ ትሆናለች ብሎ የገመተ አልነበረም። ፍታል ከተማ በአየር ንብረቷና በሰላማዊ ነዋሪዎቿ ትታወቃለች።

አቶ ቦጋለ ኃይሉ በዚህች ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በክብር የኖሩ አባት ናቸው። ከባለቤታቸው ከወይዘሮ አባይቱ ጋር ያሳለፉት የትዳር ዘመን ረጅም ከመሆኑም በላይ፣ በመካከላቸው የነበረው መከባበር ለጎረቤት ሁሉ መነጋገሪያ ነበር።

“እንደ ቦጋለና አባይቱ ይሁንላችሁ” ተብሎ እስከ መመረቅ ደርሰውም ነበር።ዶሮ ገዝተው ወደ ቤት ሲገቡ፣ ምሽቱ እንዲህ ጭልምልም ያለ በዕለቱ አቶ ቦጋለ ከገበያ አንድ እንደሚሆን ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አልነበራቸውም። ሰዓቱ ምሽት 11፡00 ነው።

አቶ ቦጋለ የዶሮ ወጥ ናፍቋቸው ስለነበር፣ ባለቤታቸውን “አባይቱ፣ ዛሬ ዶሮ አምሮኛልና ስሪልኝ” የሚል ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጡ። ሆኖም ወይዘሮ አባይቱ የቤቱን ሁኔታ ያውቁታል።
ዶሮ ለመሥራት ሽንኩርት፣ ቅመም፣ ቅቤና ረጅም ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ፤ “ዶሮ ዝም ብሎ አይሠራም፣ ግብዓቶች ያስፈልጉታል።

ያንን ሳታሟላ እንዲህ ማለትህ ተገቢ አይደለም” በማለት መለሱላቸው።ይህ መልስ በአቶ ቦጋለ ልብ ውስጥ ያልተጠበቀ ቁጣን ቀሰቀሰ። ድምፃቸው ተሰምቶ የማይታወቁት ባልና ሚስት መጮኽ ጀመሩ።

ጭቅጭቁ ከዶሮ አልፎ ወደ ቀድሞ ቂሞችና ንግግሮች ተሸጋገረ። ድምፁ ርቆ ስለተሰማ ጎረቤቶች ደንግጠው ወደ ቤታቸው በመግባት “ተው አቶ ቦጋለ! ተይ ወይዘሮ አባይቱ!” በማለት ገላገሏቸው።

አቶ ቦጋለ ግን ቁጣቸው አልበረደም ነበር። ቤቱን ለቀው ወጡ፤ ሲወጡ ግን በደብተር ቁጥር AL-34021 የተመዘገበ ማካሮፍ ሽጉጣቸውን ይዘው ነበር። ወደ መጠጥ ቤት በመሄድም ንዴታቸውን በሚያባብስ መልኩ መጠጥ ቀማመሱ።

አቶ ቦጋለ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ገደማ ወደ ቤት ተመለሱ። ዶሮዋ ታርዳ ወጥ ትሆናለች ብለው ቢጠብቁም፣ ወይዘሮ አባይቱ ግን ሥራቸውን ቀጥለው ወተት እያለቡ ነበር። ይህን ሲያዩ የአቶ ቦጋለ ንዴት ጣሪያ ነካ።

ያን የፍቅር አጋራቸውንና የልጆቻቸውን እናት እንደ ጠላት ተመለከቷት። መለስ ብለው ማሰብ ተሳናቸው። የያዙትን ማካሮፍ ሽጉጥ መዘው ወተት እያለቡ በነበሩት ባለቤታቸው ላይ አከታትለው ሦስት ጊዜ ተኮሱ።

የከተማዋን ጸጥታ የጥይት ድምፅ ሰበረው።ወይዘሮ አባይቱ በሦስት ጥይት ተመትተው በደም ተጥለቅልቀው ወደቁ።

አቶ ቦጋለ ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው የጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ዋሉ። ተጎጂዋ በፍጥነት ወደ ፍታል ጤና ጣቢያ ቢወሰዱም፣ በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።

ፖሊስ አስከሬኑን ወደ አቤት ሆስፒታል በመላክ ባደረገው ምርመራ፣ ሦስት በዶሮ ምክንያት የፈረሰው ጎጆየሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ ጥይት ማረፉንና ለሞት ምክንያት መሆኑን አረጋገጠ። ለዓመታት በሰላም የኖረው ቤት በደም ተጨማለቀ።

ፍርድ ቤት መታየት ጀመረ።አቃቤ ጉዳዩ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ሕግ ዳዊት ንጉሴና ዳንኤል በቂ ማስረጃዎችን በማቅረብ አቶ ቦጋለ ላይ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መሰረቱ።

ሕዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎት፣ የ75 ዓመቱ አረጋዊ ቦጋለ ኃይሉ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋገጠ።በእድሜያቸው ምክንያት ሊታሰብላቸው ቢችልም፣የወንጀሉ ክብደት ግን በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ አስገደደ።

የተደመደመው ይህ አሳዛኝ ታሪክ፣ በዶሮ ናፍቆት ተጀምሮ በደም ለንዴትና ለቁጣ ቦታ መስጠት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ለከተማው ሰው ትልቅ መማሪያ ሆኖ አልፏል። ትዕግስት በሌለበት ቤት ውስጥ ፍቅርም ሆነ ክብር ቦታ አይኖራቸውም።

አቶ ቦጋለ ኃይሉ ቀሪ ዘመናቸውን በጸጸትና በወህኒ ቤት እንዲያሳልፉ የተፈረደባቸው፣ አንዲት ዶሮን ሰበብ አድርገው ቁጣቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ነው። ይህ የወንጀል ጉዳይ ለሁላችንም የሚያስተምርና የሚያስጠነቅቅ ታሪክ ነው ሲል ፖሊስና ርምጃው ጋዜጣ ጠቅሶ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘገቧል፡፡

20/01/2026

"የደንብ ልብስ ለብሼ የምጠብቀው የህዝብን ሰላም ብቻ ሳይሆን የህዝብን ንብረትም ጭምር ነው" በስህተት ወደ አካውንቱ የገባ ገንዘብ በታማኝነት የመለሰው የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ በልደረባ ሳጅን ዋስይሁን በፍቃዱ።

ወላይታ ሶዶ ጥር 11/2018(ደኢፖኮ)

አንድ መቶ አርባ አምስት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ብር በስህተት ወደ አካውቱ ገብቶ በታማኝነት መልሷል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አባል ሳጅን ዋሲይሁን በፈቃዱ አስደናቂ ታማኝነቱን በተግባር አሳይቷል።

ከአቶ ይልቃል ዘውዴ ተሰማ በኩል በስህተት 145,290 (አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና) ብር ወደ ሳጅን ዋሲይሁን የባንክ አካውንት ይገባል።

ሳጅኑ ገንዘቡ በስህተት እንደገባ በተረዳበት በዚያው ቅጽበት፣ ምንም አይነት ማመንታት ሳያሳይ በዚያኑ ዕለት ሙሉ ገንዘቡን ለባለቤቱ መልሷል።

"የደንብ ልብስ ለብሼ የምጠብቀው የህዝብን ሰላም ብቻ ሳይሆን የህዝብን ንብረትም ጭምር ነው" የሚል መልዕክት የሚያስተላልፈው ይህ ተግባር፣ ለሙያ ባልደረቦቹም ሆነ ለህብረተሰቡ ትልቅ ትምህርት ሆኗል።

ባለቤቱ አቶ ይልቃል ዘውዴም በሳጅን ዋሲይሁን ድርጊት እጅግ መደሰታቸውንና ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

ክብር ለታማኙ የፖሊስ አባላችን!
እንዲህ ያሉ የሞራል ጀግኖች ሊበረታቱና ሊመሰገኑ ይገባል።

12/01/2026

Address

Geresse
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Geresse zuria woreda police office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share