Gamo Zone Finance and Plan Department

Gamo Zone Finance and Plan Department የሀብት ብክነትን በጋራ እንከላከል!!

28/05/2026
ዛሬ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ  የድጋፍ ሰልፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሄደ።
26/05/2026

ዛሬ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ የድጋፍ ሰልፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሄደ።

የሐዘን መግለጫየጋሞ ዞን ፋይናስና ፕላን ልማት መምሪያ ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ ሔዋን በረደድ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ግንቦት 13፣ 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለ...
21/05/2026

የሐዘን መግለጫ

የጋሞ ዞን ፋይናስና ፕላን ልማት መምሪያ ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ ሔዋን በረደድ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ግንቦት 13፣ 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት መምሪያው ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡
ወ/ሮ ሔዋን በመ/ቤታችን በነበራቸው ቆይታ በስራቸው ታታሪ፣ ምስጉን እና በስነምግባራቸው የተመሰገኑ ባለሙያ ነበሩ፡፡
መምሪያው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

መምሪያው

20/05/2026
የጋሞ ዞን ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛ ዙር የህዝብ ክንፍ ውይይት ተደረገ።ግንቦት 10፣ 2018 ዓ.ምአርባ ምንጭየውይይቱ ተሳታፊዎች ከሁሉም ሴክተር መስሪ...
19/05/2026

የጋሞ ዞን ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛ ዙር የህዝብ ክንፍ ውይይት ተደረገ።

ግንቦት 10፣ 2018 ዓ.ም
አርባ ምንጭ

የውይይቱ ተሳታፊዎች ከሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የልማት እቅድ ባለሙያዎች ሲሆኑ የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም እና ቀሪ ስራዎች ለውይይት ቀርቧል።

በመድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበረ በመምሪያው አገልግሎት አሰጣጥ የታዩ ጠንካራ ጎን እና የአፈፃፀም ጉድለት በጥልቀት ተገምግሟል።

በውይይቱ በርካታ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረክ እና አዘርፍ ሀላፊዎች ማብራሪያ እና መልስ የተሰጠ ሲሆን የታዩ ክፍተቶችን በማረም ቀሪ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተገልጿል።

የጨረታ ማስታወቂያ
18/05/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

ክፍት የስራ ማስታወቂያ
18/05/2026

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የስነህዝብና ልማት ከሀይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሔደ፡፡ግንቦት 07፣ 2018 ዓ.ምአርባ ምንጭየጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪ...
15/05/2026

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የስነህዝብና ልማት ከሀይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሔደ፡፡
ግንቦት 07፣ 2018 ዓ.ም
አርባ ምንጭ
የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የስነህዝብ ልማት ዳይሬክቶሬት ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይነት ያለው የምክክር መድረክ እንደሚዘጋጅ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የ2018 በጀት ዓመት ውይይት ትላንት ሲደረግ ውሏል፡፡ በውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ሰነድ በንባብ የቀረበ ሲሆን በይዘቱ
• ፈጣን የስነህዝብ ቁጥር እድገት የሚያስከትላቸው ችግሮች፤
• የማህበራዊ አገልግሎቶች ውስንነት፤
• በቤተእምነቶች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ፤
• የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ጥቅም፤
• ኑሮ እና የእምነት አስፈላጊነት የሚሉ ፅንሰሀሳቦች ዙሪያ ጥልቅ እና ዝርዝር ሀሳብ የያዘ ነበር፡፡ በመድረኩ ከተወያዮች እና ከመድረክ በርካታ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች የተንሸራሸሩ ሲሆን በስነህዝብ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመጨበጥ ተችሏል፡፡

Address

Arba Minch'

Telephone

+251468810007

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Finance and Plan Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Zone Finance and Plan Department:

Share