26/03/2026
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8)ቀን
በድምቀት ተከበረ።
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በዓለም ለ115 ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች ''የሴቶች ድምጽ እኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ'' በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች ምክንያት በማድረግ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌያት በተለያዩ ዝግጅቶች ስከበር መሰንበቱን ወ/ሮ ዝዋይ ደለለኝ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።
የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ( ማርች 8 ) ታሪካዊ መነሻው የሠራተኞች እንቅስቃሴ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመድ ዕውቅና የተሰጠው ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሆን መብቃቱን ወ/ሮ ዝዋይ አስታውሰዋል።
በመሆኑም ሴቶች ከወንዶች እኩል የመስራት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ የመሰብሰብ እና የመምራት መብቶቻቸዉን ለማስከበር መደራጀትና በጋራ መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ዝዋይ ገልፀው ሴቶች ለራሳቸውም ይሁን ለሀገራቸው ለውጥና እድገት ተግተው መስራትም ይጠበቅባቸዋል ስሉ አሳስበዋል።
በመድረኩ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሴቶች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በወሪት/ ቤተልሔም ይልማ የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የወረዳው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አማካኝነት ተላልፏል።
በመድረኩ ዕለቱን አስመልክቶ ስለማርች 8 የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ መርጊያ ማንቻ የጽ/ቤቱ ሴቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ማስፋፊያ ባለሙያ የቀረበ ሲሆን፤ ከህግ ማዕቀፍ ተጠቃሚነት እረገድ የተዘጋጀ ሰነድም በወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህግ በሆኑት በአቶ ጎሳ ጎጆ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል።