North Wollo Zone Women's, Children's And Social Affairs Department

North Wollo Zone Women's, Children's And Social Affairs Department ራዕያችን፡-

03/07/2023
13/06/2023
25/03/2023
24/03/2023

ለአብክመ ሴቶች ፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች

1. በክልሉ ውስጥ የሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር የሚረዱ የፖሊሲ ሃሣቦችን ያመነጫል፣ የማስፈፀሚያ ስልቶችን በመቀየስ ለተግባራዊነታቸው አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤
2. በሴቶች፣ በህፃናት፣ በአካል ጉዳተኞች እና በአረጋዊያን መብቶች ዙሪያ የተደነገጉ ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና አገራዊ ስምምነቶች በክልሉ ተፈጻሚ ስለመሆናቸው ክትትል ያደርጋል፣
3. ብሄራዊው የሴቶች ፖሊሲ፣ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ እና የህጻናት ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን በክልሉ ውስጥ የሚካሄዱ ጥረቶችን ያስተባብራል፤
4. በክልሉ መንግሥት አካላት የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ የልማት ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና ሪፖርቶች የስርዓተ-ጾታን፣ ህጻናትን፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ለማካተት የሚያስችላቸውን ስልት በመንደፍ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ በሂደትም የሴቶችን፣ ህጻናትን፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞችን ተሣትፎና ተጠቃሚነት ያረጋግጣል፤
5. በሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚቃጡ መድልዎችን፣ ጥቃቶች እና የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጥናት በመለየት እነዚሁ የሚወገዱባቸውን የመፍትሄ ሃሣቦች ያመነጫል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
6. ልዩ ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን የተዛባ አመላካከት ለመቀየር የሚያስችል ቀጣይነት ያላቸው የግንዛቤና የንቅናቄ ስራዎችን ያከናዉናል፣
7. በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ዝውውርና ፍልሰት፣ የጉልበት ብዝበዛ እና ሌሎች የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የሚረዱ የአሰራር ሥርዓቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይዘረጋል፣
8. ሴቶች ለዘመናት በበታችነትና በልዩነት ከመታየታቸው የተነሳ የደረሰባቸውን ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ ተሣትፏቸውን ለማሳደግ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ መስጠት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለክልሉ መንግሥት ሃሣብ ያቀርባል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፤
9. ሴቶችና አካ ጉዳተኞች በክልሉ ውስጥ የስራ፣ ቅጥር፣ የስልጠና እና የደረጃ እድገት እድሎች ሆነ እነዚህኑ ለማስፈጸም በሚደራጁ የተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በሚገባ ስለመወከላቸው ይከታተላል፣
10. የተለያዩ የክልሉ መንግሥት አካላት ሴቶችን በውሣኔ ሰጭነት ቦታዎች በመመደቡ ረገድ በቂ ትኩረት ስለመስጠታቸው ይከታተላል፤ ብቃት ያላቸውን ሴቶች እየለዩ በየደረጃው ለሚገኙ ወሳኝ አካላት ያቀርባል፣
11. ሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች እንደየ ችግሮቻቸው አይነት በነጻ ፍላጎታቸው ተደራጅተው ለመብቶቻቸውና ለጥቅሞቻቸው መከበር እንዲታገሉና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ በሙሉ አቅማቸው እንዲሳተፉና ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል፣ በየተቋቋሙበት አግባብ ተግባራቸውን እየተወጡ ስለመሆኑም በቅርብ ይከታተላል፤
12. በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና እና ሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ እንዲጠኑ ያደርጋል፣ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በዚሁ ዓላማ ላይ ተመስርተው ለሚንቀሳቀሡ ድርጅቶች አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
13. ስርዓተ-ጾታን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከተለያዩ የማህበረ-ሰብ ተቋማትና ከራሣቸው ከሴቶች ማህበራት ጋር ተባብሮ ይሰራል፤
14. የጾታ እኩልነትን ለማስፈን፣ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሴቶችን ተሣትፎ ለማጎልበትና ህብረተ-ሰቡ በሴቶች ላይ ያለውን የተሣሣተ ግንዛቤ ለመቀየር የሚረዱ ስልጠናዎችንና ዓውደ-ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ውጤቶቻቸውንም ይገመግማል፤
15. የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍትሀዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዱ ስልጠናዎችንና ዓውደ-ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ውጤቶቻቸውንም ይገመግማል፤
16. ሴቶችን፣ አረጋዊያንን እና አካል ጉዳተኞችን ለሚያግዙና ለክልሉ ዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል ሀብት ያፈላልጋል፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆንም ድጋፉ የአነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወት ለማሻሻል ስለመዋሉና ውጤታማ ስለመሆኑ ይከታተላል፤
17. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የቤተ-ሰብና የህፃናት መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ ለማድረግና የጋብቻ ስርዓትን ለመንከባከብ የወጡ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤
18. ሴቶችን፣ ህጻናትን፣ አረጋዊያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል አድርገው የሚሰሩ የተለያዩ አካላትን የተግባር ዕቅድና አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲኖራቸው ያስተባብራል፤
19. የሀገሪቱ ማህበራዊ ጉዳይ ፖሊሲዎችና ህጎች በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
20. ዝርዝሩ ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣ ደንብ የሚወሰን ሆኖ በስራ ላይ ያሉትን የአረጋዊያን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የህጻናትና ሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ድጋፍ፣ ተሀድሶና እንክብካቤ ማዕከላት ያስተዳድራል፣ በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እንደተገቢነታቸው መሰል ማዕከላትና ድርጅቶች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤
21. የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ይወገዱ ዘንድ የክልሉን ህብረተ-ሰብ ሁለንተናዊ ጥረት ያስተባብራል፣ እንደ ሴትኛ አዳሪነትና ጎዳና ተዳዳሪነት ባሉ አስከፊ ችግሮች ላይ የወደቁ ወገኖችን ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣ ይደግፋል፡፡
22. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለከፋ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን የድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ አማራጭ የድጋፍ ስልቶችን ይቀይሳል፣ ተጋላጮችን ይለያን፣ ድጋፉን ያስተባብራል፣
23. በገጠር ሆነ በከተማ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ውስጥ በቀጥታ ተጠጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መረጃ ይለያል፣ ያደራጃል፣ ለተጠቃሚነታቸው ከሚመለከታቸው አካት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣
24. የሴቶች፣ ህጻናት እና ሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚመለከት ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ስርአት ይዘረጋል፣
25. የማህበራዊ ጥበቃ ቋተ-ንዋይን ያቋቁማል፣ ወጤታማ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
26. የዜግነት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥርዓት እንዲዘረጋና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፣
27. የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር የሕፃናት መልካም አስተዳደግና ስብዕና ግንባታ፣ ድጋፍ፣ እንክብካቤ እና ተሀድሶ ላይ ለወላጆችና አሳዳጊዎች ተገቢውን ግንዛቤና ሥልጠና በመሥጠት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፤
28. በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡና ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ጉዲፈቻን ጨምሮ በሀገር ውስጥ ባሉ አማራጭ ድጋፍና እንክብካቤ ዘዴዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤

Address

Amhara Region
Amhara Region

Telephone

+251333312426

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North Wollo Zone Women's, Children's And Social Affairs Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share