20/05/2026
በጪዳ ከተማ አስተዳደር ከጫ ቀበሌ 7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ይምረጡኝ ቅስቀሳ እና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተደርጓል።
በመርሃግብሩ ተገኝተው ለወጣቶች መልዕክት ያስተላለፉት የጪዳ ከተማ አስ/ር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ካንሳ የተሻለችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ምርጫውን ብልጽግና ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።
የተጀመሩ ልማቶች ወደ ግብ እንድደርስ ወጣቱ ትውልድ የብልጽግና ፓርቲን መምረጥ እንዳለበት ያሳሰቡት የፓርቲው ኃላፊ ወጣቶች መምረጥ ብቻ ሳይሆን ከማስመረጥ ረገድም ድርሻ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ወጣቱ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ ከማስከበር አኳያም ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አቶ ደምሴ አክለው ገልጸዋል።
የቀበሌ ወጣቶችም ፓርቲው በርካታ ራዕይ ያለው በመሆኑ ነገ ላይ የተሻለችውን ኢትዮጵያን ለማየት ምርጫችን ብልጽግና ነው ሲሉ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን አጋርነት በግልጽ አሳይተዋል።
በመድረኩም የከተማ አስ/ር ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ካንሳ፣የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ብራሞ በቀለ እና ሌሎችም ደጋፍ አመራርና የቀበሌ ወጣቶች ተገኝተዋል።
ዘገባው፦ብልጽግና ፓርቲ የጪዳ ቅ/ጽ/ቤት ነው።