30/12/2023
የአዲሱ ወረዳው ስያሜ ፥ወረዳው የሚይዛቸው ቀበሌያት ላይ በአቶ ጢሞቲዎስ በቀለ የኮሬ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ እና የአደረጃጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ ለምክር ቤቱ አባላት ሞሽን አቅርበዋል።
በዚህ መሠረት ጎርካ ወረዳ የወረዳ ስያሜ ሲሆን
ማዕከሉ ጂጆላ ከተማው እንዲሆን የምክር ቤቱ አባላት በሰፊው ከተወያዩ በኋላ በቀረበው ሞሽን ጥያቄና ማብራሪያ ከተሠጠ በኋላ ሞሽኑ በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
በመጨረሻም ጉባኤው በጎርካ ወረዳ ተጠባባቅ ዋና አስተዳደር አቶ አገኘሁ በቀለና የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ሞሮማ ጨንዶ የኢትዮጵያ ናየደቡብ ኢትዮጵያ ባንድራ በመሥቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ሥነ ሥርዓት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።