31/07/2023
# # #ሰለም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ሰው የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።
**********
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር "የጋራ መነሻና መዳረሻ ካበጀን ከአሸናፊነት መንገድ ላይ እንገናኛለን!" በሚል መሪ ቃል በውቅታዊ ሀገራዊ የሰላም ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ከፍለ ሙላቴ፣ አቶ አለምሸት ቢያዝን፣አቶ አየነው እብስት የዞን አመራሮች የከተማና የወረዳ አመራሮች ፣የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች ፣ወጣቶች፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አማረ ሰውነት በመግብያ ንግግራቸው እንደገለፁት በከተማችን ብሎም በክልላችን የሚሰተወሉ ችግሮችን መፍትሄ በማበጀት ሰላም እንዲረጋገጥ ወጣቶች፤ የሃገር ሽማግሌዎች፤የሃይማኖት አባቶች ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የሚስችል ውይይት እንደሆነ አብራርተዋል።
ያአደሩ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን መሰከን ባለብን ስዓት ሰክነን መፈጠን ባለብን ሰዓት ፈጥነን ችግሮችን መፍታት ያስፈልጋል ያሉት ከንቲባው ስለዚህ ሌላውን ለመታገል እኛ አንድ ሁነን በመደማመጥ ለችግሮቹ እልባት እስክናገኝ ድረስ ልንታገል ይገባል ብለዋል።
የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አየነው እብስት አማራን አማራ በመግደል ገዳዮች በዘተው እርዕስ በዕራስ የመጠፋፋት ሴራ እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው ስለዚህ አንድነትን ሊያመጣ በሚችል መንገድ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የአማራ ህዝብ አንድ ሁኖ እንዳይቀጥል የተለያዩ አክቲቪስቶች ያልሆነ ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ነው ያሉት ደግሞ የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ አለምሸት ቢያዝን ሲሆኑ ለመረጠን ህዝብ በክልላችን ላይ የሚታዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ እኛም ትግል እያደረግን ነው ብለዋል።
የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ከፍለ ሙላቴ በአማራ ላይ የተጋረጠውን ችግር የሚፈታ ህዝብ አለ ነገር ግን ያለመደማጥ ችግሮች አሉ ሰከነን ስንነጋገር አሸናፊ እንሆናለን ብለዋል።
አያይዘውም የጋራ የሆኑ ጠላቶቻችን በመለየት እና ከመንግሥት ጎን በመሆን ሁላችንም ትግላችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።