Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት

Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በከተማው የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ለህዝብ ከማስተዋወቅም ባሻገር፡ ህዝብን ከመንግሥት፣ መንግሥትን ከህዝብ ጋር ለማገናኘትና ለማስተሳሰር የሚሰራ ተቋም ነው!!
(2)

በበጀት ዓመቱ ቀሪ ግዜ ውስጥ የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት እርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብ ስራን...
03/06/2026

በበጀት ዓመቱ ቀሪ ግዜ ውስጥ የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት እርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብ ስራንና የደረጃ ''ሀ'' እና ''ለ'' ግብር አከፋፈል አፈጻጸምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብድልቃድር ኢማም ሎላሶ በመሩት በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ በቀሪ ጊዜያት የገቢ አሰባሰቡን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ያለምንም መዘናጋት ቀን ከሌት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመደበኛና በማዘጋጃ ቤት ዘርፍ እስካሁን የተከናወኑ የገቢ አፈጻጸሞች የተገመገሙ ሲሆን የከተማውን የወጪ ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በቀጣይ በቀሪ ቀናት የደረጃ ''ሀ'' እና የደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ በማድረግ፣ የኦዲት ውዝፍ ያለባቸውን በልዩ ሁኔታ በመለየት፣ የደረሰኝ ቁጥጥር ስራን በማጠናከርና ወርሃዊ ሪፖርቶችን በትክክለኛው ጊዜና ጥራት በማደራጀት የተሸላ የገቢ አሰባሰብ ስራን ለመስራት እርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

የከተማችን የልማት ፍላጎት እንዲሟላ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት ጠቁመው በዚህም መሰረት የደረጃ "ሀ" ሁለተኛ ዙር (1/4) ግብር ከፋዮችና የደረጃ "ለ" ሶስተኛ ዙር (1/4) ግብር ከፋዮች እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኋላ ለሚመጡ ግብር ከፋዮች ወለድና አስተዳደራዊ ቅጣት የሚሰላ መሆኑን አውቀው ህጋዊ ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲወጡ አሳስበዋል።

03/06/2026
በሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲካሄድ የቆየው የቆሻሻ አወጋገድና የአረንጓዴ ልማት ማህበራት ስልጠና፡ አባላቱን ወደ (Level-1) የብቃት ማረጋገጫ ዕድል የሚያሸጋግራቸው መሆኑ ተገለጸ።-----...
03/06/2026

በሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲካሄድ የቆየው የቆሻሻ አወጋገድና የአረንጓዴ ልማት ማህበራት ስልጠና፡ አባላቱን ወደ (Level-1) የብቃት ማረጋገጫ ዕድል የሚያሸጋግራቸው መሆኑ ተገለጸ።
----------------------------------
ግንቦት 26/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ

ሰልጣኝ ባለሙያዎቹን ከሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት በቀጣይነት በሁለቱም መስኮች ላይ በተለያዩ የምዘና ደረጃዎች መሰረት በሚያዘጋጃቸው የሙያ ስልጠና መርሃ-ግብሮች ላይ በመመዝገብ የሙያ ብቃታቸውን በየደረጃው እያሳደጉ የሚሄዱበት ሥርዓት የተዘረጋ መሆኑ፡ ለሰልጣኞቹም ሆነ ለዘርፉ ስራዎች ውጤታማነት ትልቅ መልካም ዕድልን ይዞ የመጣ መሆኑም ተጠቁሟል።

ከጥቂት ቀናት በፊትም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አማካኝነት በቁሊቶ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ አሰባሰብ እና እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት መስኮች ላይ የተሰማሩ ማህበራትን በደረጃ-1 (Level-1) ለመመዘን የተዘጋጀው የምዘና መድረክ የዚሁ አካል እንደሆነም የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

ይህ ሂደትም በከተማው ውስጥ በሙያቸው ብቁ የሆኑ አባላትን በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን የሚያሳድግ ከመሆኑም በተጨማሪ በሁለቱም ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎችም የሙያ ዕውቅናን ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠናዎቹ በዞናችን ደረጃ በሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ላይ እንዲጀመርና ማህበራቱ በምዘና ስርዓቱ መሰረት የሙያ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ ለማስቻል፡ ማዘጋጃ ቤቱ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ከማዘጋጃ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

👇ከታች በምስሎቹ መካከል የሚገኘው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለማሳያነት ብቻ የተጠቀምነው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን!

▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿

➥ የኦንላይን አገልግሎት የዌብሳይት አድራሻችንን፦ www.halabamun.gov.et ይጎብኙ!

➥ የቴሌግራም ቻናላችንን፦ https://t.me/halabakullitomunicipality ይቀላቀሉ!

➥ የፌስቡክ ገፃችንን፦ https://www.facebook.com/halabakullitomunicipality ይከታተሉ!

➥ የዩቲዩብ ቻናላችንን፦ https://www.youtube.com/ ሰብስክራይብ ያድርጉ!

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሕግ በኢትዮጵያ! #መግቢያበአገራችን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 44(1) መሠረት ሁሉም ሰዎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው እንዲሁም በአን...
02/06/2026

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሕግ በኢትዮጵያ!

#መግቢያ
በአገራችን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 44(1) መሠረት ሁሉም ሰዎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው እንዲሁም በአንቀጽ 92 መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ እንዲኖረው ጥረት የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት በተጨማሪም መንግሥትም ሆነ ዜጎች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል።

ሆኖም በኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥርና የከተሞች እድገትን ተከትሎ ባልተገባ መልኩ የሚጣሉ ደረቅ ቆሻሻዎች ማለትም እንደ ፕላስቲክ/ፌስታል/ ያሉት የውሃ መስመሮችን በመዝጋት፣ ለረጅም ጊዜ ሳይበሰብሱ በመከማቸት የአካባቢን ሥነ ምህዳር እየበከሉ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ደረቅ ቆሻሻዎች የሚሰበሰቡበት፣ የሚጓጓዙበት፣ የሚከማቹበት፣ መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉበት እና የሚወገዱበትን ሂደት የሚገዛ የሕግ ሥርዓት የሚያስፈልግ በመሆኑ የአካባቢ ጥበቃ ሕጎች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ።

ከእነዚህም መካከል የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 በሥራ ላይ ውሏል። በዚህ ጽሑፍም በሕጉ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን አጭር እንመለከታለን።

✅ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ምንነት፤
ደረቅ ቆሻሻን ማለት ማንኛውም ፈሳሽ ያልሆነ ወይም ነፋሽ /gas/ ያልሆነ ቆሻሻ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2(1) ትርጓሜ የተሰጠው ሲሆን ይህም ፈሳሽ ወይም ጋዝ ነክ ከሆኑት ውጭ ያሉ ቆሻሻዎችን ለምሳሌ ፕላስቲክ፣ ጠርሙስ፣ ወረቀት፣ ካርቶን፣ ወዘተ ያካትታል። የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ማለት ይህንኑ ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ መቀነስ፣ በፈርጅ መለየትና መሰብሰብ፣ ማጓጓዝ፣ ማከም፣ መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ዑደት ማድረግ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ባለው መልኩ ማስወገድን እንደሚያጠቃልል በአዋጁ አንቀጽ 2(2) ስር በግልጽ ሰፍሮ እናገኘዋለን።

ስለሆነም ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ እንዳይባዛ መከላከል፣ ከተባዛም በየፈርጁ ለይቶ እንዲሰበሰብ ማድረግና ወደሚፈለግበት ቦታ ማጓጓዝ እንዲሁም አስፈላጊው የማከም ሥራ ታክሎበት መልሶ ጥቅም ወይም ዑደት ላይ የሚውልበት ሂደት መሆኑን መረዳት ይቻላል።

✅ የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን፤
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅን ተፈጻሚነት ስንመለከት በአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1090/2010 በተሸፈኑ አደገኛ ቆሻሻዎች እና ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻዎች በስተቀር በመላ አገሪቱ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ተፈጻሚ መሆኑን በአዋጁ አንቀጽ 3 ስር ተደንግጎ እናገኘዋለን።

ይህ የሆነበት ምክንያትም ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የአደገኛ ቆሻሻዎችን አያያዝና አወገገድን በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 1090/2010 ስለሸፈነው ድግግሞሽን ለማስቀረት እንዲሁም አላስፈላጊ የኃላፊነት መቀላቀልን ለማስወገድ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻዎች የተለየ አደገኝነት ያላቸውና በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ደንብ ቁጥር 425/2010 ላይ ሽፋን ስላገኙ በዚህ አዋጅ እንዳይሸፈኑ ተደርገዋል።

✅ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ መርሆዎች፤
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የሚከተሉትን መርሆዎች መከተል እንዳለበት በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጁ አንቀጽ 4 ስር በግልጽ ተደንግጎ እናገኘዋለን። እነዚህም ፡-

➥ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ /reduction of waste generation from its source/፣
➥ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም /waste reuse፣
➥ ቆሻሻን መልሶ ዑደት ማድረግ /waste recycle/፣
➥ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ /waste disposal/፣
➥ የኅብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ /public participation/፣
➥ የበከለን ማስከፈል /polluter pay/ የሚሉት ናቸው።

✅ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሂደቶች፤
የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የተለያዩ ሂደቶች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡-

• ደረቅ ቆሻሻን መሰብሰብ /collection of solid waste/፡- ይህ ሂደት ከተለያዩ ቦታዎችና ምንጮች የመጣን ቆሻሻ በየፈርጁ የመለየትና በጊዜያዊነት ማከማቸትን ያካትታል። በአዋጁ አንቀጽ 6(3) ስር ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ፣ ከአገልግሎት መስጫ ወይም ማምረቻ ተቋሙ የሚመነጭን ደረቅ ቆሻሻ በየፈርጁ የመለየት፣ አመቺ በሆነ ቦታ በጊዜያዊነት የማከማቸትና ፈቃድ ለተሰጣቸው ቆሻሻ ሰብሳቢዎች የማስተላለፍ ኃላፊነት ተጥሎበታል። ይህ እንዳለ ሆኖ ደረቅ ቆሻሻ ሰብሳቢዎች በማይኖሩበት አካባቢ የሚኖር ሰው ደረቅ ቆሻሻን ጊዜያዊ ማከማቻ ቦታ ድረስ የማድረስ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።

• ደረቅ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ዑደት ማድረግ እና ማስወገድ፡- እነዚህ ደረቅ ቆሻሻ ከተሰበሰበ በኋላ በድጋሜ ለአገልግሎት ማዋል፣ በጥሬ እቃነት ተጠቅሞ ለቀድሞ አገልግሎታቸው ወይም ለሌላ አገልግሎት ማዋልና ሙሉ በሙሉ ማስወገድን የሚመለከቱ ሂደቶች ናቸው፡፡ መልሶ መጠቀም /reuse/ ማለት ከደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ጠቃሚ እቃዎችን በማውጣት ለተሰሩበት ዓላማ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉበት አሰራር ስለመሆኑ እንዲሁም መልሶ ዑደት ማድረግ /recycle/ ማለት ደግሞ ከደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ጠቃሚ ቁሶችን በመለየትና ወደ ጥሬ እቃ በመቀየር ለቀድሞ አገልግሎታቸው ወይም ለሌላ አገልግሎት ማዋል እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2(5) እና አንቀጽ 2(6) መረዳት ይቻላል። ደረቅ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ዑደት ማድረግ እና ማስወገድ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ፣ የጤና እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ባለው መንገድ እንዲሁም ለኅብረተሰቡ ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት መከናወን እንዳለበት በአዋጅ አንቀጽ 8 ስር ተደንግጎ እናገኛለን።

ሌላው ነጥብ ቆሻሻን ማስወገድ የሚቻለው ለዚህ ዓላማ ተብሎ ከተዘጋጀ ቦታ ብቻ እንደሆነ እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻን በማቃጠል ማስወገድ እንደማይቻል በአዋጁ አንቀጽ 9 ስር ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ ሆኖም ግን በሚመለከተው ከተማ አስተዳደር ፈቃድ መሠረት ፈቃድ ባገኘ የማቃጠያ መሳሪያ እና ለዚሁ ዓላማ በተፈቀደ ቦታ እና ሁኔታ ማስወገድ እንደሚቻልም በዚሁ ድንጋጌ ስር በልዩ ሁኔታነት ተቀምጦ እናገኘዋለን።

✅ የልዩ ልዩ ደረቅ ቆሻሻዎች አያያዝ እና አወጋገድን በተመለከተ የተጣሉ ኃላፊነቶች፤
አዋጁ ከአንቀጽ 10 እስከ 15 የልዩ ልዩ ቆሻሻዎች አያያዝ እና አወጋገድ በተመለከተ የተጣሉ ኃላፊነቶችን ደንግጓል፡፡ ይኸውም፡-

✅ የመኖሪያ፣ የአገልግሎት መስጫ ወይም የማምረቻ ተቋማት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ
በአዋጁ አንቀጽ 10 መሠረት ግለሰቦች፣ የአገልግሎት መስጫ ወይም የማምረቻ ተቋማት ያለባቸውን ኃላፊነት ደንግጓል፡፡ ይኸውም፦

➥ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤት ይዞታው ድንበር አንስቶ እስከ 20/ሀያ ሜትር/ ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት፣

➥ ማንኛውም የአገልግሎት መስጫ ወይም የንግድ ተቋም ከይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 50/ሀምሳ ሜትር/ ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት እንዲሁም በየቆሻሻ ፈርጁ ተለይተው ምልክት የተደረገባቸዉ የጉድፍ ማጠራቀሚያዎችን አመቺ በሆነ ቦታ የማስቀመጥ ኃላፊነት አለበት።

✅ የግንባታና የፍርስራሽ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፤
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋራጩ (ግንባታ የሚያካሂድ አካል) የግንባታ ፍርስራሽን ወይም ተቆፍሮ የወጣ አፈርን አካባቢያዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ ማስወገድ የሚጠበቅበት ሲሆን የግንባታ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት ይንን እንደሚያደርግ መረጋገጥ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 11 ስር ሰፍሯል።
➥ ጠርሙስ፣ ጣሳ፣ የታሸገ ውኃ መያዣ ፕላስቲክ፤

የከተማ አስተዳደሮች ቆሻሻ ጠርሙስ፣ የቆርቆሮ ጣሳ ወይም ፕላስቲክ መያዣ በጊዜያዊነት የሚከማችበት ቦታ መመደቡንና ክምችቱም በየወቅቱ መነሳቱን የማረጋገጥ ግዴታ የተጣለባቸው ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 12 ያሳያል።

➥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ፤

አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ ማለት መልሶ ጥቅም ላይ የማይውል ወይም መልሶ ዑደት የማይደረግ እና አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ውሎ ቀጥታ የሚወገድ የፕላስቲክ ምርት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 2(11) ትርጉም ያሳያል።

ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ ማምረት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ መሸጥ፣ ማከማቸት ወይም መጠቀም በአዋጁ አንቀጽ 13 የተከለከለ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 14 ስር ደግሞ በልዩ ሁኔታ ስለሚፈቀድበት ሁኔታ ያስቀምጣል። የክልከላው የተፈጻሚነት ጊዜ ስንመለከትም ለአንደ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ/ፌስታል/ ክልከላ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት የተመረተ፣ ወደ አገር ውስጥ የገባ ወይም ለመግባት ሂደት ላይ ያለን የማይመለከት ሲሆን ይህ ልዩ ሁኔታ የሚቆየውም ግን አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ወር ብቻ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 13 ሥር ተደንግጎ እናገኘዋለን።

➥ ጉድፍ እና የጉድፍ ማጠራቀሚያ አያያዝና አጠቃቀም፤
ሁለም የከተማ አስተዳደሮች የጉድፍ ማጠራቀሚያ ዕቃዎችን በተገቢ ቦታዎች ላይ የማስቀመጥ እና የጉድፍ ማጠራቀሚያ ወይም በገንዳ የተጠራቀመ ቆሻሻን በተቀመጠለት ጊዜ የማንሳት ኃላፊነት የተጣለባቸው ሲሆን ማንኛውም ሰው የጉድፍ ቆሻሻዎችን በጉድፍ ማጠራቀሚያ ውስጥ የመጣል ግዴታ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 15 ሥር ተደንግጓል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምንነቱን ስንመለከት ጉድፍ /litter/ ማለት ደረቅ ቆሻሻ ሆኖ በሰዎች የሚመነጩ የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ የትራንስፖርት ደረሰኝ፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ካርድ፣ የፈጣን ምግቦች መጠቅለያ ወይም የመሳሰሉትን እንደሚያጠቃልል የአዋጁ አንቀጽ 2(4) ትርጓሜ ያሳያል።

✅ ጥሰቶች የሚያስከትሉት ተጠያቂነት፤
➥ አስተዳደራዊ እርምጃዎች፦
የአዋጁ አንቀጽ 24 አስተዳደራዊ ቅጣቶችን በሚመለከት የደነገገ ሲሆን የእርምጃው ዝርዝር ይዘት የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን (ለአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ተፈጻሚ የሚሆን) ወይም የክልል አካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት (በክልል ደረጃ ተፈጻሚ የሚሆን) በሚያወጣው መመሪያ እንደሚወሰን በድንጋጌው ተመልክቷል፡፡

➥ የወንጀል ተጠያቂነት፦
በአዋጁ አንቀጽ 25 ስር እንደተመላከተው ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ ከረጢት /plastic bag/ ወይም በተለምዶ አጠራሩ ፌስታል ከተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ ከተገኘ ከብር 2,000 (ሁለት ሺ) በማያንስና ከብር 5,000 (አምስት ሺ) በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።

በሌላ በኩል ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ ከረጢት/ፌስታል/ ካመረተ ወይም ወደ አገር ውስጥ ካስገባ፣ ለገበያ ካቀረበ ወይም ከሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ካከማቸ ወይም ይዞ ከተገኘ ከብር 50,000 (ሀምሳ ሺ) በማያንስና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 (አምስት) አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

ይኸውም የፕላስቲክ ከረጢት/ፌስታል/ ከግለሰባዊ አገልግሎት ውጪ ለንግድ ዓላማ ጥቅም ላይ ሲውል ከገንዘብ ቅጣት በተደራቢነት በእስራት እንደሚያስቀጣ መረዳት ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት ድርጊቶች የተፈፀሙት የሕግ ሰውነት በተሰጠው አካል ከሆነ ቅጣቱ ከላይ የተቀመጠውን የገንዘብ ቅጣት 3 (ሶስት) እጥፍ እንደሚሆንም በድንጋጌው ስር ተመላክቷል።

#ማጠቃለያ
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ በኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ዘላቂና አካባቢን የሚጠብቅ የቆሻሻ አያያዝ ሥርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ሕጋዊ ማዕቀፍ ነው። ይህን አዋጁ በተገቢው ሁኔታ ለማስፈጸም በዋናነት የከተማ አስተዳደሮችን የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ፣ የሕዝብ ግንዛቤን ማሳደግ እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ማሳተፍ ይጠይቃል። ኅብረተሰቡም ለአካባቢ ጽዳት ዋና ተዋናይ በመሆን ለጤናማ አካባቢ መፈጠር የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊወጣ ይገባል።

👉 በፍትህ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ!!!

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ህብረት አመራሮች ለተለያዩ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ!!‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ...
26/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ህብረት አመራሮች ለተለያዩ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ!!

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር የብልጽግና ህብረት አመራሮች፣ በከተማዋ ለሚገኙ አቅመ ደካማ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች ለበዓል የሚሆን የአስቤዛ ድጋፍ በማድረግ ደስታቸውን ተጋርተዋል።

‎ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር "አብሮነትና መረዳዳት የባህላችን መገለጫ ነው" በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በዓላትን አስመልክቶ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ያለምንም ችግር በዓሉን በደስታና በሰላም እንዲያሳልፉ ለማስቻል ነው።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ቁ 1 ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሱልጣን እማም ሁሴን በማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ማዕድ ማጋራት ልመናን ከመቅረፍ ባለፈ፣ በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ፍቅር፣ አንድነት እና የመረዳዳት እሴት ይበልጥ ያጠናክራል ብሏል።

‎ ድጋፉ ለበዓል ብቻ የሚቆም ሳይሆን፣ ወደፊትም አቅመ ደካሞችን በዘላቂነት ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።

‎የማዕድ ማጋራቱ ተጠቃሚ የሆኑት አቅመ ደካሞች በበኩላቸው፤ በአስቸጋሪ ወቅት የተደረገላቸውን ይህንን የበዓል አስቤዛ ድጋፍ ስለተደረገላቸው፣ስላስታወሷቸውና ከጎናቸው ስለቆሙ ያላቸውን ታላቅ ምስጋና እና ምርቃት ለግሰዋል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ለአረፋ በዓል አከባበር በኢድ መስገጃ ስፍራው ላይ የቅድመ ዝግጅት መርሃ-ግብር ተካሄደ።‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ለኢድ አል አድሃ በዓል አከባበር የኢድ ሰላት የ...
26/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ለአረፋ በዓል አከባበር በኢድ መስገጃ ስፍራው ላይ የቅድመ ዝግጅት መርሃ-ግብር ተካሄደ።

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ለኢድ አል አድሃ በዓል አከባበር የኢድ ሰላት የሚከናወንበትን ቦታ ዝግጅት ስራዎች ተሰርቷል ።

‎የ1447ኛው ኢድ አል-አድሃ(አረፋ) በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በነገው ዕለት የሚከበር ሲሆን፡ ይህንንም በማስመልከት በዛሬው ዕለት በከተማው በሚገኘው የኢድ መስገጃ ቦታ ላይ የቅድመ ዝግጅትና የጽዳት ስራዎች መረሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄዷል።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ የዞን እና የከተማ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የሀይማኖት መሪዎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች በጋራ በመሆን የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ላይ ተገኝቷል ።

በዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት በሚከናወኑ የእርድ ስነ-ስርዓቶች ዙሪያ ከቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት!እንደሚታወቀው በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘ...
26/05/2026

በዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት በሚከናወኑ የእርድ ስነ-ስርዓቶች ዙሪያ ከቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት!

እንደሚታወቀው በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል በነገው ዕለት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

በመሆኑም በዓሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት የእርድ ስነ-ስርዓቶች እና ሌሎችም ኩነቶች የሚስተናገዱበት በዓል እንደመሆኑ መጠን፡ ህብረተሰቡ የእርድ ተረፈ ምርቶችን ጨምሮ በበዓሉ ምክንያት በሚመነጩ ሌሎች ቆሻሻዎችም ዙሪያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴን በዛሬው ዕለት አሳስበዋል።

በተጨማሪም በዓሉን ምክንያት በማድረግም ሆነ ከበዓል ውጪ በሆኑ ወቅቶች፡ የቁም እንስሳት የእርድ ስነ-ስርዓቶች በከተማው የሚሰጡ የቄራ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዳለባቸው የጠቀሱት ዋና ስራ አስኪያጁ፡ ይህን በመተላለፍ ህገወጥ እርድ ሲያካሂዱ በተገኙ አካላት ላይ ማዘጋጃ ቤቱ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በመንግስት ደረጃ ጽዱ ከተሞችን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት፡ በበዓል ወቅት የሚፈጠሩ የእርድና ሌሎች ተረፈ-ምርቶች የከተማውን ፅዳት ከማበላሸት ባለፈ፡ በከተማው ውስጥ እየተሰሩ ለሚገኙ የልማት ተግባራት ጉድፍ የሚሆኑ በመሆናቸው ስርዓትና ደንቡን የጠበቀ የተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድ ሂደት ሊከበር እንደሚገባም ዋና ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘውም፡ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት፡ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

!!!

▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿

➥ የኦንላይን አገልግሎት የዌብሳይት አድራሻችንን፦ www.halabamun.gov.et ይጎብኙ!

➥ የቴሌግራም ቻናላችንን፦ https://t.me/halabakullitomunicipality ይቀላቀሉ!

➥ የፌስቡክ ገፃችንን፦ https://www.facebook.com/halabakullitomunicipality ይከታተሉ!

➥ የዩቲዩብ ቻናላችንን፦ https://www.youtube.com/ ሰብስክራይብ ያድርጉ!

አረንጓዴ ከተሞች!!ክፍል-1በፈጣን የከተሞች እድገት እና መስፋፋት፥ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉ መዘመን ትልቁን ድርሻ በወሰደበት በዚህ ጊዜ የአረንጓዴ ከተሞች እሳቤ ለከተሞች እድገት ዘላ...
25/05/2026

አረንጓዴ ከተሞች!!
ክፍል-1

በፈጣን የከተሞች እድገት እና መስፋፋት፥ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉ መዘመን ትልቁን ድርሻ በወሰደበት በዚህ ጊዜ የአረንጓዴ ከተሞች እሳቤ ለከተሞች እድገት ዘላቂነትና ፈተናን የመቋቋም አቅም (resilience) የሚመዘንበት አንዱና ዋነኛው መስፈርት ነው።

አረንጓዴ ከተሞች የኢኮኖሚ እድገትን ከተፈጥሮ ጥበቃ እና ከማኅበረሰብ ደኅንነት ጋር ያስማሙ ናቸው። እድገታቸውም የሥነ ምኅዳሩን ጤንነት በመጠበቅ እና የቀጣይ ትውልዶችን ሕይወት ታሳቢ ባደረገ መልኩ ነው።

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ገና በመልማት እና በመከተም ላይ ያሉ ሀገራት ደግሞ ከተሞቻቸውን በዚህ እሳቤ ለማልማት የሚቻልበት ዕድል ሰፊ ነው። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ10 ዓመት ዕቅድ ውስጥ አረንጓዴ ከተሞችን የመፍጠር ትልም አጽንኦት ተሰጥቶት ይገኛል። ይህ ትልም ኢትዮጵያ ከከተማ ልማት እና የኃይል አጠቃቀም አኳያ የምታማትርበትን የለውጥ አቅጣጫ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ከተሞቻችን ሀገራዊ የብልጽግና እና ኢኮኖሚያዊ የስበት ማዕከላት እንደመሆናቸው መጠን ለነዋሪዎችም ምቹ ፣ ውብ ፣ ንጹሕ እና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ላይ ይገኛል። አረንጓዴ ከተሞችን የማልማት አስፈላጊነት በተለይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም። ፈጣን የሆነው የሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ፣ የከተሞች መስፋፋት እና በከተሞች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር ከተሞችን በአየር ንብረት ለውጥና በአከባቢ ብክለት ምክንያት ለሚከሰቱ ችግሮች ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ለዛም ነው በአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ (Ethiopia’s Climate-Resilient Green Economy Strategy) ሰነድ ላይ ኢትዮጵያ እንደ ጎርፍ ፣ ድርቅ እና መሬት መሸርሸር ላሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች ያላትን ጉልህ ተጋላጭነት አስምሮ የሚነሳው።

ጠንካራ መሠረተ ልማት ያላቸው አረንጓዴ ከተሞች ይህን ተጋላጭነት በመከላከልና በመቀነስ ዘላቂነት ያለው ልማትን ለማረጋገጥ እድሉን ይፈጥራሉ። ከዚህም ባሻገር የአረንጓዴ ከተማ መሰረተ ልማቶች በራሳቸው የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ቱሪዝምን በማሳደግ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት በማሻሻል የኢኮኖሚ እድገትን ያነቃቃሉ። አረንጓዴ ከተሞችን የማልማት አስፈላጊነት በተለይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ነዋሪ፥ በከተማ የሚኖር፤ ነገር ግን ከተሜነት ሊሰጠው ይገባ ከነበሩት ትሩፋቶች የራቀ ሆኖ እናገኘዋለን። በዝቅተኛ ጥራትና እቅድ የተገነቡ፣ የተጨናነቁ፣ እልፍ ሲልም ለጎርፍና መሰል የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ጉድለቶች እና አየር ብክለት ከተሞችን ለዜጎች ጤናማ እና ምርታማ ህይወት አመቺ እንዳይሆኑ አድርጓቸው ቆይቷል። ስለዚህም ይህን በመቀየር አመቺ የኑሮ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊነትም አንዱ እና ዋነኛው የአረንጓዴ ከተሞች ርዕይ መገለጫ ሆኖ እናገኘዋለን።

የጽዳት፣ የአረንጓዴና የተፋሰስ ልማት፣ በግንባታ፣ ምርትና ትራንፖርት ዘርፎች ላይ የሚደረጉ የአከባቢ ብክለት ጥበቃና ቁጥጥር ማዕቀፎች በሙሉ የዚህ ርእይ እውናዊ መንበሪያዎች ናቸው። በአረንጓዴና ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክቶች ለከተሞች ሳንባ የሚሆኑ አረንጓዴ ቦታዎችን ማስፋፋት፣ ወንዞችን መታደግና የጎርፍ ተጋላጭነትን መቀነስ ተችሏል።

ከተሞች ከጥቅማዊ ፋይዳቸው ባለፈም የሥነ ውበት ዕሤትን የተጎናጸፉ፤ ለመኖር ምቹና ለእይታ ውብ እንዲሆኑ ተሠርቷል እየተሠራም ነው። በተመሳሳይ በአዲስ አበባ 69 ኪ.ሜ በሚሸፍኑ ተመጋጋቢና ገባር ወንዞች ላይ የሚተገበረው የሸገር ወንዞች ልማት ፕሮጀክት ወንዞቹን ከመጠበቅ፣ ከማጽዳትና ማልማት ባለፈ ከ1.3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በአረንጓዴ አሻራ ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለው 90% ማጽደቅ የተቻለ ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እ.አ.አ በ2018 ከነበረው 17.2% በእ.አ.አ በ2023 ወደ 23.6% አድጓል። የአዲስ አበባን የደን ሽፋን ብቻ ለይተን ብንመለከት እንኳን ከ11% ወደ 20% ደርሷል። እኚህና መሰል ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ መልክዓ ምድሮች የከተማ ልማት ዕቅድ አንድ አካል ወደሆኑበት ሥነ ምኅዳራዊ (ecological) የከተማ ንድፍ እየተደረገ ላለው ሽግግር ሕያው ማሳያዎች ናቸው።

Ministry of Urban and Infrastructure/Ethiopia

በዛላ ፍሬ ቀበሌ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የመንገድ ጥገና ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።----------------------------------ግንቦት 17/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶ ማ...
25/05/2026

በዛላ ፍሬ ቀበሌ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የመንገድ ጥገና ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።
----------------------------------
ግንቦት 17/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ዛላ ፍሬ ቀበሌ በደነቤ ፋማ ቀጠና ላይ በብልሽት ምክንያት ለእንቅስቃሴ አዳጋች ሆኖ የነበረውን መንገድ በአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች ትብብር እና በማዘጋጃ ቤቱ አማካኝነት የጥገና ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

የቀበሌው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ቅር/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሙህዲን አህመድ እንደተናገሩት፡ በሂደቱ ላይ የአካባቢው ወጣቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር ለጥገናና ለማሽነሪ ጠረጋ የሚሆኑ ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

‎ከሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወደ ደነቤ ፋማ የሚወስደውና የአካባቢው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ እንዲጠገንለት ሲጠይቅ የነበረው ይሄው መንገድ፡ በዛሬው ዕለት በአካባቢው ንቁ ወጣቶች አስተባባሪነት፣ የሰሌክት አፈርና ሌሎችንም ተያያዥ ወጪዎች በራሳቸው በመሸፈን የጥገና ሥራው በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

‎ወጣቶች የልማት አጋርነታቸውንና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በተግባር ያሳዩበት ይህ የጥገና ሥራ፤ የአካባቢውን የትራፊክና የህዝብ እንቅስቃሴ በእጅጉ እንደሚያቃልል ይታመናል።

▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿

➥ የኦንላይን አገልግሎት የዌብሳይት አድራሻችንን፦ www.halabamun.gov.et ይጎብኙ!

➥ የቴሌግራም ቻናላችንን፦ https://t.me/halabakullitomunicipality ይቀላቀሉ!

➥ የፌስቡክ ገፃችንን፦ https://www.facebook.com/halabakullitomunicipality ይከታተሉ!

➥ የዩቲዩብ ቻናላችንን፦ https://www.youtube.com/ ሰብስክራይብ ያድርጉ!

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች የደም ልገሳና የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች “የእግር ኳስ ፍቅር ለሰብአዊነት” በሚል ሃሳብ በዛሬው ...
24/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች የደም ልገሳና የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች “የእግር ኳስ ፍቅር ለሰብአዊነት” በሚል ሃሳብ በዛሬው ዕለት የደም ልገሳና የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

የእግር ኳስ እውነተኛ ውበትና አቅም ከደጋፊነት ስሜት በላይ ወጥቶ ለወገን ደራሽ መሆን መቻሉን የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች በተግባር አሳይተዋል።

መድፈኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እጅግ አስደናቂና አስደሳች በሆነ ሁኔታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን ተከትሎ ደስታቸውን በጭፈራ ብቻ ሳይሆን የሰውን ህይወት በሚታደግ በጎ ተግባር አክብረውታል።

የሻምፒዮናነቱ ድል እና በጎ አድራጎቱ በሀላባ ሴራ አደራሽ የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች የዓመቱን የመጨረሻ ጨዋታ በጋራ ለመታደም እና የዋንጫ ድላቸውን ለማክበር በሀላባ ሴራ አደራሽ በታላቅ ድምቀት ተሰባስበው ደም ልገሳ አድርገዋል።

ስፖርት በፍቅርና በስነ-ስርዓት ከተያዘ አንድነትን ለማጠናከር፣ የሰውን ህይወት ለመታደግ ብሎም ለሀገር ግንባታና ለልማት ትልቅ አቅም መፍጠር እንደሚችል ደጋፊዎቹ በተግባር አስመስክረዋል።

ደጋፊዎቹ ከዚህ በጎነት ተግባር በተጨማሪ የጽዳትም ዘመቻም አካሄደዋል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share