የሀላባ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት-Halaba Zone Disaster Risk Management Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት-Halaba Zone Disaster Risk Management Office

የሀላባ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት-Halaba Zone Disaster Risk Management Office 𝑚𝑎𝑛𝑎𝑔𝑒 𝑎𝑛𝑑 𝑚𝑖𝑛𝑖𝑚𝑖𝑧𝑒 𝑛𝑎𝑡𝑢𝑟𝑎𝑙 𝑎𝑛𝑑 𝑚𝑎𝑛 𝑚𝑎𝑑𝑒 𝑑𝑖𝑠𝑎𝑠𝑡𝑒𝑟𝑠 𝑎𝑛𝑑 𝑟𝑖𝑠𝑘𝑠 𝑎𝑠 𝑚𝑢𝑐ℎ 𝑎𝑠 𝑝𝑜𝑠𝑠𝑖𝑏𝑙𝑒.

16/05/2026

የ2026 የክረምት ወቅት የዝናብ ትንበያና የቅድመ ዝግጅት ምክሮች

በቀጣይ የክረምት ወቅት የሚጠበቀው የዝናብ ሁኔታ በተለይም በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምሥራቅ እና በአንዳንድ መካከለኛ የሀገራችን ክፍሎች ከመደበኛ በታች የማግኘት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን ግምቶች ያመለክታሉ።

ይህም ማለት በቀጣይ ወራት የሚጠበቀው ዝናብ አስተማማኝና በቂ ላይሆን እንደሚችል ያሳያል። በመሆኑም ከወዲሁ የተቀናጀ የውሃና የግብርና ስራ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
የሚመከሩ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎች

1) በግድቦች፣ በኩሬዎች እና በውሃ ማከማቻ ሥርዓቶች ያለውን ውሃ በአግባቡ መያዝና በቁጠባ መጠቀም።

2) መጠነኛ ዝናብ የሚገኝበት ጊዜ የምርት ጉዳትን ለመቀነስ የድርቅ የሚቋቋሙ ሰብሎች፣ አትክልቶችና ፍራፍሬዎችን ለመዝራትና ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ።

3)የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን ማጠናከር።

4)የአየር ሁኔታ መረጃዎችን በቅርብ መከታተልና በሁኔታው መሰረት የእርሻ እቅዶችን ማስተካከል።

በአጠቃላይ፣ የቀጣይ የክረምት ወቅት የዝናብ ሁኔታ ጥንቃቄና ቅድመ ዝግጅት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም የተጠቃሚ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ ከወዲሁ ዝግጅታቸውን ማጠናከር ያስፈልጋል ።

12/05/2026
06/05/2026
የለውጥ ፍሬዎች በሀላባ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ፦ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት! የሀላባ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽሕፈት ቤት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የአሰራርና የአመለካከት...
06/05/2026

የለውጥ ፍሬዎች በሀላባ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ፦ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት!

የሀላባ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽሕፈት ቤት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የአሰራርና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት ማህበረሰባችንን ከእጅ ወደ አፍ ህይወትና ከተረጂነት ስነ-ልቦና በማውጣት ወደ ምርታማነት የሚያሸጋግሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ጽሕፈት ቤታችን ባለፉት የለዉጥ ዓመታት "አደጋን ወደ ጸጋ" በመቀየር ረገድ ያስመዘገባቸው ዋና ዋና ድሎች የሚከተሉት ናቸው፦
 የአመለካከት ለውጥና ከተረጂነት መውጣት፦ ባለፈው የለውጥ ዓመት አርሶ አደሩ የነበረበትን "ተረጂነት" አመለካከት በመቀየር ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅሞ ወደ "ምርታማነት" እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡ እስከ ዛሬ ተረጂ ሆኖ መቆየቱ "ቁጭት" ውስጥ የከተተው አርሶ አደራችን ፣ ዛሬ በራሱ ጥረት ምርታማ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
 አደጋን ወደ ጸጋ መቀየር፦ ከዚህ ቀደም አደጋ ሲደርስ ምላሽ መስጠት ላይ ብቻ ያተኮረውን አሰራር በመቀየር አደጋ ከመድረሱ በፊት በመከላከልና በመቀነስ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የነበሩ እንደ ሲንቢጣ ፣ በንዶ ፤ ጮባሬ ሜዕኖ እና ኡዳና ሜዕኖ ያሉ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋን ወደ ጸጋ በመቀየር ከ20 ዓመት በላይ የቆየውን ተረጂነት መስበር ችለዋል፡፡
 የራስን አቅም መገንባትና የሰብዓዊ ድጋፍ ክምችት፦ ባለፉት የለዉጥ ዓመት የሰብዓዊ ድጋፍን ከፌዴራልና ከክልል ከመጠበቅ ወጥተን በዞኑ መንግስት በውል መሬቶች ላይ በማምረትና የማህበረሰቡን የመረዳዳት ባህል በመጠቀም ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ ከ11,000 ኩንታል በላይ እህል በማከማቸት በራስ አቅም ምላሽ የመስጠት አቅም ተፈጥሯል፡፡
 የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ከሴፍትኔት መመረቅ፦
 በተደረገላቸው የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ድጋፍና በተለያዩ የግብርና ኢንሼቲቮች አማካኝነት 6,376 አባወራዎች (26,051 የቤተሰብ አባላት) ከሴፍትኔት ፕሮግራም መመረቅ ችለዋል፡፡
 የሰብዓዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ከነበሩ 49,132 ቤተሰቦች መካከል 39,079 የሚሆኑት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ተቀይረዋል፡፡
 በቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ለ4,481 አባወራዎች በ149.2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በዚህም ለድለባ ፣ ለማሞከትና ለወተት እርባታ 7,078 እንስሳት ቀርበው የቤተሰብ ገቢ ማሻሻል ተችሏል፡፡
 በቁጠባ ሀብት ማፍራት፦ ባለፉት 2 ዓመት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በቋሚነት እንዲቆጥቡ በማድረግና የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ ለቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ የሚሆን መነሻ 125,000,000 ብር ካፒታል በመቆጠብ በመረጡት የስራ መስክ በመሰማራት "የቤተሰብ ጥሪት" እንዲያፈሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ቁጠባ ተጠቃሚዎች ከእርዳታ ጥገኛነት እንዲላቀቁ ትልቅ አቅም ሆኗቸዋል፡፡
 የቴክኖሎጂና የውሃ አማራጮች አጠቃቀም፦በዌራ ዲጆ ወረዳ 190 አባወራዎች በ7.6 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የሶላርና የዴዝል ፓምፖችን እንዲያገኙ ተደርጎ በ41.5 ሄክታር መሬት ላይ የጓሮ አትክልትና የበልግ ሰብሎችን በማልማት ኑሮአቸውን ማሻሻል ችለዋል፡፡
ጽሕፈት ቤታችን ይህንኑ ስኬት አጠናክሮ በመቀጠል አደጋዎችን መቋቋም የሚችልና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
"አደጋን በመከላከል ምርታማነትን እናረጋግጣለን!"
#ኢትዮጵያ

የሀዘን መግለጫየስራ ባልደረባችን የአቶ ሙሊዬ ተፈሰ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።አቶ ሙሊዬ በስራ ገበታቸው ትጉህና ውጤታማ ከመሆናቸውም በላይ፣ በባህሪያቸው ትሁት፣ ሰ...
03/05/2026

የሀዘን መግለጫ
የስራ ባልደረባችን የአቶ ሙሊዬ ተፈሰ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።
አቶ ሙሊዬ በስራ ገበታቸው ትጉህና ውጤታማ ከመሆናቸውም በላይ፣ በባህሪያቸው ትሁት፣ ሰው አክባሪ እና ለሁላችንም እንደ አባት የሚመክሩ ታላቅ ሰው ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!
የሀላባ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት

03/05/2026

እ.ኤ.አ ከሜይ 1 እስከ 10/2026 (ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 2/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
/////////
በሚቀጥሉት ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። በመሆኑም ከሚጠበቀው የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳብ ከወዲሁ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

21/04/2026

Address

Alaba K'ulito
046556

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:28 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት-Halaba Zone Disaster Risk Management Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share