Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ

Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ This is the official Halaba Zone Peace And Security Department page.

Detail contact information to follow us:
https://halaba.gov.et
ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የተቋቋመዉ ግጭትን በመከላከልና በመፍታት፤ በሀይማኖትና እምነቶች መካከል ዘላቂ መቻቻልና የመከባበር እሴት በማጎልበት እና ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግስቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ነዉ።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ገለጸሆሳዕና 25/09/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥ...
02/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ

ሆሳዕና 25/09/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለጹ።

ምርጫው መጠናቀቁን ተከትሎም ቢሮው መግለጫ ሰጥቷል።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዜጎች በሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ ያላቸውን የላቀ ተሳትፎ ያሳዩበት ዕለት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተመስገን ካሳ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደው ድምፅ የመስጠት ሂደት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ከምርጫው አስቀድሞ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች የምርጫ ሂደቱ የተረጋጋ እና ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ኃላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከምርጫ በኋላ (በድህረ-ምርጫ) ሊኖሩ ስለሚገባቸው የፀጥታ ሥራዎች ጭምር ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል።

በምርጫው ወቅት ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ኅብረተሰቡን ከማስተማር ጀምሮ፣ በየአካባቢው ሰላምን ለማስከበር የተመደቡ የፀጥታ አካላት በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ ምን ዓይነት ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ሥልጠና መሰጠቱንም አቶ ተመስገን ጠቁመዋል።

ግንቦት 24 ቀን በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በክልሉ ሥር ባሉ የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች የነበረው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሰላማዊና የኅብረተሰቡ ጉልህ ተሳትፎ የታየበት እንደነበር ተገልጿል።

በምሽቱ መርሃ ግብር የተከናወነው የድምፅ ቆጠራ ሂደትም ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ግን እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል።

በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ወቅት የታየው የኅብረተሰቡ ከፍተኛ እገዛና ተሳትፎ፣ በቀጣይም የምርጫ ውጤት በሚገለጽበት ወቅት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው በመጨረሻም፣ በቅድመ-ምርጫና በምርጫው ዕለት አጠቃላይ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱና ከተቋሙ ጋር ለተባበሩ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ******ግንቦት 25/2018) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን  የሰባተኛው ጠቅላ...
02/06/2026

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
******
ግንቦት 25/2018) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም ተጠናቋል ብለዋል።

በክልሉ እስከ ታችኛው መዋቅር የጸጥታ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መገባቱን ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ማህበረሰቡን በጸጥታ ስራ ማሳተፍ አብይ አጀንዳ እንደነበር ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ይህም አስቀድሞ ወንጀልን በመከላከል ረገድ የላቀ አበርክቶ ነበረው ሲሉም ጠቁመዋል።

ወጣቶችን፣ሴቶችን፣የሀይማኖት አባቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ውይይት ማካሔድ በመቻሉ የወንጀል መከላከል ስራው ስኬታማ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ የገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት እና የጸጠሰታ ምክር ቤት ማጠናከር ተጠቃሽ መሆኑን ኮሚሽነር ሽመልስ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን በማቅረብ እና ምርመራ በማካሔድ ህግ የማስከበር ስራ ማከናወን ስለመቻሉም ተናግረዋል።

የክልሉ አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በየጊዜው እየተገመገመ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ በዚህም አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም በመገንባት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።

ከምርጫ በፊት የጸጥታ ሀይሉን የማጠናከር ስራ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው የጠቆሙት ኮሚሽነሩ በዘርፉ ተጨማሪ የሰው ሀይል በማሰልጠን ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዋል።

የጸጥታ ሀይሉን በምርጫ ስነ ምግባር ላይ አስቀድሞ ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ 35 የምርጫ ክልሎች እና 2ሺ 998 የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አውስተዋል።

በክልሉ በሁሉም የየምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ ሀይል በመመደብ ወደ ተግባር መግባት መቻሉን የገለጹት ኮሚሽነር ሽመልስ ተጨማሪ እገዛ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የክልሉ አድማ ብተና ፖሊስ፣የፌደራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ባላት ስምሪት ወስደው ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበርም አብራርተዋል።

በምርጫ በሂደቱ ያጋጠሙ ቀላል ጉዳዮች ከምርጫ አስተባባሪዎች ጋር በመነጋገር መፍታት መቻሉን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል ።

በክልሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያጋጠመ የጸጥታ ችግር አለመኖሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በዚህም ህብረተሰቡ በነጻነት ድምጽ በመስጠት ወደ መደበኛ ስራው መሰማራቱን በመግለጫቸው አብራርተዋል።

አብዛኛው የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ክልል የማጓጓዝ ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ፣ፖሊስ፣የድማ ብተና ኃይል፣ቪአይፒና ተቋማት ጥበቃ ሻለቃ፣ማረሚያ ቤቶች፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ፣የሚሊሻ አባላት፣የክልል፣የዞን ፣የልዩ ወረዳ፣የወረዳ፣የከተማ አስተዳደር እስከ ቀበሌ ያለው አመራር ለጸጥታ ስራው የላቀ ድጋፍ በማድረጋቸው ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል። ስል የዘገበው የክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

ሀገሪቱ የጀመረችውን የልማት የዕድገት ስራዎችን ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥ...
31/05/2026

ሀገሪቱ የጀመረችውን የልማት የዕድገት ስራዎችን ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ተጠየቀ።

ሆሳዕና :- ግንቦት 23/2018 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአጠቃላይ የፀጥታ ስራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት መግለጫ ክልሉ በሰባት ዞኖችና በሶስት ልዩ ወረዳዎች የተደራጀ ሲሆን አዲስ ክልል እንደመሆኑ የምርጫ ሁነትን ሲያስተናገድ የመጀመሪያው መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በቅድመ ምርጫ ወቅት በርካታ የፀጥታ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

በየደረጃው የፀጥታ ግብረ ሃይል በማቋቋም እና ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

በየአካባቢው ወንጀልን በመከላከልና አጥፊውን በማጋለጥ ሂደት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን መቆም እንዲችልና ምርጫው በሰላምና በስኬት እንዲካሄድ በሁሉም አካባቢዎች በጸጥታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉንም ም/ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን አጥፊዎችን የመያዝና ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመሆን ወንጀልን በምርመራ የማጣራትና በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም በመግለጫቸው አክለዋል።

ይህ ሁሉ ስራ ሲሰራ መላው የፀጥታ ኃይል በጋራ እና በቅንጀት በመስራታቸው እንዲሁም አጠቃላይ የፀጥታ ስራዎችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በጋራ በመገምገም አቅጣጫ እየሰጡ በመሄዳቸው በቅድመ ምርጫ ወቅት በተሰሩ የጸጥታ ስራዎች በክልሉ የተሻለ ሰላም መኖሩንም አስረድተዋል።

በክልሉ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸው 35 ምርጫ ክልሎችና 2ሺ 9መቶ98 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በሁሉም ቦታዎች የጸጥታ ኃይል ተሰማርቶ ስራላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከስምሪት በፊት በቂ የምርጫ ስነምግባር ስልጠና በመስጠት የጸጥታ ኃይሉ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ መደረጉንም ም/ ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ገልጸዋል።

ለስኬቱ የፌዴራል ፖሊስና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ድጋፍ እያደረጉ መቆየታቸውን ገልጸው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።

ሀገር የጀመረችውን የልማት የዕድገትና የቴክኖሎጂ ስራዎች ህልውናዋ ተጠብቆ ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማስቀጠል ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

እንዲሁም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ታዛቢዎች ምርጫ አስፈጻሚዎች እና በምርጫው ስራ ላይ የተሰማሩ ሁሉም አካላት የምርጫ ስነምግባር ደንብ በመከተል የምርጫ ስራውን በመስራት ለስኬት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ችግሮች ሲከሰቱም ወዲያው ለፀጥታ ኃይል ማሳወቅ እንደሚገባ ም/ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ከአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ጋር ተወያዩ***********************በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢጋድ (IGAD) የምር...
31/05/2026

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ከአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ጋር ተወያዩ
***********************

በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ከሆኑት ከኡሁሩ ኬንያታ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

የሁለቱ ታዛቢ ቡድኖች መሪዎች ባደረጉት በዚህ ውይይት፣ ከምርጫው በፊት የታዘቧቸውን ምልከታዎች የተለዋወጡ ሲሆን፣ የታዛቢዎችን ስምሪት ዕቅድ በተመለከተም መክረዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ ተዓማኒ፣ ግልጽና ሁሉንም ያካተተ የምርጫ ሂደት እንዲኖር ለመደገፍ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ እና ኡሁሩ ኬንያታ በውይይቱ ወቅት በየራሳቸው የሥራ ቡድኖች መካከል ስለሚኖረው የማስተባበሪያ ሥርዓት ተነጋግረዋል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ አበባ ከተማ ይፋ የሚደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ሪፖርት የሚያወጡበትን የጊዜ ሰሌዳም አመቻችተዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላአዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ...
30/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ለፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለምርጫው ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ቢሆንም መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች እነዚህን የጥፋት ዕቅዶች ማክሸፉን አረጋግጠዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው÷ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከምርጫ ቦርድ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥና ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በቅድመ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ደህንነት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አንስተዋል።

FBC

እንኳን ለ1447ኛው ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የሰላም ሚኒስቴር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት...
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የሰላም ሚኒስቴር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት እንዲሆን ይመኛል።

ዒድ አል-አድሃ ሙባረክ!

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አባለት ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቆመ ።ግንቦት 18/2018 የፀጥታ አካላት በመቀናጀትና በመናበብ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እ...
26/05/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አባለት ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቆመ ።

ግንቦት 18/2018 የፀጥታ አካላት በመቀናጀትና በመናበብ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁመዋል ።

መድረኩን የዌራ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ በህረዲን ኬዳ እና የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና አዛዥ ረ/እንስፔክተር ናስር አወል ጋር በጋራ መርተዋል ።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም የማጠናቀቅ ጉዳይ የሁሉም ፀጥታ አካላት ኃላፊነት መሆኑን የተናገሩት አቶ በህረዲን ወቅቱ የፀጥታ ተቋማት በቅንጅት ፣ ተናበው እና ተባብሮ የሚሰሩበት ጊዜ መሆኑን በማንሳት የሀገር ደህንነት ለማስጠበቅ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በውይይታቸው "ሰላምን ለማቆየት በሰራነውና በምንሰራው ስራ ይወሰናል ያሉት አቶ በህራዲን ለዚህም በተለይም የፖሊስ መዋቅሩ የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ያለውን ጥረት ያለመዘናጋት ሀላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል።

ዋና አዛዥ ረ/እንስፔክተር ናስር አወል በበኩላቸው ምርጫው ፍፁም ሠላማዊ፣ ፍትሃዊና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የፀጥታ መዋቅሮች ትልቅ ኃላፊነት ያለበት ወቅት መሆኑን ገልፀው ንቁና ብቁ ሆኖ መዘጋጀት የአከባቢውን ደህንነት መጠበቅ ከእያንዳንዱ ፖሊስ አካላት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

አክለውም የፀጥታ አካላት በተሰማሩበት የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በጥንቃቄ መሥራትና ለስኬታማነቱም በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም ገልፀዋል።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ምሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድራህማን ኢብራሂም ፣የዌራ ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት የፖሊስ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል ።

የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል _ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ሆሳዕና  ግንቦት 17  ቀን 2018 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ...
25/05/2026

የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል _ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

ሆሳዕና ግንቦት 17 ቀን 2018 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በተገኙበት ሰባተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ የምርጫ ሂደት ሠላማዊ በማድረግ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል ።

በመድረኩ ፣የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ከማድረግ አኳያ የእሰከ አሁኑን አዝማሚያ የሚያመላክት አጭር ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተካሂዷል፤ ቀጣይ ትኩረቶችም ተመላክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመድረኩ እንደገለፁት ፣የቅድመ _ምርጫ፣ የምርጫና የድህረ_ ምረጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የምርጫ ሂደት ሠላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ፣ ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ በተደራጀና በተናበበ መንገድ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።

በውይይት መድረኩ፣ የየአካባቢውን ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ አዝማሚያዎች የዳሰሰ ዉይይት ከመደረጉ ባሻገር፣ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት በመፍጠር ተጠናቅቋል ።

በዉይይት መድረኩ፣ብርጌደር ጄኔራል ተመስገን መሎሬ:- በመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ዋና መምሪያ መረጃና ማስረጃ መምሪያ ሀላፊና የክልሉ ጸጥታ ግብረ ሀይል ሰብሳቢ ፣ አቶ ተመስገን ካሳ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ፣ የከልል፣የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ሠላምና ፀጥታ መዋቅር አመራሮች ፣የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ፖሊስ አዛዦች ፣ የክልል፣ የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች የሚልሻ ጽህፈት ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የዘገበዉ የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነዉ። ።

# #ሰላም!!

በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ሚ...
25/05/2026

በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ሚና ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ።

የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ፣ፖሊስና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን ከፖሊስ አባላትና ከጸጥታ ከሚሊሻ ባለሙያዎች ጋር በሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የውይይት መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙስጠፋ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረብዩ መሐመድ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ሳጅን ሳብቱ አሊ በጋራ መርተውታል።

በዚህም ወቅት የጸጥታ አካላት በሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል አከባበር ዙሪያ ትኩረት በመስጠት መርሃግብሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ልተገብሩ እንደሚገባ ተገልጿል።

ግንቦት 17/2018 በሸኖ፣(ዌራ ዲጆ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን)

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸርፉ ሼክቻ የሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላምና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅና በልዩ ትኩረት ለመጠበቅ ከሀላባ ቁሊ...
24/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸርፉ ሼክቻ የሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላምና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅና በልዩ ትኩረት ለመጠበቅ ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር ውይይት አደረገ
==========

ግንቦት 16/2018 የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸርፉ ሼክቻ በግንቦት 24 ለሚካሄደው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫና የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን የኢደል አድሃ አረፋ በዓልን በሰላም እንዲጠነቀቁ ለማድረግ ከሀላበ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።

የፀጥታ ተቋማት የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና እንደሌላቸው የገለጹት አቶ ሸርፉ ሽክቻ የፀጥታ ተቋማት ያንን በውል በመገንዘብ ፀጥታውን የማስከበር ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፊታችን ረቡዕ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የኢድ አልሀዳ (የአረፋ) በዓል በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የፀጥታ ተቋማት የጋራ ቅንጅት ተግባርና አስፈላጊ የሆነ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቆ እንደሚጠብቅ ገልጸዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ም/እ /ር ሹክራለ ሱጋቶ በበኩላቸው የፀጥታ ተቋማት ገለልተኛነት እንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ በሀገራቸው ጉዳይ የመወሰንና የመምረጥ መብት እንዳላቸው ገልፀው ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ሆነው መወዳደር እንደማይችሉም ገልፀዋል።

የፖሊስ አባላቶቻችን ከወትሮው በተለያ መልኩ በዚህ በሀገራዊ ጉዳይ በተጠንቀቅ ንቁ ሆነው በመጠባበቅ የከተማውን እና የመላው ህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ መዘጋጀት ይገባቸዋል ስሉ አሳስበዋል።

በተጨማሪም እያንዳንዱ አባላቶቻችን ነቅቶ በመጠበቅ የሚሰጣቸውን ስምሪትና ተልዕኮ እንደ ከዚህ ቀደሙ በሚገባ መከናወን እንዳለባቸውም አንስተዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የጸጥታ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ምርጫውንና የኢድ አል አድሃ በዓሉ በሰላም ተጀምረው እስኪጠናቀቁ በቅንጅት እንደሚሰሩ በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።

!!

ዘገባው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት !!

Address

Halaba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share