በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት, Political organisation, atoti ulo Guba, Alaba K'ulito.

ይህ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ይፋዊ የፌስቡክ የሚዲያ ገፅ ስሆን አጠቃላይ ወቅታዊና መደበኛ የፓርቲ ስራዎች ዘወትር ይተላለፋል።
👇ከታች ያለውን Follow በታን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069137263054

 እርስዎስ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በድምፅዎ መሪዎን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል?
27/05/2026



እርስዎስ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በድምፅዎ መሪዎን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል?

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል።
27/05/2026

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል።

የ1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በዒድ መስገጃ ቦታ በድምቀት ተከበረ! Halaba Tv
27/05/2026

የ1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በዒድ መስገጃ ቦታ በድምቀት ተከበረ!
Halaba Tv

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በዒድ መስገጃ ቦታ  በተክቢራ፣ በዒድ ሶላትና በዒድ መልዕክቶች በድምቀ...
27/05/2026

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በዒድ መስገጃ ቦታ በተክቢራ፣ በዒድ ሶላትና በዒድ መልዕክቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

➡ ብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ እሳቤዎችን በማንገብ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የገባውን ቃል ኪዳን አልቆ የፈጸመ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉም ህዝብ ቃሉን በተግባር የመተርጎም ልምድ ያለውን ፓርቲያችንን በመም...
26/05/2026

➡ ብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ እሳቤዎችን በማንገብ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የገባውን ቃል ኪዳን አልቆ የፈጸመ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉም ህዝብ ቃሉን በተግባር የመተርጎም ልምድ ያለውን ፓርቲያችንን በመምረጥ የሀገራችንን ሁሉን አቀፍ የለውጥ ጉዞ እንዲያስቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ!!።

አቶ መሐመድከማል ኑርዬ፦የሀላባ ዞን ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ!!
● ፓርቲያችን፦ብልፅግና!!
● ምልክታችን!፦የስንዴ ነዶ!!
● መልዕክታችን፦ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
➡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ዕለተ ሰኞ በነቂስ በመዉጣት ብልጽግና ፓርቲ ይምረጡ!!

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል !!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ክላስተር የሴቶች ክንፍ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም አካሄዱ!!!የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሀላባ ክላስተር የሴቶች ...
26/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ክላስተር የሴቶች ክንፍ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም አካሄዱ!!!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሀላባ ክላስተር የሴቶች ክንፍ 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት በሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የዕለቱን መርሃ-ግብር በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ በይዳ ሙንዲኖ እንደገለጹት የለውጡ መንግስት ሴቶችን በሁሉም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተዓማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ወ/ሮ በይዳ ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታና ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር እያደረገ ያለውን ጉዞ በመደገፍ የተጠናከረችና የበለጸገች ሀገርን ለማስቀጠል የክላስተሩ ሴቶች የተጣለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዕለቱ ለሴቶች ክንፍ አባላት የተዘጋጀውን ሰነድ የክላስተሩ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጥሩነሽ አንሸቦ በዝርዝር አቅርበዋል።
የከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው፣

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለ1ሺ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል...
26/05/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለ1ሺ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ለ1ሺ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፣ እንኳን ለ1 ሺ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

ዒድ አል-አድሃ ሙባረክ!

በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት ከሚከበሩት በዓላት መካከል አንዱ የሆነዉ ፣የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮቶቹ ባሻገር፣ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዲነቃቁ፣ የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶችና ትዉፊቶች እንዲጠናከሩ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል፤ ተካፍሎ የመብላትን ፣ለተቸገሩ የመድረስን፣ የሌሎችን ችግር ለማቃለል የመነሳሳት ሥነ ልቦናን ከፍ ያደርጋል።

በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች፣በተለያዩ የሕይወት መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ የክልላችን ተወላጆች፣ ወላጆቻቸውን፣ ቤተዘመዶቻቸውን የሚጠይቁበት፣ የሐሴትና የፍቅር መንፈስ የሚጎላበት፣ ልጆች በወላጆቻቸው ምርቃት በረከትን የሚላበሱበት፣ ተስፋቸውም የሚለመልምበት ነው _የዓረፋ በዓል።

ይህን የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴት ሕዝበ ሙስሊሙ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

የዘንድሮው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል እየተከበረ የሚገኘው፣ ሀገራችን _ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ እያከናወነች በምትገኝበት እና ለድምፅ መስጫው ዕለትም በጣት የሚቆጠሩ ቀናት በቀሩበት ዋዜማ ላይ ነው።
ስለሆነም መላው ሕዝበ ሙስሊም እና መላው የክልላችን ሕዝቦች ፣ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን ከመወጣት ባሻገር፣ በድምፅ መስጫው ዕለት ማልዳችሁ ድምፅ ለመስጠት ከወዲሁ እንድትዘጋጁ ጥሪ አቀርባለሁ !

መልካም የዒድ አል-አድሃ ( ዓረፋ ) በዓል!
አመሠግናለሁ !

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በፓርቲያችን መሪነት የወጣቱን ስራ አጥነትን በመቀነስና የስራ እድል በመፍጠር ተጠቀሚነቱ ለማረጋገጥ በልዩ ትኩራት እየተሰራ ይገኛል።=======(ግንቦት፣18/2...
26/05/2026

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በፓርቲያችን መሪነት የወጣቱን ስራ አጥነትን በመቀነስና የስራ እድል በመፍጠር ተጠቀሚነቱ ለማረጋገጥ በልዩ ትኩራት እየተሰራ ይገኛል።
=======
(ግንቦት፣18/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ

በወረዳው የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ የስራ አጥነትን በመቀነስ ሁለንተናዊ የወጠቱ ተጠቃሚነት በኢኮኖሚና በመህበራዊ በማረጋገጥ የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ለመፋጠን በሁሉም ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም በዛሬዉ ዕለት በግብርና ዘርፉ "ለአንድመህበር"በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በጉባ ከተማ የኢንተርፕራይዝ መህበር የገቼኖ ብልፅግና መህበር ለተደራጁ ለስራ አጥ ወጠቶች የእንቁለል ዶሮ ግዥ ተፈፁሟል ።

በግብርና ዘርፉ ለተደራጁ ለስራ አጥ ወጠቶች በጉባ ከተማ ለተደረጁ መህበራት ከኦሞ በንክ የነቀታ ቅርንጨፍ ጋር በመሆን 400000 ብር( አራት መቶ ሺ ብር) ግዥ በመድረግ
በቋም ስራ ዕድል ለ10 አባለት መፍጠር ሲሉ የወረዳው ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከድር ሪባቶ ገልጸዋል

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

➡ ለኢትዮጵያ ከፍታ፣ለሁለንተናዊ ብልጽግና፦የስንዴ ነዶን ይምረጡ!!=====================================ሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ ተስፋ እና በታላቅ የለውጥ ምዕራፍ ላይ...
26/05/2026

➡ ለኢትዮጵያ ከፍታ፣ለሁለንተናዊ ብልጽግና፦የስንዴ ነዶን ይምረጡ!!
=====================================
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ ተስፋ እና በታላቅ የለውጥ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።ይህ ጉዞ የዳር ቆሞ ተመልካች ሳይሆን፣የሁሉም ዜጎች ንቁ ተሳትፎና የጋራ ጥረት ውጤት ነው።በፊታችን ባለው ምርጫ የምናደርገው ውሳኔ የነገዋን ኢትዮጵያ መልክ የሚወስን፣የልጆቻችንን የወደፊት ዕጣ-ፈንታ የሚያፀና ይሆናል።

የስንዴ ነዶ የብልፅግና ፓርቲ ምልክት ብቻ አይደለም፤ የድካማችን ውጤት፣የላባችን ፍሬ እና የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተምሳሌት ነው።በትላንትናው ታሪካችን ስንዴ የልመናና የርዳታ ምልክት ነበረ።

ዛሬ ግን በመደመር እሳቤ፣ በቆላ ስንዴ ልማትና በክረምት መስኖ ኢትዮጵያን በስንዴ ምርት ራሷን እንድትችል አልፎም ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ አድርገናል።

የመደመር እሳቤ መሰረቱ ካለፈው መልካሙን ወርሶ፣ የጎደለውን ሞልቶና ስህተትን አርሞ ለጋራ ከፍታ መትጋት ነው።እንደ ስንዴ ዘሮች በተለያዩ አካባቢዎች ብንበቅልም፣ በአንድ ነዶ ታስረን ለሀገር በረከት እንሆናለን።በመደመር ውስጥ ማንም አይገለልም፤ የገጠር አርሶ አደር፣ የከተማው ሰራተኛ፣ምሁሩና ወጣቱ በአንድነት ለኢትዮጵያ ብልፅግና ይሰለፋሉ።

ፊታችን ባለው ምርጫ"የስንዴ ነዶን"መምረጥ ማለት በኢኮኖሚ የጠነከረች፣በማህበራዊ ኑሮ የተደላደለችና በፖለቲካ የሰለጠነች ሀገርን ለመገንባት ፣ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ፣ በወሬ ሳይሆን በገሃድ በሚታይ ልማት፣ በታላላቅ ፕሮጀክቶችና በስንዴ ማሳዎች የተረጋገጠ ውጤትን ማስቀጠል ማለት ነው።

በምርጫ ካርዳችሁ ላይ የብልፅግና ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ፣የኢትዮጵያን ትንሳኤ በጋራ እናረጋግጥ ነው።

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ፣

Address

Atoti Ulo Guba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት:

Share