በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ይህ የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነዉ follow በማድረግ መረጃዎችን ያግኙ!!

የዓለም ሀገራት ምርጫን ለምን ያካሂዳሉ ? =====ግንቦት 22/2018 ምርጫ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ዋና መሣሪያ ነው። ምርጫ ለአንድ ሀገር የ...
30/05/2026

የዓለም ሀገራት ምርጫን ለምን ያካሂዳሉ ?
=====

ግንቦት 22/2018 ምርጫ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ዋና መሣሪያ ነው።

ምርጫ ለአንድ ሀገር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ዕድገት በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡

ከእነዚህ መካከል፡-

1. የሕዝብ ውክልናን ማረጋገጥ

ምርጫ ዜጎች ፍላጎታቸውን፣ እምነታቸውንና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁላቸውን መሪዎችና ተወካዮች በነፃነት እንዲመርጡ ዕድል ይሰጣል። በዚህም የተመረጡ አካላት የሕዝብ እውነተኛ ተወካይ ሆነው እንዲሠሩ ያደርጋል።

2. ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር መፍጠር

ሥልጣንን በኃይል ወይም በግርግር ከመያዝ ይልቅ፣ በሕዝብ ድምፅና በሰላማዊ መንገድ ከአንድ መሪ ወይም ፓርቲ ወደ ሌላው ለማስተላለፍ ምርጫ ብቸኛውና አስተማማኙ መንገድ ነው።

ይህ ለአገር መረጋጋትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው።

3. ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን ማስፈን

የተመረጡ መሪዎች ለሰጡት ተስፋና ለሚያከናውኑት ሥራ ለሕዝብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጋል።

ሕዝብን በታማኝነት ካላገለገሉ በሚቀጥለው ምርጫ በድምፅ ሊወርዱ እንደሚችሉ ስለሚያውቁ፣ ሥራቸውን በኃላፊነትና በግልጽነት ለማከናወን ይገደዳሉ።


4. ሕጋዊነትን መስጠት

በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሥልጣን የያዘ መንግሥት በሕዝብ ዘንድም ሆነ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትና ሕጋዊነት ይኖረዋል።

ይህም መንግሥት ያወጣቸውን ፖሊሲዎችና ሕጎች ሕዝቡ በፈቃደኝነት እንዲቀበልና እንዲተገብር ያግዛል።

5. የዜጎችን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ

ምርጫ ዜጎች በአገራቸው የወደፊት ዕድልና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ ያደርጋል።

ድምፅ በመስጠት ሂደት ውስጥ መሳተፍ የዜግነት ክብርንና ኃላፊነትን ያሳድጋል።

6. የፖሊሲና የአማራጭ ሐሳቦች ፉክክር

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አገርን የሚጠቅሙ አማራጭ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የፖለቲካ ፖሊሲዎችን ይዘው እንዲቀርቡ ያደርጋል።

ይህ የሐሳብ ፉክክር ሃገር የተሻለ የዕድገት አቅጣጫ እንድትመርጥ ይረዳታል።

ምርጫ የሕዝብ ድምፅ የሚሰማበት፣ የመንግሥት ሥልጣን የሚወሰነዉ በሕዝብ ድምጽ መሆኑ የሚረጋገጥበትና የሕግ የበላይነት የሚሰፍንበት የዴሞክራሲ ምሰሶ ነው።

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል" – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠...
30/05/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል" – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ በዋና መስሪያ ቤቱ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ለጋራ ግብረ-ኃይሉ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት፣ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለምርጫው ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ቢሆንም፣ መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች እነዚህን የጥፋት ዕቅዶች ማክሸፉን አረጋግጠዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አክለውም፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሪፎርሙ በኋላ በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በዘመናዊ ትጥቅና በቴክኖሎጂ መደራጀቱ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥ እና ከህዝቡ ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በቅድመ-ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ደህንነት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ አያይዘውም፣ ቀሪውን የምርጫ ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ ሎጀስቲክስ እና ትጥቆች መሟላታቸውን እንዲሁም ለተልዕኮው የሚመጥን በቂ ስልጠና እና ኦሪንቴሽን የወሰደ የሰው ኃይል በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች መሰማራቱን ገልጸዋል።

በቀጣይም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና ደህንነት የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከምርጫው በኋላ የሚከናወኑ ሂደቶችም በስኬት እንዲጠናቀቁ ግብረ-ኃይሉ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ኮሚሽነር ጀነራሉ አረጋግጠዋል።

Ethiopian Federal Police

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ማዕከል በበሸኖ ከተማ የ1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።በ...
27/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ማዕከል በበሸኖ ከተማ የ1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ማዕከል በበሸኖ ከተማ የ1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

✍️በደሳለኝ ቱልቻ
ግንቦት 19/2018 በሸኖ፣(ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት በUNFPA የተራድኦ በጀት ድጋፍ በስነ-ተዋልዶ ጤና፣በጾታዊ ጥቃቶች እና በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ...
26/05/2026

በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት በUNFPA የተራድኦ በጀት ድጋፍ በስነ-ተዋልዶ ጤና፣በጾታዊ ጥቃቶች እና በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።

በዌራ ዲጆ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት በUNFPA የተራድኦ በጀት ድጋፍ በስነ-ተዋልዶ ጤና፣በጾታዊ ጥቃቶች እና በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል።

ለግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የተዘጋጀ ሰነድ የዌራ ዲጆ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ባለሙያ በወሪ/ት አምሪያ ዋበላ እና በበሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቶ ሙህዲ አማካኝነት በጎጂ ልማዳዊና በስነ-ተዋልዶ ጤና፣በጾታዊ ጥቃቶች እና በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ዙሪያ በሰፊው ተብራርቶ ቀርቧል።

በዚህም የማጠቃለያ መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ባለሙያ በወሪ/ት አምሪያ ዋበላ አማካኝነት የተመራ ስሆን፣በዚህም ወቅት ለመድረኩ በቀረበው ሰነድ መነሻ ሀሳብ አስተያየት ተነስቶ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች፣ከተለያዩ ቀበሌዎች የተወጣጡ ሴቶች ተገኝተዋል።

✍️በደሳለኝ ቱልቻ
ግንቦት 18/2018 በሸኖ፣(ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ሚ...
25/05/2026

በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ሚና ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ።

የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ፣ፖሊስና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት በጋራ በመሆን ከፖሊስ አባላትና ከጸጥታ ከሚሊሻ ባለሙያዎች ጋር በሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የውይይት መድረኩን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙስጠፋ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረብዩ መሐመድ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ሳጅን ሳብቱ አሊ በጋራ መርተውታል።

በዚህም ወቅት የጸጥታ አካላት በሀገራዊ ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫና በቀጣይ በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚከበረው ኢድ-አል አደሃ በዓል አከባበር ዙሪያ ትኩረት በመስጠት መርሃግብሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ልተገብሩ እንደሚገባ ተገልጿል።

✍️በደሳለኝ ቱልቻ
ግንቦት 17/2018 በሸኖ፣(ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

24/05/2026

"የባህር በር አስፈላጊነትን በመረዳት ቀዳሚ አጀንዳው ካደረገ ፓርቲ ጋር መቆም የነገይቱን ኢትዮጵያ ከመስራት ጋር አብሮ መራመድ ነው":- የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳደርና ግብርና መመሪያ ሀላፊ አቶ ሐጂ ኑሪዬ

!!!
#ምርጫችን- ብልጽግና
#ምልክታችን - የስንዴ ነዶ
በዚህ ሀገራዊ አሻራ አሻጋሪ የሆነዉን ብልፅግና ፓርቲ ይምረጡ የድርሻችንን እንወጣለን!!

በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

#ምርጫ2018


24/05/2026
"የባህር በር አስፈላጊነትን በመረዳት ቀዳሚ አጀንዳው ካደረገ ፓርቲ ጋር መቆም የነገይቱን ኢትዮጵያ ከመስራት ጋር አብሮ መራመድ ነው" አቶ ሀጂ ኑሪዬ*****በዌራ ዲጆ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡ እ...
24/05/2026

"የባህር በር አስፈላጊነትን በመረዳት ቀዳሚ አጀንዳው ካደረገ ፓርቲ ጋር መቆም የነገይቱን ኢትዮጵያ ከመስራት ጋር አብሮ መራመድ ነው" አቶ ሀጂ ኑሪዬ
*****
በዌራ ዲጆ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበት 8ኛ ዓመት እና 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳን አስመልክቶ በሚቶ ዲጆ ታዳጊ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ እንደተናገሩት "የባህር በር አስፈላጊነትን በመረዳት ቀዳሚ አጀንዳው ካደረገ ፓርቲ ጋር መቆም የነገይቱን ኢትዮጵያ ከመስራት ጋር አብሮ መራመድ ነው ስሉ ተናግረዋል።

አቶ ሀጂ አክለው የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ መሆኑን ጠቁመው፣ በለውጡ መንግስት ታሪካዊው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን አብስረዋል።

"መንግስት የወደብ አስፈላጊነትን በልዩ ትኩረት በመረዳት ሀገሪቱን በሰላማዊ መንገድና በድርድር የወደብ ባለቤት ለማድረግ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

የባህር በር አስፈላጊነትን ተረድቶ ቀዳሚ አጀንዳው ካደረገ ፓርቲ ጋር መቆም የነገይቱን ኢትዮጵያ በጋራ ከመስራት ጋር አብሮ መራመድ ነው በማለት አቶ ሀጂ ተናግረዋል።

የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም በበኩላቸው ፓርቲያችን የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

አቶ አብዲ አያይዘውም የብልጽግና መንግስት የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን አስደናቂ ጉዞ እውን ለማድረግ የአፈር ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ለማምረት የፋብሪካ ግንባታ መጀመሩ በቀጣይ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር ቀጥተኛው ማሳያ እንደሆነ አመላክተዋል።

የዌራ ዲጆ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሱራጅ ጎድሶ እንደተናገሩት ይህ በሰላማዊ አማራጭና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተው የወደብ ባለቤትነት ጥረት የሀገሪቱን የንግድና የኢኮኖሚ አቅም ከመገንባት ባለፈ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያላትን ተሰሚነትና ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ካለፉት የፖለቲካና የማህበራዊ ቁርሾዎች ወጥታ በሀገራዊ ምክክርና በሽግግር ፍትህ ሂደት አዲስ ምዕራፍ እየቀረጸች መሆኑን የገለጹት ዋና ተጠሪው፣ፓርቲው ያስቀመጣቸውን ታላላቅ ሀገራዊ ራእዮች ይፋ አድርገዋል፦

በ2023 ዓ.ም፦ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ሁለንተናዊ የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ።

በ2040 ዓ.ም፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት ብልጽግናቸውን ካረጋገጡና በኢኮኖሚ ከበለጸጉ ቀዳሚዎቹ 10 ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን ማስቻል ነው ብለዋል።

አቶ ሱራጅ በመጨረሻም በግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገራዊ ክልላዊ ምርጫ ላይ መላው አባላት የብልጽግና ፓርቲ በመምረጥ ሀገራዊ ግዴታቸውን ልወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።ሲል የዘገበው የወረዳው መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በሁሉም መስክ ስኬታማ ስራዎች ተሰርቷል ፦ ወ/ሮ ዘብባ ሀ/ናስር **********ግንቦት 16/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛው በደኔ ቀበሌ በወረዳው ብልፅግና ...
24/05/2026

በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በሁሉም መስክ ስኬታማ ስራዎች ተሰርቷል ፦ ወ/ሮ ዘብባ ሀ/ናስር
**********
ግንቦት 16/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛው በደኔ ቀበሌ በወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያና የቅስቀሳ መርሐግብር ተካሄደዋል ።

‎መድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሀላፍ ወ/ሮ ዘብባ ሀ/ናስር እንደገለፁት ብልጽግና ፓርቲ ሀገርን መምራት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በሁሉም መስክ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን የሚያደርጉ ስራዎችን በመስራት የተመሠከረለት ፓርቲን ወክሎ መወዳደር ልዩ ስሜትን እንደሚፈጥርና ብልፅግና ፓርቲ በቀጣይም ቃሉን ጠብቆ ለክልላችን እና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና እንደሚሰራም ገልፀዋል ።

ብልፅግና ፓርቲ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚተጋ እና ሀገር የምትገነባው በሴቶች የላቀ ተሳትፎ መሆኑን የሚያምን ፓርቲ መሆኑንም ወ/ሮ ዘብባ ጠቁመዋል።

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ተዓማኒ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን እና በብልጽግና ፓርቲ በአብላጫ ድምጽ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ክንፍ አመራርና አባላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ኃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ የብልጽግና ፓርቲ ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ጠቁመው በዚህ የምርጫ ሂደትም አባሎቻችን ጉልህ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ወ/ሮ ዘብባ።

የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ለሴቶች ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ፓርቲ መሆኑን ገልፀው ፓርቲ በሰጠው ትኩረት መሠረት የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ።

ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር መሆኑን ጠቅሰው በሴቶች ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ላይም በቁርጠኝነት እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል ።

ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ይችላሉ በማለት የሴቶችን ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ እያረጋገጠ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው ሴቶች የብልፅግና ስኬቶችን በመግለፅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል ።

በመድረኩ ላይ ዞኑ ለብልፅግና ፓርቲ ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልሉ ምክር ቤት ያቀረባቸው እጩዎች የትውውቅ ስነ ስርዓት በማድረግ ቀጣይ ተልዕኮዎችን በመቀበል መርሃ ግብሩ ተጠናቋል ።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ እና የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ ያዲሶ ዱበላ፣ የሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት ጀማል ፣የዌራ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል እና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙዘይን ጀማል የዌራ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አምሪያ ሁሴን እና ሌሎችም የዞን እና የወረዳው የፓርቲ ባለድርሻ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።ሲል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

የእግር ኳስ ፍቅር ለሰብአዊነት በሚል ሃሳብ የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች በሚተካ ደም የማይተካ የብዙሃንን ህይወት ለመታደግ የደም ልገሳ አደረጉየእግር ኳስ እውነተኛ ውበትና አቅም ከደጋፊነት ...
24/05/2026

የእግር ኳስ ፍቅር ለሰብአዊነት በሚል ሃሳብ የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች በሚተካ ደም የማይተካ የብዙሃንን ህይወት ለመታደግ የደም ልገሳ አደረጉ

የእግር ኳስ እውነተኛ ውበትና አቅም ከደጋፊነት ስሜት በላይ ወጥቶ ለወገን ደራሽ መሆን መቻሉን የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች በተግባር አሳይተዋል።

መድፈኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እጅግ አስደናቂና አስደሳች በሆነ ሁኔታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን ተከትሎ ደስታቸውን በጭፈራ ብቻ ሳይሆን የሰውን ህይወት በሚታደግ በጎ ተግባር አክብረውታል።

የሻምፒዮናነቱ ድል እና በጎ አድራጎቱ በሀላባ ሴራ አደራሽ
የሀላባ የአርሰናል ደጋፊዎች የዓመቱን የመጨረሻ ጨዋታ በጋራ ለመታደም እና የዋንጫ ድላቸውን ለማክበር በሀላባ ሴራ አደራሽ በታላቅ ድምቀት ተሰባስበው ደም ልገሳ አድርገዋል።

ስፖርት በፍቅርና በስነ-ስርዓት ከተያዘ አንድነትን ለማጠናከር፣ የሰውን ህይወት ለመታደግ ብሎም ለሀገር ግንባታና ለልማት ትልቅ አቅም መፍጠር እንደሚችል ደጋፊዎቹ በተግባር አስመስክረዋል።

ደጋፊዎቹ ከዚህ በጎነት ተግባር በተጨማሪ የጽዳትም ዘመቻም አካሄደዋል ሲል የዘገበው የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ነው።

Address

Besheno
Alaba K'ulito
HALABA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት:

Share