Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ

Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት Security Guard

ለኮሪደር ልማት የተዘጋጀን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለውን የኤሌክትሪክ ኬብል የሰረቁ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡***አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28 ቀን 201...
06/05/2026

ለኮሪደር ልማት የተዘጋጀን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለውን የኤሌክትሪክ ኬብል የሰረቁ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ሦስቱ ግለሰቦች ወንጀሉን የፈፀሙት ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ስፖርት ፌደሬሽን አካዳሚ ፊት ለፊት ከጠዋቱ 4 ላይ ነው።

አስመራ ነገራ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 47749 ኢት የሆነ ክሬን ተሽከርካሪ ሹፌር፣ ኤልያስ በርሄ የሹፌሩ ረዳት እና ወርቁ ኖራህ ተባባሪ በመሆን 9 ጥቅል እና አንድ ገመድ የሌለው የኬብል መጠቅለያ አጠቃላይ የዋጋ ግምቱ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣና ለኮሪደር ልማት ሊዘረጋ የነበረ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ ሲጭኑ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ገመዶች አስጭናችሁ አምጡ ተብለን ነው በማለት ንብረቱን ሲጭኑ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ ሦስቱ ወንጀል ፈፃሚዎች ከነተሽከርካሪው እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገ ተጨማሪ ምርመራ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ሰራተኞች አለመሆናቸው ተረጋግጧል።

ወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ከፍንጅ እንዲያዙ የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ፖሊስ ገልፆ የወንጀል ፈፃሚዎች መያዝ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ያለው ቁርኝት ይበልጥ እየጠነከረ መምጣቱን ጥሩ ማሳያ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትልቅ ምስጋና የሚቸረውና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ

“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”

የሀላባ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም ላይ ድጋፍና ክትትል አደረገ።።።።...
06/05/2026

የሀላባ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም ላይ ድጋፍና ክትትል አደረገ።

።።።።።ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ዌራ፤።።።።።

የሀላባ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ አቶ ሁሴን ኢብራህም የተመራው የዞንና የዌራ ወረዳ የድጋፍና ክትትል ቡድን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትን በ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር የዕቅድ አፈፃፀምን በቼክ ሊስት ድጋፍና ክትትል አደረጉ።

ቡድኑ ለድጋፍና ክትትል አዘጋጅቶ ባቀረበዉ ቼክ ሊስት መሠረት በጽ/ቤት እስካሁን የተከናወነ ዕቅድ አፈፃፀም መሠረት ምላሽና ማብራርያ የተሰጠ መሆኑን የወረዳዉ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢ/ር ናስር አወል ገለፁ።

የዞንና የወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በጽ/ቤቱ ባደረገዉ ድጋፍና ክትትል በክንዉን ወቅት ተግዳሮት የገጠማቸዉ ዉስንነቶች ቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫ የተመላከተ ሲሆን አንዳንድ የተስተዋሉ ጉድለቶች መሻሻል እንዳለበቸዉ እና ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረዉ መቀጠል እንደሚገባቸዉ ሀሳብ አስተያየት በመስጠት ዉይይቱ ተጠቃሎ የተከናወኑ ተግባራትን የመስክ ምልከታ ማድረጋቸዉንም ገልፀዋል።

=====ወንጀልን በጋራ እንከላከል።=====

ሸምሰዲን ከድር
ረ/ኢ/ር

ለሴት የፖሊስ አመራርና አባላት የተዘጋጀ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ መሰጠቱ ተገለፀሆሳዕና ሚያዝያ 27 ቀን 2018 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዳይሬ...
05/05/2026

ለሴት የፖሊስ አመራርና አባላት የተዘጋጀ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ መሰጠቱ ተገለፀ

ሆሳዕና ሚያዝያ 27 ቀን 2018 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከወርልድ ቨዥን ኢትዮጵያ ሌሞ አካባቢ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለሴት የፖሊስ አመራርና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል።

ስልጠናዉ በሴቶችና ህፃናት ጥቃት ዙረያ እንዲሁም ለክልሉ ሰላም እሴት ግንባታ የሴት ፖሊስ ሚና በሚሉ ርዕሶች ላይ የተዘጋጀና ለሁለት ተከታታይ ቀናት መሰጠቱን ተገልጿል።

በስልጠናዉ ክልሉ ፖሊስ የተለያዩ ክፍሎች ፣ከዞንና ከልዩ ወረዳ የመጡ ሴት የፖሊስ አባላት ተሳታፊ መሆናቸዉን ከኮሚሽኑ ሴቶችና ህፃናት ክፍል ያገኘንዉ መረጃ አመላክቷል።
# #ሰላም!!

በአርባ ምንጭ የምርጫ ማስታወቂያ የቀደደው ግለሰብ በ9 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ።በአርባ ምንጭ ከተማ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያ በመቅደድ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በዘጠኝ...
04/05/2026

በአርባ ምንጭ የምርጫ ማስታወቂያ የቀደደው ግለሰብ በ9 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በአርባ ምንጭ ከተማ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያ በመቅደድ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በዘጠኝ ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ወላይታ ሶዶ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም(ደኢፖኮ)

ተከሳሽ ተመስገን ካርታ አይሳ የተባለ የ25 ዓመት ወጣት በፈጸመው ሕገ-ወጥ ድርጊት ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

የወንጀሉ ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ ድርጊቱ የተፈጸመው ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 12፡30 ገደማ በሼቻ ክፍለ ከተማ ጫሞ ቀበሌ "ባይራ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ግለሰቡ በኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው የነበሩ ሁለት የምርጫ ማስታወቂያዎችን በመቅደድ ስራ ላይ እያለ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

እነዚህ ማስታወቂያዎች ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል የሚወዳደሩ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎችን የሚወክሉ እንደነበሩ ተገልጿል።

የሼቻ ክፍለ ከተማ ታክቲክ ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ተወካይ ም/ኢ/ር ቤዛ ቤርገሳ ለሚዲያ እንደገለጹት፣ ፖሊስ ምርመራውን በሰው ምስክር አጠናክሮ ለዐቃቤ ሕግ መላኩንና ዐቃቤ ሕግም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 158ን መሠረት በማድረግ ክስ መስርቶበታል።

የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በዛሬው ዕለት በዋለው የወንጀል ችሎት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተከሳሹን የዘጠኝ ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ እንደገለጸው፣ ቅጣቱ ወንጀል ፈጻሚውን ከማረሙም በላይ ሌሎች መሰል እኩይ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላትን የሚያስጠነቅቅና የሕግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ነው።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ሕብረተሰቡ ከእንዲህ ዓይነት የዴሞክራሲ ሂደትን ከሚያውኩ ተግባራት እንዲቆጠብ መልዕክቱን አስተላልፏል።

መረጃው የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነው።

በሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በትራንስፖርርት ዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቁጥጥሮች ተጠናክረው ቀጥለዎል።በትራንስፖርት ዘርፍ የተወሰደው እርምጃ የሚመሰገን ነው ያሉት ተሳፋ...
04/05/2026

በሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በትራንስፖርርት ዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቁጥጥሮች ተጠናክረው ቀጥለዎል።

በትራንስፖርት ዘርፍ የተወሰደው እርምጃ የሚመሰገን ነው ያሉት ተሳፋሪዎች ቀጣይም ቁጥጥሩ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ገለፁ።

የዜጎችን እንግልት ለማስቀረትና የትራንስፖርት መስተጓጎልን ለመቀነስ መንግስት ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ ማደያዎች ቅድሚያ እንዲያገኙ እያደረገም ይገኛል።

ይሁን እንጂ ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ከታሪፍ በላይ በማስከፈል አሁንም ህብረተሰቡን የሚያማርሩ አሽከርካሪዎች እንዳሉ ተሳፋሪዎች ይናገራሉ።

ተሳፋሪዎችም እየከፈሉ እንደነበር አስታውሰው መስተጓጎሉን ለመቅረፍ መንግስት የወሰደውን ወሳኝ እርምጃ አድንቀዋል።

ሌላኛው ተሳፋሪ አቶ መሀመድ የትራንስፖርት ታሪፍ መሻሻሉ ትልቅ እፎይታ የሰጠ መሆኑን ተናግረው አሁንም መናሀሪያ ቆርጠን ከወጣን ቡኋላ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ጭማሪ እያስከፈሉን በመሆኑ ቀጣይ የበለጠ እንዲሻሻል መንግስት በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ከአሁን በፊት ለከፍተኛ ችግር ይጋለጥ እንደነበር ያስታወሱት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሡልጣን አ/ቃድር መንግስት ችግሩን ካስተካከለ ወዲህም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ እንዳሉ ጠቁመው ተገልጋዩ ማህበረሰብ መብቱን ማስከበር እና ጥቆማ በመስጠት አጋዥ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተሰሩ ስራዎች ፦ ከታሪፍ በላይ በማስከፈ ፣ ከመናህሪያ ውጭ በመጫን ከተፈቀደለት ሰው በላይ መጫን የተያዙ መኪኖች ላይ እጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከታሪፍ በላይ ተከፍሎ የተመለሰ የገንዘብ መጠን በሁሉም መስመሮች አጠቃላይ 28,500 ብር በላይ ነው

ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር፣ ለህግ አስከባሪዎች መረጃ በመስጠት እንዲተባበር እና በጋራ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን እንዲከላከልም አጋዥ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የኮሩ የሠራዊት አባላት ለጥፋት የተዘጋጁ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረ...
03/05/2026

የኮሩ የሠራዊት አባላት ለጥፋት የተዘጋጁ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ የተሰማራው የማዕከላዊ ዕዝ ጋሻ ኮር የሰራዊት አባላት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ለጥፋት የተዘጋጁ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የፅናት ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ተወካይ ሻለቃ መለስ አስማማው ተናግረዋል።

ሻለቃ መለስ እንዳሉት ክፍለጦሩ የፀረ ሰላም ሃይሎችን ህገወጥ ተግባር በየጊዜው በማክሸፍና በማምከን የሀገርን እና የህዝብን ሰላም በታላቅ ቁርጠኝነት እያስጠበቀ ይገኛል።

መቶ አለቃ ሳምሶን ከበደ በበኩላቸው አሁን ላይ በየጫካው ተበትኖ በተራ ሽፍትነት የዘረፋ ተግባር ላይ የተሰማራው የፅንፈኛው እና የሸኔ ቡድንን እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ከመቼውም በተለየ ሁኔታ ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን ገልፀው የጥፋት ቡድኑን በገባበት ገብተን የመደምሰሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በተመሳሳይ የጋሻ ኮር አይበገሬ ክፍለጦር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እየተቀሳቀሴ በህዝብ ላይ ኢ-ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሲያደርስ በቆየው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ ታጣቂዎችን በመማረክ ብሬን ጨምሮ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክፍለጦሩ አዛዥ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍቃዱ አበራ ነው

03/05/2026
በውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በፖሊስ ክትትል ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ።‎***አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አብዲ ሀሰን እ...
03/05/2026

በውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በፖሊስ ክትትል ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
‎***
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አብዲ ሀሰን እና ቃልዓብ ወርቁ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ኢሰመኮ አካባቢ ነው የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት።

ኢብራሂም ሀሰን የተባሉ የዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዜግነት ያላቸው የግል ተበዳይ በአካባቢው ካለ ሱፐር ማርኬት ዕቃ ገዝተው ወደ አረፉበት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል እያመሩ ሳለ ተጠርጣሪዎቹ በግራና በቀኝ ሆነው በማዋከብ አንደኛው ተጠርጣሪ ሄድ ፎን ግዛን ሲል ሁለተኛው ተጠርጣሪ ከግል ተበዳይ ኪስ ውስጥ በመግባት ግምቱ 2 መቶ ሺ ብር የሚያወጣ አይፎን15 ፕሮማክስ ሞባይል ስልክ በማውጣት ከአካባቢው መሰወራቸውን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የባምቢስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።

‎ፖሊስ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ፈጣን የሆነ የምርመራ እና የክትትል ስራ በመስራት ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች በሰዓታት ልዩነት ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው መቻሉን አስታውቋል።

‎ራስን ባልተገባ መንገድ ለማበልጸግ መሠል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚገቡ አካላት ከፖሊስ አይን እና ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን መልካሙ ዜና

“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”

በሀላባ ዞን ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር  ተደረገ፡፡በሀላባ ዞን ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ ፣ ትርፍ ሰው በሚጭኑ እና ከተሰጣቸው ስምሪት ውጭ የሚንቀሳቀሱ (ከመራሀ-...
03/05/2026

በሀላባ ዞን ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ተደረገ፡፡

በሀላባ ዞን ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ ፣ ትርፍ ሰው በሚጭኑ እና ከተሰጣቸው ስምሪት ውጭ የሚንቀሳቀሱ (ከመራሀ-ግብር ውጭ) እየሰሩ የነበሩ ከመነሐሪያ ውጪ የጫኑ መኪኖች ላይ
1. 00004ማ/ኢ
2.02156ማ/ኢ
3.04055ማ/ኢ
4.02124ማ/ኢ
እጋዊ እርምጃ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

በሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ እና ትራፊክ ፖሊስ ተቋም ጋር በመቀናጀት በሀሉም መስመሮች ላይ በተደረገ ጥብቅ ቁጥጥር ከተቀመጠው የታሪፍ ገደብ ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ ተከፍሎ የነበረ ከ12,500 ብር በላይ በማስመለስ ለተሳፋሪዎች እንዲሰጥ መደረጉ ተመላክቷል።

የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች የዋጋ ጭማሪን ምክንያት በማድረግ የተከሰተውን ችግር ለማቃለል መንግስት ከበጀት ድጎማ ጀምሮ የተለያዩ የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ችግሩን ለመቅረፍ የተቀመጡ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ በሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ እና ትራፊክ ፖሊስ ተቋም አስታውቋል።

የትራንስፖርት ማህበራት መንግስት ባወጣው ታሪፍ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን በማህበረሰቡ ላይ ጫና በሚፈጠሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሡልጣን አ/ቃድር ገልፀዋል።

ትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!!

በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ የሚሊሻ አባላት የስልጠና መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።በወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ከወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገዛ የሚሊሻ...
03/05/2026

በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ የሚሊሻ አባላት የስልጠና መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ከወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገዛ የሚሊሻ አባላት የደንብ ልብስ ምረቃ እና የሚሊሻ አባላት የስልጠና መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ-ግብሩ የዌራ ዲጆ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሱራጅ ጎድሶ፣የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙደስር ጉታጎ፣የሀላባ ዞን ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገመቹ ወርቅቾ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ አለሙ ዳርሰቦ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙስጠፋ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረብዩ መሐመድ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ሳብቱ አሊን ጨምሮ የጸጥታና የሚሊሻ ባለሙያዎች እንድሁም የፖሊስ አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ሚያዝያ 25/2018 (ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለሚያስገነባው የተሽከርካሪ ጥገና ማእከልና የነዳጅ ማደያ ግንባታ ለማስጀመር ከተቋራጭ ድርጅቱ ጋር ውል ፈጸመ።ወላይታ ሶዶ ሚያዝያ 22/2018 ዓ/ም(ደኢ...
30/04/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለሚያስገነባው የተሽከርካሪ ጥገና ማእከልና የነዳጅ ማደያ ግንባታ ለማስጀመር ከተቋራጭ ድርጅቱ ጋር ውል ፈጸመ።

ወላይታ ሶዶ ሚያዝያ 22/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ)

ግንባታው በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ እንደሚሠራ ተቋራጭ ድርጅቱ አስታውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ተደራሽ የማድረግ አቅምን ከፍ ያደርጋል ተብሎ እምነት የተጣለበትና በክልሉ መንግስት በበጀት አመቱ እንዲገነባ በጀች የተያዘለት ፕሮጀክት እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ ወቅት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው የፖሊስ ተቋም የስራ ባህሪ ወትሮ ዝግጁነትን የሚጠይቅ እንደሆነ ገልጸው የቴክኒክ ብቃታቸው የተረጋገጠ ተሽከርካሪዎችና የነዳጅ አቅርቦት መኖር አገልግሎት አሰጣጣችንን እንደሚያቀላጥፍ ይታመናል ብለዋል።

ይህን ግንባታ ለማከናወን ያሸነፈው አንጆኑስ ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግል ድርጅት አስፈላጊነቱን ከግምት በማስገባት በጥራትና ፍጥነት አጠናቆ እንዲያስረክብ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ በግንባታ ሒደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመከታተል ለመፍታት ይሞክራል ብለዋል።

የተቋራጩ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አበበ አሞኖ በበኩላቸው የዚህ ግንባታ አሸናፊ ሆነን ከፖሊስ ጋር መስራት በመቻላችን እጅጉን ደስተኞች ነን ያሉ ሲሆን ግንባታውን በጥራትና በተያዘለት ጊዜ አጠናቀን ለማስረከብ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ተብሏል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ ግንባታው በ84557256.51 (ሰማኒያ አራት ሚሊየን ስምንት መቶ ሀምሳ ሰባት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት ከሃምሳ አንድ ሳንቲም) ወጪ የሚደረግበት ሲሆን የተሽከርካሪ ጥገና ማእከል፣ቢሮ፣ ካፍቴሪያና መጸዳጃ የተሟላለት እንደሆነ ተገልጿል።

በውል ስምምነቱ ወቅት የክልሉ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተቋራጩ ባለቤት እንዲሁም ከክልሉ ኮንስትራክሽን ቢሮ የተወከሉ ባለሞያዎች በተገኙበት ተፈርሟል።

የተፈቀደዉን ኪሎ ሜትር ጥሰዉ የተገኙ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ትራፍክ ፖሊስ ተቆጣጥረዉ እርምጃ መዉሰዱ ተገለፀ።።።።።።።22/08/2018 ዓ.ም ዌራ፤።።።።። የተፈቀደዉን ኪሎ ሜት...
30/04/2026

የተፈቀደዉን ኪሎ ሜትር ጥሰዉ የተገኙ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ትራፍክ ፖሊስ ተቆጣጥረዉ እርምጃ መዉሰዱ ተገለፀ።

።።።።።።22/08/2018 ዓ.ም ዌራ፤።።።።።

የተፈቀደዉን ኪሎ ሜትር ጥሰዉ የተገኙ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ትራፍክ ፖሊስ ተቆጣጥረዉ እርምጃ መዉሰዱን በዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፍክ አደጋ መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ረ/ኢ/ር ፉዓድ ታጁ ገለፁ።

ከተፈቀደዉ በላይ ርቀት ስያሽከረክሩ የተገኙ የባለ ሦስት እግር ባጃጂ ተሽከርካሪወችን መቆጣጠርና እርምጃ መዉሰድ የትራፍክ አደጋን ለመከላከል ስባል ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በቅንጅት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኃላፊዉ አክለዉም የተሽከርካሪ ደንብ መተላለፊ ጥሰቶች ከጥቅሙ ይበልጥ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን አዉቀዉ ከጥሰቱ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንድያደርጉም አሳስበዋል።

።።።።የትራፍክ አደጋን በጋራ እንከላከል።።።።
የወረዳዉ ትራፍክ ማኔጅመንት

በሸምሰዲን ከድር
ረ/ኢ/ር

Address

City
Alaba K'ulito
POLICE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ:

Share