በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት, Government Organization, ሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ, Alaba K'ulito.

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል።
27/05/2026

1447ኛው የዒድ አልአድሃ (ዓረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በድምቀት ተከብሯል።

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ተገመገመ*************(ግንቦት፣17/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶ...
25/05/2026

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ተገመገመ
*************
(ግንቦት፣17/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ተገምግሟል።

የግምገማ መድረኩን ያመሩት የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር አብዱልቃድር አማን፣የሀላባ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባ አልዬ በጋራ በመሆን መርተዋል።

7ተኛ ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠነቀቅ የአመራሩ ሚና የጎላ መሆኑ ተገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በክሪ አብደላ፣እንዲሁም የዞን የወረዳ አመራሮች ሌሎችም ተገኝተዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

➡ ሀገር የሚያበለፅግ ጤናማ ዜጋ የመፍጠር!!ጉዞ በሀላባ ዞን፣●በጤና ዘርፍ ፓርቲያችን አንግቦ እየሠራ የሚገኘውን በሽታን ከመከላከል ባለፈ አክሞ የማዳን ተግባር ውጤታማነትን ወደላቀ ደረጃ ለ...
25/05/2026

➡ ሀገር የሚያበለፅግ ጤናማ ዜጋ የመፍጠር!!ጉዞ በሀላባ ዞን፣

●በጤና ዘርፍ ፓርቲያችን አንግቦ እየሠራ የሚገኘውን በሽታን ከመከላከል ባለፈ አክሞ የማዳን ተግባር ውጤታማነትን ወደላቀ ደረጃ ለመሸጋገር ጉልህ ሚና አለው!!

ፓርቲያችን ባለፉት ስምንት የለውጡ ዓመታት እንደሀገር በጤና ዘርፍ ያገኘቻቸውን ውጤቶች እንደ ምንዳ በመያዝ፣ የነበሩበትን ክፍተቶች የማሻሻል ሥራ ሠርቷል።

በዚህም መሠረት በሥራ ላይ የነበረው የጤና ፖሊሲ፣በሽታን ከመከላከል ባለፈ አክሞ ማዳን ላይ እንዲያተኩር ተደርጓል።

ይህንንም ግብ ከደር ለማድረስ እንዲቻል በፓርቲያች ብልፅግና የሚመራው የመደመር መንግስት በጤናው ዘርፍ የጤና ፖሊሲን ሪፎርም በማድረግ በሽታን ከመከላከል ወደ አክሞ ለማዳን የመንግሥትና የግል ዘርፍ የጤና ተቋማት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እየሠራ ይገኛል።

እንደ ሀላባ ዞንም ከለውጡ ወዲህ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡን ፍትሃዊ የጤና ይበልጥ ለማጎልበት በርካታ የጤና ተቋማት ተገንብተው የተሳለጠ አገልግሎት እየሰጡ ናቸዉ።

የጤና ተቋማት በመድኃኒት የመደገፍ፣በቁሳቁስ የማሟላት እና ሌሎችንም ጤናን የሚያጎለብቱ ተግባራት በስፋት ተከናውኗል።

ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት በዞኑ በየደረጃው ከተገነቡት የጤና ተቋማት የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የላቀ አስተዋጽኦ እየበረከቱ ይገኛሉ።

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት የብልጽግና ፓርቲ ወረዳዊ የምርጫ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሃግብር ተካሄደበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ...
25/05/2026

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት የብልጽግና ፓርቲ ወረዳዊ የምርጫ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሃግብር ተካሄደ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወረዳዊ የምርጫ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር የድጋፍ ሰልፍ በወረዳ ማዕከል በበሸኖ ከተማ ተካሂዷል።

በዕለቱ መርሃግብር ላይ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደተናገሩት በለውጡ መንግስት ጊዜውን የዋጀ ዘመን ተሻጋሪ ሀሳቦች መነሻ በማድረግ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ገልፀው፣ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር የመቀየር ቃላችንን የምናድስበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉም አብራርተዋል።

በዚህም የለውጡ መንግስት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የነበሩ በንጽሁ መጠጥ ውሃ፣በመንገድና በማብራት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየፈታ መሆኑን አቶ ሙህዲን ተናግረዋል።

የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም፣በበከላቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ፣የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲ መምረጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በፖለቲካ ፣በኢኮኖሚ ፣በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲ መስኮች የተመዘገበው ውጤት በአለም አቀፍም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ በአብነት የሚጠቀስ ነው ሲሉም አቶ አብዲ ተናግረዋል።

የመደመር መንግስት በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ እና የነበሩ ስብራቶችን ለመጠገን እየሰራ ስለመሆኑ የተናገሩት አቶ አብዲ የመጪውን ትውልድ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲ በመምረጥ ሀገራዊ ግዴታቸውን ልወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የሀላባ ቁ.1 ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ አቶ ሙበራ ለሀላባ ዞን አስተዳደርና ለሀገር ሽማግሌዎች በስልጤ ብሔረሰብ ለጀግናው ህዝብ የሚሰጥ ባህላዊ ምግብ በስጦታ መልክ አበርክተዋል።

✍️ግንቦት 17/2018(ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

የብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን እኩልነትንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ስሰራ ቆይቷል፦ክብርት መነቴ ሙንድኖ========(ግንቦት፣16/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ  ብልጽግና ፓር...
24/05/2026

የብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን እኩልነትንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ስሰራ ቆይቷል፦ክብርት መነቴ ሙንድኖ
========
(ግንቦት፣16/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩትን እጩዎችን የማስተዋወቅና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐግብር በጤፎ ግርሜ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

ክብርት መነቴ ሙንዲኖ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/አፈጉባኤ በመርሐግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነትን በትኩረት ስሰሩ መቆየቱን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሰራው ጠንካራ ስራም ሴቶች ከቀበሌ አስከ ፌዴራል ለትልልቅ ኃላፊነቶች በመብቃት ሀገራቸውን እያገለገሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ፓርቲያችን ለሴቶች የሰጠውን ትኩረት መላው ህብረተሰባችን በውል በመገንዘብ ሴቶችን ከስደት ይልቅ እንዲማሩ ማድረግ ቅድሚያ መስጠት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ነው አመላክተው ህብረተሰቡ ብልጽግናን ብልጽግናን እንዲመርጥ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በክሪ አብደላ በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ ብሄር ብሄረሰቦችን እኩል የፖለቲካ ተሳትፎን ለማረጋገጥ አግላይ ፖለቲካን በማስቀረት ሁሉንም ያሳተፈና አካታች ስርዓትን መፍጠሩን አብራርተዋል።

ፓርቲው ትላልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎችን በመያዝና በርካታ ፈተናዎችን በጽናት በማሻገር አበረታች ውጤቶችን በማስመዝገብ ዛሬ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ለብሄር ብሄረሰቦች እኩልነትና ፍትሃዊነት እንዲሰፍን ሀገር ጸንታ እንድትቀጥል ብልጽግናን ይምረጡ "ኢትዮጵያውያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ ገራድ ድልታታ ሙዜ በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ ከባለፉት ስርዓቶች አንጻር ለህብረተሰቡ በእጅጉ መጥቀሙን ገለጸው የሀላባ ህዝብ ብልጽግና ፓርቲ እንዲመርጥ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል !!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የባለፉት 8 የለውጡ አመታት ጠንካራ የዕሳቤ ለውጥ በመተግበር በብልጽግና ፓርቲ ግንባር ቀደም መሪነት፣በመደመር መንግሥት ንቁ ክዋኔ እና በተደራጀ የህዝ...
23/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የባለፉት 8 የለውጡ አመታት ጠንካራ የዕሳቤ ለውጥ በመተግበር በብልጽግና ፓርቲ ግንባር ቀደም መሪነት፣በመደመር መንግሥት ንቁ ክዋኔ እና በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ በየዘርፉ በተከናወኑት ተግባራት
በርካታ ታሪክ የቀየሩ አንጸባራቂ ድሎች ተገኝተዋል።
ለአብነትም፦
➡ ክቡር አቶ ሙህድን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በዞናችን የባለፉት የለውጡ ዓመታት የህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በውሃ እና በመንገድ በሌሎችም መሠረተ ልማቶች፣ እንዲሁም በየዘርፉ በተከናወኑት ተግባራት አንጸባራቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የጤና ሽፋን ማሳደግ ተችሏል!!፤የትምህርቱ ዘርፍ በማሳለጥ ከዞንም ባለፈ ሀገር መረከብ የሚችል ዜጋ ለማፍራት በአጽንኦት ተሠርቷል፣እየተሠራ ይገኛል። በአጠቃላይ በዞኑ የህብረተሰቡን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣እና ሌሎችንም መስኮች ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል፣በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ።
➡አቶ መሐመድካማል ኑርዬ፦የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ!!በዞኑ ከለውጡ ወዲህ የህዝቦችን አንድነት በጽኑ መሰረት የገነባውና በልማቱ ጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ እውን ያደረገው የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ለቀጣዮቹ ትልልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ልማት ሥራዎች የአርአያነት መሰረት የጣለ ሜጋ ፕሮጀክት አንዱና ዋነኛ መሆኑን አንስተዋል!!።

በተለይም ኃላፊ እንደገለፁት በለውጡ ዓመታት፦
●ከሁሉ በላይ አንጻራዊ ሰላም ማሰፈን፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ህብረብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብት አስችሏል።
●ከዕዳ ወደምንዳ እና የመደመር መንግሥት እሳቤ ለዘርፎች እምርታ በሚል የተሰጠው ስልጠና በአጠቃላይ አመራር፣ አባል፣በአርሶአደሩ አስተሳሰብና ተግባር አመርቂ ውጤቶችን አስገኝቷል።
ይህም በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል።

ይህንንም ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ሁሉም ዜጋ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ ይገባዋል።

ሁሌም ድልና ድምቀት ለፓርቲአችን!!፣ ለለውጡ መንግሥታችን እና ለመላው ህዝባችን ይሁን!!፣

#ክፍል በቀጣይ ይቀጥላል!!

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ፣ግንቦት 15/2018፤ሀላባ ቁሊቶ፤

●ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!!!➡ #ምርጫችን  #ብልጽግና ➡ #ምልክታችን!! #የስንዴ ነዶ ነው።➡ #መልዕክታችን  !●ለሀገርና ለዜጎች ሁለንተናዊ ለውጥና ተጠቃሚነት ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!...
23/05/2026

●ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!!!
➡ #ምርጫችን #ብልጽግና
➡ #ምልክታችን!! #የስንዴ ነዶ ነው።
➡ #መልዕክታችን !

●ለሀገርና ለዜጎች ሁለንተናዊ ለውጥና ተጠቃሚነት ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!፣

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል !!

ባለፉት የለወጡ ዓመታት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃን ተደራሽነት ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የአቶቲ ኡ...
22/05/2026

ባለፉት የለወጡ ዓመታት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃን ተደራሽነት ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ኢንጅነር አ/ቃድር አማን

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በወቅታዊና መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች የወረዳው አስተባባሪዎች በተገኙበት ተገመገመ!*************(ግንቦት፣14/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መ...
22/05/2026

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በወቅታዊና መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች የወረዳው አስተባባሪዎች በተገኙበት ተገመገመ!
*************
(ግንቦት፣14/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በወቅታዊና መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች በተላይም ግንቦት 24 2018 ዓ.ም 7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በማስመልከት የሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተገምግመው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።

7ኛ ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለመስቻል አመራሩ ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ተገልጸዋል

ግንቦት 24 ህዝቡ በነቂስ በምርጫ ጠቢያዎች ድምጹን እንዲሰጥ ቀን በቀን ቅስቀሳ ማድረግ እንዲገባ ተገልጸዋል።

በመድረኩ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በክሪ አብደላና የወረዳው ፓርቲ ምክትል ሀላፊዎች የመሩ ሲሆን በመድረኩ ሰፊ ሃሳብ አስተያየቶች ተነስተው መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

የዛሬው ፕሮግራም በሰላምና በድምቀት እንዲጠነቀቅ አስተዋጾ ያደረጉ አካላትን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር አብዱልቃድር አማን አመሰገኑ!=======(ግንቦት፣14/2018 ዓ.ም)ጉ...
22/05/2026

የዛሬው ፕሮግራም በሰላምና በድምቀት እንዲጠነቀቅ አስተዋጾ ያደረጉ አካላትን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር አብዱልቃድር አማን አመሰገኑ!
=======
(ግንቦት፣14/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ በዛሬው ዕለት በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ የተመረቀውን ፕሮጀክት በድምቀትና በሰላም እንዲጠነቀቅ አስተዋጾ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል ።

የዛሬው መድረክ በድምቀትና በሰላም እንዲጠነቀቅ የወረዳው አመራሮች የቀበሌ አመራሮች፣የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳው ዉሃ ማዕድን ባለሙያዎች ለዚህ ስኬት አስተዋጾ ያደረጉት አካላትን ዋና አስተዳዳሪው አመስግነዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

22/05/2026

Address

ሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ
Alaba K'ulito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share